ዓመት በዓላት እና ታሪካዊ ማስታወሻዎች
መስከረም ፩፦ አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ፣ ብሄራዊ ቀን በካታሎኒያ እስፓንያ
- 1507 - የፖሎኝ ሠራዊት በኦርሻ ውግያ በሩስያ ላይ አሸነፈ።
- 1806 - የአሜሪካ መርከቦች በኤሪ ሐይቅ በእንግሊዝ አሸነፉ።
- 1890 - በላቲመር ፔንሲልቬኒያ ፖሊሶች 19 የማዕደን ሰራተኞች በእልቂት ገደሉ።
- 1915 - የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ።
- 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምዕራብ ፈለሱ።
- 1994 - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ታጣቂዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ።
- ፲፩፻፹፬ ዓ/ም- በመስቀል ጦርነት የእንግሊዝ ንጉሥ ቀዳማዊ ሪቻርድ በሳላዲን ላይ በአርሱፍ ውግያ አሸነፈ።
- ፲፬፻፵፪ ዓ/ም - በቱሙ ምሽግ ውግያ የሞንጎል ሃያላት የቻይናን ንጉስ ማረኩ።
- ፲፭፻፮ ዓ/ም - የስኮትላንድ ንጉሥ ጄምስ ፬ኛ እንግሊዝን ወርሮ በፍሎደን ሜዳ ውግያ ተሸንፎ ሞተ።
- ፲፭፻፴፭ ዓ/ም - አምባ ሰሜን በተባለ ሥፍራ ላይ በቡርቱጋል ሠራዊት እና በአህመድ ግራኝ መኻከል በተካሄደው ጦርነት ላይ ዶም ክርስቶፍ ዳጋማ በጥይት ቆስሎ በግራኝ ወታደሮች ተማረከ።
- ፲፰፻፺ ዓ/ም - የዳግማዊ ምኒልክ የጦር አበጋዞች የከፋውን ንጉሥ ጋኪ ሸሮቾ በመማረክ ያንን መንግሥት ጨረሱ።
- ፲፱፻፴፭ ዓ/ም - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪቃን ስትቀርብ በጀርመኖች ተኩስ ሰመጠች።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ከ ፶፰ ዓመታት በሥልጣን፣ መጀመሪያ በአልጋ ወራሽነትና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነት፣ ከ መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በንጉሠ ነገሥትነት ኢትዮጵያን የመሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በደርግ የአብዮት ሥርዓት ተሽረው ከሥልጣን ወረዱ።
- ፲፱፻፸ ዓ/ም -የጸረ-አፓርታይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
- ፲፱፻፹፭ ዓ/ም - መይ ካሮል ጀሚሶን በጠፈር የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊት ሆነች።
- 1883 - ሳልስበሪ ሮዴዚያ ተመሰረተች።
- 1893 - በፊሊፒንስ ጦርነት የፊሊፒንስ ተዋጊዎች በአሜሪካ ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ።
- 1899 - በአውሮፓ የተደረገ መጀመርያው የአውሮፕላን በረራ።
- 1907 - በ1ኛ አለማዊ ጦርነት የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች ጀርመን ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ (ናሚቢያ) ወረሩ።
- 1952 - መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ።
- 1996 - ስዊድን በምርጫ ለዩሮ እምቢ አለች።
- ፲፭፻፴፬ - ሳንቲያጎ ቺሌ በኗሪ አርበኞች ጠፋ።
- ፲፮፻፪ - የስፓንያ ከተማ ቫሌንሲያ ሞሪስቾዎችን (አረብ ክርስቲያን) ሁሉ አባረራቸው።
- ፲፮፻፸፮ - የአውሮፓ ሠራዊት በቪዬና ውግያ ቱርኮችን አሸነፉ።
- ፲፰፻፺፬ - የአሜሪካ ፕሬዚደንት መኪንሊ በነፍሰ ገዳይ ጥይት ሲሞቱ ቴዮዶር ሩዝቬልት ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፶፫ - "ኦፔክ" -" የነዳጅ አስወጪ አገራት ድርጅት" - ተመሰረተ።
- ፲፫፻፵፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው መነኩሴ አባ ኤውስጣቴዎስ በስደት በሚኖሩበት አርመን አገር ላይ ሞቱ።
- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም -አጼ ልብነ ድንግል በነገሡ በ፴፪ ዓመታቸው ሐሙስ ዕለት ደብረ ዳሞ ላይ አረፉ። የንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን፣ ዘውድና ዙፋናቸው በዚሁ ዕለት ወደልጃቸው የ፲፰ ዓመቱ አጼ ገላውዴዎስ (ስመ መንግሥት፣ አፅራር ሰገድ) ተላለፈ።
- ፲፮፻፪ ዓ/ም - የእንግሊዝ መርከበኛ ሄንሪ ሀድሰን (በዛሬዋ ኒው ዮርክ ከተማ) በስሙ የተሠየመውን የሀድሰን ወንዝን አገኘ።
- ፲፰፻፭ ዓ/ም - የናፖሌዎን ወራሪ ሠራዊት እንዳይማርከው የሩሲያ ሰራዊት የመስኮብን ከተማ አቃጠለ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም በወንጀላዊ ልብ ወለድ ጽሑፎቿ “አቻ የላት” የምትባለው እንግሊዛዊቷ ደራሲ አጋታ ክሪስቲ (Agatha Christie)፣ ቶርኪ (Torquay) በምትባል ከተማ ተወለደች። (ክሪስቲ በ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሞተች)
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ ታንክ የተባለው የጦር መሣሪያ አገልግሎት ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራና ኢትዮጵያ በ«ኅብረታዊ መንግሥት» እንዲዋሃዱ አጸደቀ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - በሁለት ትላልቅ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ድርጅቶች የመሪዎች መፈንቅል ተፈጸመ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት ስድስት ዓመት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ ሥራቸውን ለቀቁ። አቶ ግርማን የሚተኳቸው ምክትላቸው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይሆናሉ ይባላል። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አማረ አምሳሉም ሥራቸውን ለቀቁ
- ፬፻፷፱ - ሮሙሉስ አውግስጦስ የመጨረሻው ምዕራብ ሮማ ንጉስ ወደቀ።
- ፲፮፻፶፩ - ኦሊቨር ክሮምዌል ዓረፉ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ.ም. - የግብጽ ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜናኽም ቤጊን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር ሸምጋይነት፣ ከ፲፪ ቀናት የምሥጢር ድርድር በኋላ፤ በካምፕ ዴቪድ የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ተፈራረሙ።
- ፫፻፹፯ዓ/ም - የሮማ ንጉዛት ክርስቲያናዊ ቄሳር ቀዳማዊ ቴዎዶስዮስ ዘውዱን ለመንጠቅ የተነሳውን አረመኔያዊ የምዕራብ ሮማ መሪ አውግንዮስን በፍሪጊዱስ ውግያ ሲያሸንፍ የሮማ ክርስቲያናዊ ንጉዛት በመጽናቱ የክርስትና ሃይማኖት በአውሮፓ ቀደምትነትን እንዲይዝ አድርጎታል።
- ፲፰፻፺፱ ዓ/ም - በሆንግ ኮንግ አካባቢ የተከሰተ አውሎ ንፋስ እና የባሕር ሞገድ (tsunami) ፲ ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሁለተኛው ዋና ፀሐፊ፣ ሲዊድናዊው ዳግ ሀመርሾልድ በ’አየር ዠበብ አደጋ’ በቀድሞዋ ሮዴዚያ (የአሁኗ ዚምባብዌ) ላይ ሞቱ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ፤ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር እንግሊዝ አገር በስደት ላይ እንዳሉ፣ በተወለዱ በስድሳ ዓመታቸው ዓረፉ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ዛንዚባር ደሴት ላይ የተወለዱት የታንዛንያው ዜጋ ሳሊም አህመድ ሳሊም ስምንተኛው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ በመሆን ሥልጣኑን ከ ኤዲ ኡማሩ ተረከቡ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው ያዘጋጁትን “የታሪክ ማስተወሻ” ላኩ። በመስከረም ወር ፲፱፻፹፮ ዓ/ም በጦብያ መጽሔት ላይ የወጣው ይኼው የትሪክ ማስታወሻ ለሕይወት ታሪካቸው ዋቢ ምንጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረው ኢቲ-ኤጂዩ (ET-AGU) ዲ-ሲ ፫ (Douglas C-47 A -20-DK) አየር ዠበብ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ፣ ከባረንቱ ማረፊያ ሊነሳ ሲያኮበኩብ በአፍንጫው ተደፍቶ ሲከሰከስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም - የቀድሞዋ መካከለኛ አፍሪቃ ንጉዛት መንግሥት (Central African Empire) መሪ ዣን ቢዴል ቦካሳ በፈረንሳይ መንግሥት ዕርዳታ በተደራጀ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ተወገዱ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት በየዓመቱ በመስከረም ወር በሁለተኛው ሳምንት ዕለተ ሰኞ እንዲከበር በተወሰነው ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ ያለበት ሰንደቅ ዓላማ ቀን።
- ፲፮፻፳፭ ዓ/ም - በዙፋን ስማቸው "መልአክ ሰገድ" የሚባሉት ዓፄ ሱስኒዩስ በጽኑ ደዌ ታመው በዕለተ ዐርብ ሞቱ፤ አዘዞ ላይ ተቀበሩ።
- ፲፯፻፹፭ ዓ/ም በፈረንሲስ የዘውድ ስርዓት ተሽሮ አገሪቱ ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፱፻፪ ዓ/ም - የጋናው የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ክዋሜ ንክሩማ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፵ ዓ.ም - የክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አጽም በስደት ዘመን አርፈው ከተቀበሩበት ከእንግሊዝ አገር ወደ ውድ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሶ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተቀበረ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሥራ ሚኒስትር ከአሜሪካ ጉዟቸው ሲመለሱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ቦይንግ ፯መቶ፳-ቢ (Boeing 720B) ጄት አውሮፕላኖች መግዣ እና ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የሚውል ብድር ከ ኤክሲም ባንክ (Export Import Bank) ጋር የስምምነት ውል መፈራረማቸውን ይፋ አደርጉ።
- ፳፻፪ ዓ/ም በምዕራብ ጐጃም የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮ አስተባባሪዎች ላይ ድብደባ ተፈጸመ
- ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. - የሙሶሊኒ አዲስ ፋሺስታዊ መንግሥት በአዶልፍ ሂትለር ግፊት እና ድጋፍ 'የጣልያን ሕብረተሰባዊ ሪፑብሊክ' በሚል ስም በሰሜን ጣልያን ጀመረ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - ቀድሞ "የፈረንሣይ ሱዳን" የተባለው ቅኝ ግዛት የማሊ ሪፑብሊክ ተብሎ ነጻነቱን አወጀ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ምክትል ፕሬዚደንት እና ዋና ጸሐፊ አዲስ ሥልጣን በያዘው የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ትዕዛዝ ተይዘው ታሠሩ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም የህውሐት ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ መለስ ዜናዊ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ መረጠ፡ ...
- ፮፻፲፭ ዓ/ም - ነቢዩ መሐመድ ከመካ እስከ መዲና ያደረገውን የሱባዔ ጉዞ (ሂጅራ) ፈጸመ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም-ስዋዚላንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -ጊኒ-ቢሳው ነጻነቷን ከፖርቱጋል ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - በአፍሪቃ አኅጉር ደቡባዊ አካል፣ በ ኢያን ስሚዝ የሚመራው የሮዴዚያ (የአሁኗ ዚምባብዌ) የነጭ አስተዳደር መንግሥቱን ለበዢው የጥቁር ሕዝብ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማስረከብ ተስማማ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የጄኔቫውን ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር አግኝቶ ፵፰ኛው አባል ሆኗል።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ (ዘብሔረዘጌ) በዚህ ዕለት በእሥራት ላይ በነበሩበት ጅረን በሚባል በጅማ ከተማ አቅራቢያ ባለ ቦታ በተወለዱ በ ፸፱ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም አየር ዠበብ (አውሮፕላን) አብራሪው ሰሎሞን ግዛው በዚህ ዕለት ተወለዱ።
መስከረም ፲፮፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት የመስቀል ዋዜማ
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት የኔልሰን ማንዴላ የመጀመሪያ ሚስት የነበሩት ዊኒ ማንዴላ ተወለዱ።
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሰጠው ውሳኔ መሠረት ፥ኤርትራ ከኢትዮጵያጋራ ተዋሃደች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በአሜሪካ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ ጆን ኤፍ ኬኔዲ እና ሪቻርድ ኒክሰን በመጀመሪያው የቴሌቪዥን ሙግት ላይ በሺካጎ ከተማ ተሳተፉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የየመን አረባዊ ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በፈረንሳይ እና ብሪታንያ በኅብረት የተሠራው ‘ኮንኮርድ’ የተባለው አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትላንቲክ ውቅያኖስን በማቋረጥ የፍጥነት ክብረ ወሰን አስመዘገበ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - ‘ጁላ’ (MV Joola) የተባለች የሴኔጋል የንግድ መርከብ ከተፈቀደላት የሰው ጭነት በላይ ሦስት እጥፍ ጭና ስትጓዝ ከጋምቢያ ጠረፍ አካባቢ ላይ ሰምጣ ወደ ፩ሺ ፰፻፷፫ መንገደኞች ሕይወታቸውን አጡ።
መስከረም ፲፯፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በዓለ መስቀል
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - በትልቁ የመስቀል በዓል ቀን መኳንንቱ ከነሠራዊቱ፤ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስና እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ ከነካህናቱ በተሰበሰቡበት በ፲ ነጥብ የተዘረዘረው የልጅ እያሱ ወንጀል ተነቦ እሳቸውን ሽረው ወይዘሮ ዘውዲቱን ንግሥት፣ ደጃዝማች ተፈሪን ራስ ብለው አልጋ ወራሽና የመንግሥቱ እንደራሴ ተደረጉ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በፋሺስት ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን በመደገፍ በእንግሊዝ አገር እርዳታ በመሰብሰብ፣ የኢጣልያን ግፍ እና የምዕራባውያንን ድክመት በማጋለጥ የታገሉት ዕመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተገኙበት በመንግሥታዊ ሥርዓት በኢጣሊያ ጦርነት ሰማዕት ለሆኑ ጀግኖች በተዘጋጀው መካነ መቃብር፣ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም -ሴየራ ሌዎን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ሁለት የአሜሪካ የጦር አየር ዠበቦች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለምን ዙሪያ በአየር በረራ በመቶ ሰባ አምሥት ቀን ካከናወኑ በኋላ ሲያትል ላይ አረፉ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ዓለቃ እስክንድር ፍሌሚንግ (Sir Alexander Fleming) የተባለ ሰው ፔኒሲሊን አገኘ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - ማሊ እና ሴኔጋል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባላት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በአፍሪቃ አኅጉር ላይ የመጀመሪያውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት የግብጽ ሁለተኛ ፕሬዚደንት የነበሩት ኮሎኔል ጋማል አብደል ናስር አረፉ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በሮማው የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር በፓፓነት የተመረጡት ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በተመረቁ በ ሰላሳ ሦስት ቀናቸው ሞቱ።
- ፳፻፩ ዓ/ም - በጅጅጋ ከተማ "አንድነት" በተባለ ሆቴል በተከሰተ ፍንዳታ አራት ሰዎች ሲሞቱ አስር ሰዎች ቆስለዋል።
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት አገራችንን ኢትዮጵያን ሲወር በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገባው ማርሻል ፒዬትሮ ባዶልዮ፤ ተሸናፊዋን አገሩን በመወከል የሽንፈቱን ስምምነት ፈረመ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ከዚያ በፊት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ በ ሶቪዬት ኅብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቾቭ ድንፋታ ተረበሸ። በዚህ ስብሰባ ላይ ክሩስቾቭ ጫማቸውን አውልቀው ጠረጴዛቸውን በመቀጥቀጥ ዓለምን አስገርመዋታል።
- ፳፻፪ ዓ/ም - በሳሞዋ ደሴቶች አጥቢያ የተከሰተው፣ በ ‘ሪክተር ሚዛን’ ስምንት ነጥብ ያስመዘገበው የመሬት እንቅጥቅጥ ‘ሱናሚ’ (tsunami) የሚባለውን የባሕር ነውጥ አስከተለ።
- ፲፱፻፴፮ - የአሜሪካ ሃያላት ወደ ናፖሊ በጣልያን ገቡ።
- ፲፱፻፶፱ - የብሪታንያ ቅኝ ግዛት የነበረችው የደቡብ አፍሪካዋ ቤችዋናላንድ ነጻነቷን ተቀዳጅታ የቦትስዋና ሪፑብሊክ ተብላ ተሰየመች። ሰሬትሴ ካማ የመጀነሪያው ፕሬዚደንት ናቸው።
- ፲፱፻፹፭ - ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ በአንጎላ ፕሬዚዳንት ምርጫ ጆናስ ሳቪምቢን አሸነፉ።
መስከረም ፳፩፦ በዚህ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ማርያምን በዓል በማሰብ ትዘክረዋለች።
- ፲፬፻፵፮ ዓ/ም -ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አስቀመጡ።
- ፲፱፻፵፩ ዓ.ም -ማኦ ዘዶንግ የቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክን መመሥረት ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም - ናይጄሪያ ነጻነቷን ከብሪታንያተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፬ ዓ.ም - የምስራቅ እና የምዕራብ ካሜሩን ክፍሎች ተዋህደው፣ የካሜሩን ፌዴራላዊ ሪፑብሊክን መሠረቱ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ.ም - በአሜሪካ የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ትግል ጄምስ መሬዲዝ የተባለውን ጥቁር ተማሪ ወደ ሚሲሲፒ ዩኒቨርሲቲ መግባት በተከሰተው ግጭት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሰባ አምሥት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - ለሟቹ የግብጽፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናስር የቀብር ስርዓት የወጡ ወደ አምሥት ሚሊዮን የሚገመቱ አዘነተኞች በተነሳ ግርግር እና ግፊያ ብዙ ሰዎች ተጨፍልቀው ሞቱ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በፊሊፒንስ ከተማ ማኒላ ላይ በተካሄደው የቡጢ ውድድር ሞሐመድ አሊ ባላጋራውን ጆ ፍሬዘርን ከአሥራ አራት ዙር ግብግብ በኋላ በነጥብ ብልጫ አሸነፈ።
- ፲፰፻፷፪ ዓ.ም. ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲ ፤ ወይም ማሃትማ ጋንዲ በዛሬው ዕለት ጉጅራት በሚባለው የህንድ ክፍለ ሀገር ውስጥ ፖርባንዳር በምትባል የጠረፍ ከተማ ተወለደ።
- ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. በብሪታንያ የስኮትላንድ ተወላጅ የሆነው ጆን ሎጊ ቤርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ቴሌቪዥን ፈተነ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. ጊኒ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛትነት ተላቃ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. - በጄነራል ኤሚልዮ ደቦኖ የሚመራው የፋሽሽት ኃይል ኢትዮጵያን ወረረ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. - የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ፦ ምስራቃዊ የጀርመን አገር የነበረችው የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ከምዕራባዊው የጀርመን አገር ጋር ተቀላቅላ ክልሏ የጀርመን ፈዴራላዊ ሪፑብሊክ አካል ሆኖ ሕዝቦቿም የአውሮፓ ሕብረት ዜጎች ሆኑ።
- ፲፱፻፹፭ ዓ/ም - በሞቃዲሹ የሶማሌውን የጦር ዓለቃ ሞሐመድ ፋራ አይዲድን ለመያዝ በተደረገው ሙከራ አሥራ ስምንት የአሜሪካ ወታደሮች ሲሞቱ አንድ ሺ ያህል ሶማሌዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፭፻፸፭ ዓ.ም. - የካቶሊኩ ቤተ ክርስትያን ፓፕ ግረጎሪ ፲፫ኛ በኢጣልያ ፤ በፖላንድ ፤ በፖርቱጋል እና በእስፓንያ አገሮች የግሪጎርያዊ ዘመን አቆጣጠርን መሠረተ።
- ፲፭፻፺ ዓ.ም. - የንግሥ ዘመናቸውን (ከ ፲፭፻፶፯ ዓ.ም. እስከ ፲፭፻፺ ዓ.ም.) ሙሉ በቀይ ባሕር በኩል ቱርኮችን (ኦቶማን)፤ በደቡብ የኦሮሞዎችን ጥቃት በመከላከል ያሳለፉት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሰርጸ ድንግል በተወለዱ በ ፵፯ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፰፻፲፯ ዓ.ም. - ሜክሲኮ አዲስ ሕገ መንግሥቷን አጽድቃ የፌዴራል ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፰፻፳፫ ዓ.ም. - ከኔዘርላንድ ጋር በመለያየት የቤልጂግ ሉዓላዊ አገር ተመሠረተ።
- ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. - የኦቶማን ግዛት በሩሲያ ላይ ጦርነት አወጀ። ባንድ በኩል ሩሲያ፤ በሌላው በኩል ደግሞ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና የኦቶማን ግዛት በትብብር የተዋጉት የሁለት ዓመት በላይ ጦርነት የክራይሚያ ጦርነት የሚባለው ነው።
- ፲፱፻፫ ዓ.ም. - የፖርቱጋል ንጉሥ ማኑዌል ፪ኛ ወደብሪታንያ ኮብልሎ አገሪቱ ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፱፻፶ ዓ.ም. - ሩሲያ የመጀመሪያዋን ሰው ሰራሽ ሳቴላይት፣ ስፑትኒክ ፩ መሬትን ለመዞር ተኮሰች።
- ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. - የብሪታንያ ቅኝ ግዛት የነበረችው፣ በቀድሞ ስሟ ባሱቶላንድ ትባል የነበረችው የደቡባዊ አፍሪካ አካል፣ ነጻነቷን ተቀዳጅታ የሌሶቶ ንጉሥ መንግሥት ተባለች።
- ፲፬፻፬ ዓ/ም - በ፲፫፻፸፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ ተቀምጠው ለሃያ ዘጠኝ ዓመት የነገሡትና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል ወደኢትዮጵያ ያስመጡት ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት ፈረሳቸው ረግጧቸው ሞቱ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ/ም -ቶማስ ኤዲሶን የተባለው አሜሪካዊ የፈጠራ ሰው የመጀመሪያውን ተንቀሳቃሽ ምስል (motion picture) አሳየ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የግብጽ ሠራዊት በእስራኤል ላይ የ’ራመዳን ጦርነት’ ወይም የ’ዮም ኪፑር’ ጦርነት በመባል የሚታወቀውን የስድስት ቀን ውጊያ ከፈቱ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - የግብጽ አመጸኛ መኮንኖች ፕሬዚደንታቸውን አንዋር ሳዳትን አደባባይ ላይ በጥይት ደብድበው ገደሏቸው።
- ፲፱፻፲፪ ዓ/ም - የሆላንድን ዓርማ ያዘለው ‘ኬ. ኤል. ኤም’ (KLM) የተባለው እና ከምሥረታው ጀምሮ እስካሁን ስሙንም ሆነ ዓርማውን ሳይቀይር በመቆየት አንደኝነትን ያስመዘገበው ዓየር መንገድ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እጅ ዘውድ ጭነው ንጉሥ ተፈሪ ተባሉ።
- ፲፱፻፳፬ ዓ/ም - የደቡብ አፍሪቃው ጳጳስ እና የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀባይ ዴዝሞንድ ቱቱ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - አምሥት ነባር የፈረንሳይ አየር መንገዶችን በማዋሐድ የአሁኑ ‘ኤየር ፍራንስ’ (Air France) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፵፪ ዓ/ም - የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዚደንት እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቭላዲሚር ፑቲን በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - ናይጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - ኦማንየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓባል ሆነች።
- ፲፱፻፺፬ ዓ/ም - አፍጋኒስታን በ አሜሪካ ሠራዊት ተወረረች።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - ኤርትራዊው ዘፋኝ፣ ገጣሚ እና የሙዚቃ አቀናባሪ አብርሐም አፈወርቂ ቀይ ባህር ውስጥ ሰምጦ በተወለደ በ ፵ ዓመቱ ሞተ።
- ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው ስብከተኛ እና የሰብዓዊ መብት ታጋይ ጄሲ ጃክሰን በዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአርጀንቲናው ተወላጅ ኤርኔስቶ ቼ ጌቫራ ከነአበሮቹ ቦሊቪያ ውስጥ ተያዘ።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - በፓኪስታን እና ሕንድ ድንበር አካባቢ የሚኖሩ ፹፮ንሺህ ያህል ሰዎች በተከሰተው ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ አደጋ ሕይወታቸውን አጡ።
- ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. - የሴኔጋል መሪ የነበሩት ሌኦፖልድ ሴዳር ሴንግሆር ተወለዱ።
- ፲፱፻ ዓ/ም - የሐረር ገዥ የነበሩት ደጃዝማች ይልማ መኮንን (የራስ መኮንን የመጀመሪያ ልጅ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታላቅ ወንድም) አርፈው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአባታቸው መቃብር ተቀበሩ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ የኢትዮጵያ አራተኛው ዋና መላክተኛ (Envoy Extraordinary and Minister Plenipotentiary) የነበሩት ሐኪም አዛዥ ወርቅነህ (Dr. Charles Martin) በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. - ዩጋንዳ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. - የአርጀንቲና ተወላጅ የነበረው፤ በአብዮት ቅስቀሳና ፍልሚያ፣ በተለይም በኩባ አብዮታዊ ትግል የሚታወቀው ኤርኔስቶ ጌቫራ በቦሊቪያ የአብዮት ፍንዳታ ሊያንቀሳቅስ ሲሞክር በተያዘ በማግስቱ ተረሽኖ ሞተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን፣ ሎንዶን በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ለማገገም በዛሬው ዕለት ወደ ስዊዘርላንድ አመሩ
- ፮፻፸፫ ዓ/ም - የቀሊፋ ቀዳማዊ ያዚድ ወታደሮች በካርባላ ጦርነት ላይ የነቢዩ ሞሐመድን የልጅ ልጅ የአሊ ልጅ ሁሴንን አንገቱን በመቁረጥ ሰውት። ሺአቶች ዕለቱን በሐዘን ያስቡታል፡፡
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - የጋናው የገንዘብ ሚኒስትር ኮምላ አግቤሊ ግብዴማ፣ በዘረኛነት ጥላቻ ምክንያት በዴላዌር ምግብ ቤት መስተንግዶ በመነፈጋቸው፣ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ድዋይት አይዘንሃወር ይቅርታ ጠየቋቸው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ቶክዮ፣ ጃፓን ላይ የተካሄደው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር መክፈቻ ስርዓት ለመጀመሪያ ጊዜ በሳተላይት ተሰራጨ።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - ሁለት ትላልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ነውጦች ኤል አስናም በምትባለዋ የሰሜናዊ አልጄሪያ ከተማ ላይ የ፳ ሺህ ሰዎችን ነፍስ ጥፋትና የብዙ ሺህ ሰዎችን የአካል ጉዳት አስከተሉ።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - ዩጋንዳን መጀመሪያ ወደነጻነትና በጄኔራል ኢዲ አሚን መፈንቅለ መንግሥት እስከወደቁ ጊዜ ድረስ በቀዳማዊ ጠቅላይ ሚንስትርነት፤ ከአሚን ውድቀት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በመፈንቅለ መንግሥት እስከተሰደዱ ድረስ ያገለገሉት አፖሎ ሚልተን ኦቦቴ ጆሃንስበርግ ላይ አረፉ::
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ድዋይት አይዘንሃወር በዘርያነት ምክንያት በዴላዌር ምግብ ቤት መስተንግዶ የተከለከሉትን የጋና ገንዘብ ሚኒስቴር ኮምላ አግቤሊ ግብዴማን ይቅርታ ጠየቁ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የክራሩ ጌታ፤ የኮሪያው ዘማች፤ ካሳ ተሰማ በተወለደ በ፵፯ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባዔ (Ethiopian Human Rights Council) በ ፴፪ መሥራች አባላት አዲስ አበባ ላይ ተመሠረተ።
- ፲፯፻፸፫ዓ/ም - በካሬቢያን ባሕር ላይ የተነሳው የአውሎ ንፋስ ማዕበል በማርቲኒክ እና በባርቤዶስ ደሴቶች ላይ ሲጎርፍ እስከ ፳፪ ሺ ሰዎች ጠፍተዋል።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ፓትሪያርክ፣ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የክብር ዘበኛ ሠራዊት ሸንጎ ሊቀ መንበር በደርግ ተያዙ። በዚሁ ዕለት የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ፩መቶ ሚሊዮን ብር የተገመተ ንብረት ለቀድሞ ባለ-ሥሎጣኖቻቸው ሰጥተዋል ተባለ።
- ፲፱፻፹፯ ዓ/ም - የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሓቅ ራቢን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስምዖን ፔሬዝ የዓመቱን የኖቤል ሰላም ሽልማት በኅብረት ተቀበሉ።
- ፲፱፻፵፯ ዓ.ም - የብሪታንያዋ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ ለሁለት ሣምንት ጉብኝት የመጡትን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በለንደን ቪክቶርያ የባቡር ጣቢያ ተቀበሉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ.ም - የአሜሪካ ዓየር ኃይል የስለላ አውሮፕላን በኩባ ላይ የሶቭየት ኅብረት የኑክሊየር መሣሪያዎች በመገጣጠም ላይ መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃ ፎቶግራፎች አነሳ። ይኼም የኩባ ሚሳይል ክራይስስ በመባል የተጠራውን አደገኛ መፋጠጥ ያስከተለ ሂደት ነው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም - በአሜሪካ የሰብዐዊ መብት እንቅስቃሴ መሪ የነበሩት ጥቁር አሜሪካዊ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፹፯ ዓ.ም - የፍልስጥኤም መሪ ያስር አራፋት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ይስሓቅ ራቢን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ (የአሁኑ ፕረዚዳንት) ስምዖን ፔሬስ የዓመቱ የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. - በምሥራቅ አፍሪቃ የታንዛኒያ መሪ የነበሩት፤ በወገኖቻቸው አቆላማጭ ጥሪ ምዋሊሙ (አስተማሪ) በመባል የሚታወቁት ጁልየስ ካምባራጌ ኔሬሬ በለንደን ሆስፒታል በሉኪሚያ በሽታ ምክንያት አረፉ። እኒህ ታላቅ አፍሪቃዊ መሪ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን ከመሠረቱት አንዱ ሲሆኑ፤ በአህጉሩ የመጀመሪያው በፈቃዳቸው የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን የለቀቁ ናቸው።
- ፲፭፻፸፭ ዓ.ም. - የግሪጎሪያዊ ዘመን አቆጣጠር በዛሬው ዕለት በኢጣልያ፤ በፖላንድ ፤ በፖርቱጋል እና በእስፓንያ ከመስከረም ፳፭ ቀን በቀጥታ ወደ ጥቅምት ፭ ቀን በመዝለል ተጀመረ።
- ፲፮፻፺፱ ዓ/ም - በዓፄ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥት ልዑል ሰገድ) ትዕዛዝ፣ ሸሽተው ጣና ሐይቅ ላይ በጨቅላ መንዞ ደሴት የነበሩትን አባታቸውን ዳግማዊ ኢያሱ አድያም ሰገድን ጳውሎስ እና ደርመን የተባሉ ነፍሰ ገዳዮች ሕይወታቸውን ካጠፉ በኋላ አስከሬናቸውን በእሳት አቃጠሉት። ከቃጠሎ የተረፈውን ካህናቱ በታንኳ ወስደው ምጽራሓ ደሴት ላይ ቀበሩት።
- ፲፯፻፩ ዓ/ም - ከ፪ዓመት በፊት በዚህ ዕለት ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱን (ስመ መንግሥት አድያም ሰገድ) የገደሉትን ጳውሎስ እና ደርመንን ንጉሠ ነገሥቱዓፄ ቴዎፍሎስ የስቅላት ሞት ፍርድ ፈረዱባቸው።
- ፲፰፻፰ ዓ.ም. - የፈረንሳይ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ ናፖሌዮን በወተርሉ ጦር ሜዳ ላይ ከተሸነፈ በኋላ በአሸናፊዎቹ በብሪታንያ ቁጥጥር ሥር አትላንቲክ ውቅያኖስ ወደምትገኘው የቅድስት ሔሌና ደሴት ተሰደደ።
- ፲፰፻፴፯ ዓ.ም. - ታዋቂውና ተቀዳሚው የጀርመን ፈላስፋ ፍሬድሪክ ቪልሄልም ኒቺ ተወለደ።
- ፲፱፻፫ ዓ.ም. - ታዋቂው ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንዳዶም ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ ተወለዱ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በፈረንሳይ አገር የናዚ ጀርመን ደጋፊ የነበረው የቪሺ አስተዳደር ጠቅላይ ሚንስቴር የነበሩት ፒዬር ላቫል በሞት ተቀጡ። ላቫል ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከነበሩት ዊሊያም ሆር ጋር በታኅሣሥ ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለፋሽሽት ኢጣልያ በሚያመች መልክ ለመከፋፈል የምስጢራዊ ስምምነት የፈጸሙ ናቸው።
- ፲፱፻፴፱ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወንጀለኛነቱ የሞት ቅጣት የተፈረደበት ኸርማን ጎሪንግ ለቅጣቱ መፈጸሚያ ጥቂት ሰዐታት ሲቀሩ ሳያናይድ መርዝ በመውሰድ ራሱን ገደለ
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. - የቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት መሪ የነበሩት ኒኪታ ክሩስቼቭ ከሥልጣን ተሽረው፣ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት በአሌክሲ ኮሲጊን፤ በኮሙኒስት ፓርቲ ሊቀመንበርነት ደግሞ በሌዮኒድ ብሬዥኔቭ ተተኩ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ ልጅ መቶ-ዓለቃ ልዑል መኮንን መኮንን ትምህርት ላይ ከነበሩበት ከአሜሪካ ወደአገራቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ደርግ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. - የቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚካይል ጎርባቾቭ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፹፮ ዓ.ም. - የደቡብ አፍሪቃ መሪዎች ኔልሰን ማንዴላና ፍሬድሪክ ዊሌም ደክለርክ የዓመቱ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊዎች መሆናቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው የያዘች የሰማይ መንኮራኩር ተኮሰች።
- ፲፰፻፸፱ ዓ/ም - የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት ዴቪድ ግሪን ወይም ዴቪድ ቤንጎርዮን ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ የመጀመሪያዋን አቶሚክ ቦንብ አፈነዳች።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በጋማል አብደል ናስር ሞት ምክንያት በግብጽ አንዋር ሳዳት የአገሪቱ ፫ኛ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የዋቢ ሸበሌ ሆቴል ድርጅት በደርግ መንግሥት ተወረሰ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቫቲካን የተሰበሰቡ የዓለም ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳሳት፣ በ ፬፻ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ጣሊያናዊ ያልሆኑትን በ ፖላንድ የክራካው ካርዲናል የነበሩትን ካሮል ዮሴፍ ቮይትዋን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፖፕ) በማድረግ መረጡአቸው። ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በተመረጡ በ ፴፫ ቀናቸው በድንገት በሞት የተለዩትን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስን በመተካት ፪፻፷፬ናው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነዋል።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን የኬፕ ታውን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ደቡብ አፍሪቃዊው ዴዝሞንድ ቱቱ የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀባይነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ስመ ጥሩው የእስራኤል ጄኔራል፤ እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ሚንስቴርነት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ማዕረግ የበቁት ሞሼ ዳያን በተወለዱ በ፶፮ ዓመታቸው በሞት ተለዩ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር የሱዳን ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ.ም - ታዋቂው አይሁዳዊው የጀርመን ጉስነኛ(physicist) አልበርት ኣይንስታይን በትውልድ አገሩ እየገነነ ከመጣው የናዚ ጭቆናና ሥርዐተ መንግሥት ሸሽቶ አሜሪካ አገር ገባ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ.ም - አረባዊ የነዳጅ አምራች አገሮች፣ እስራኤልን ረድታችኋል በማለት የወነጀሏቸውን ምዕራባዊ አገሮችችና በጃፓን ላይ ለአንድ ዓመት ሙሉ የነዳጅ ክልከላ ስልት አካሄዱ።
- ፲፱፻፺ ዓ.ም - የአርጀንቲና ተወላጁ ታዋቂው አብዮታዊ ተዋጊ ኤርኔስቶ ቼ ገቫራ፤ በቦሊቪያ ተግድሎ በተቀበረ በ፴ ዓመቱ አጽሙ ወደ «ሁለተኛ አገሩ» ኩባ ተመልሶ በክብር ተቀበረ።
- ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. - የኤሌክትሪክ መብራትን እንዲሁም አምፑልን በመፍጠር የሚታወቀው አሜሪካዊው ቶማስ አልቫ ኤዲሰን በ ኒው ጀርሲ ክልል ዌስት ኦሬንጅ ላይ በተወለደ በ ፹፬ ዓመቱ አረፈ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - የአሜሪካውን ፴፭ኛ ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል በመባል የተያዘው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ በዛሬው ዕለት ተወለደ። ኬኔዲ በሞቱ በሁለተኛው ቀን እሱም ተገደለ።
- ፲፱፻፸ ዓ.ም. - የምዕራብ ጀርመን ወታደራዊ ጸረ ሽብርታዊ ቡድን በሽብርተኞት ተጠልፎ ሞጋዲሹላይ ያረፈውን የሉፍትሃንሳ አውሮፕላን ካስገደዱት አራት ሽብርተኞች መኻል ሦስቱን በመግደል የተያዙትን ፹፮ ሰላማዊ ተሳፋሪዎች ነጻ አወጣ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. - በቀድሞው የምሥራቃዊ ጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ መሪ የነበሩት ኤሪክ ሆኔካ ከሥልጣን ወረዱ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም -የዓለም መንግሥታት ማኅበር በግፍ ኢትዮጵያን በወረረችው ፋሺስት ኢጣልያ ላይ የዱኛ ማዕቀብ ውሳኔ አስተላለፈ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኅብረተ-ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፣ የቀድሞ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ባለሥልጣናት የሚዳኝ ወታደራዊ የፍትሕ ሸንጎ መሠረተ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም.- ስመ ጥሩው የቡልጋ ተወላጅ አርበኛና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀ መንበር፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን በ ፷፬ ዓመታቸው መስኮብ ላይ አረፉ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የሞዛምቢክን ፕሬዚደንት ሳሞራ ማሼልን እና አብረዋቸው የሚጓዙ ፴፫ ሰዎችን የጫነው አየር ዠበብ በአገሪቱ ውስጥ ሌቦምቦ ተራራ ጋር ሲጋጭ ተሳፋሪዎቹ ሕይወታቸው አልፏል።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን በነፍሰ ገዳይነት እና በሰፊው በሰው ልጅ ላይ ወንጀል ሠርተዋል በመባል ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች ሁሉ ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - በከፍተኛ ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያንን በሞያሌ በኩል ሸኝተው ለማስኮብለል የሞከሩ የውጭ ዜጋ የሆኑ ሁለት የአውሮፓ ኮሚሽን ሠራተኞች በወንጀል ከተጠረጠሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በዛሬው እለት እጅ ከፍንጅ ተያዙ ከተባለ በኋላ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ዋና መምሪያ ይህን ህገ ወጥ ተግባር የፈፀሙት ሁለቱ የውጪ ዜጎችም ከአገር እንዲወጡ መወሰኑን ገለፀ፡፡
- ፲፯፻፴፫ ዓ/ም - “የአውስትሪያ አልጋ የውርስ ጦርነት” ዐቢይ ምክንያት የሚባለው፣ ንግሥትማሪያ ተሬዛ አባቷ ንጉሥ ቻርልስ ስድስተኛ በዛሬው ዕለት አርፎ እሷ ዙፋኑን መውረሷ ነው።
- ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. - በ ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ሐረር ላይ ሰፍሮ ይኖር የነበረው፣ ፈረንሳዊው ግጥም ተቃኝ አርተር ራምቦ (Arthur Rimbaud) በዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፰፻፹፬ ዓ.ም -በጎረቤት አገር በኬንያ አገራቸውን ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻ ለማውጣት በመጋደል ቆይተው አገሪቱ ነጻ ስተውጣም የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ተወለዱ።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - የትግራይ ግዛት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስ ቡልጋ ውስጥ አርፈው በእቲሳ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ተቀበሩ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ.ም - በብሪታንያ ቅኝ ግዛት፣ ኬንያ ውስጥ ለነጻነት ይካሄድ የነበረውን የማው ማው ትግልን ለማክሸፍ በሚል ምክንያት የግዛቷ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው ኤቨሊን ቤሪንግ “አደገኛና አስቸኳይ ሁኔታ” አውጆ የሽብሩ መሪዎች የነበሩትን እነጆሞ ኬንያታን በእሥራት ቁጥጥር አዋለ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም - ፴፩ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኸርበርት ሁቨር ኒው ዮርክ ከተማ ላይ በተወለዱ በ፺ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፭፻፲፫ ዓ.ም - የፖርቱጋል ተወላጅ ፈርዲናንድ ማጄላን በደቡብ አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ መርከብ የሚያስተላልፍ በስሙም የሚጠራውን የማጄላን ስትሬይት (Magellan Straits) አገኘ።
- ፲፯፻፺፰ ዓ.ም. - በታዋቂው የብሪታንያ የባህር ኃይል አበጋዝ ሆሬሽዮ ኔልሰን መሪነት ከፈረንሳይና ከእስፓኛ ከተውጣጣ የባሕር ኃይል ጋር የትራፋልጋር ውጊያ (Battle of Trafalgar) እየተባለ በታሪክ በሚታወቀው ጦርነት የብሪታንያ ኃይል ድልን ተቀናጀ። ሆሬሽዮ ኔልሰንም በዚሁ ውጊያ ሞተ።
- ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. - ዳይናማይትን የፈጠረ፤ ፖካርሲ(chemist) ፤ መሐንዲስ እና የጦር መሣሪያ ሠሪ የነበረው እንዲሁም የኖቤል ሽልማትን የመሠረተው የስዊድን ተወላጅ አልፍረድ በርንሃርድ ኖቤልበዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ.ም - የመጀመሪያዋ ሐጽናሚ(Medical Nurse) በመባል ስሟ የሚታወቀው ፍሎሬንስ ናይቲንጌል ከ፴፰ ሐጽናሚያን ጋር ወደ ክራይሚያ ጦርነት ዘመቱ።
- ፲፰፻፸፩ ዓ.ም - ከጨሊዛ(carbon) የተሠራ ክር በመጠቀም ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የመጀመሪያውን የጾፓስ(electric) መብራት ብልቃጥ ሞከረ። ይኼውም መብራት ከመቃጠሉ በፊት ለ ፲፫ ሰዐት ተኩል አበራ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የሮማ ኦሊምፒክ የማራቶን ድል አድራጊው አበበ ቢቂላበቶክዮ ውድድር የራሱን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰከንድ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ድልን ተቀዳጀ። ከዚህ ድል ከሰላሳ ስድስት ቀናት በፊት ትርፍ አንጀቱን በቀዶ ሕክምና አስወግዶ ስለነበረ፣ ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳያገግም በአዲስ ክብረ ወሰን ማሸነፉ በማራቶን ውድድር እስካሁን ድረስ አቻ የለሽ ጀግና አድርጎ አስመስክሮለታል።
- ፲፱፻፹፩ዓ.ም - የቀድሞው የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርቆስና ሚስታቸው ኢሜልዳ ማርቆስ በማጭበርበር ወንጀል ኒው ዮርክ ተከሰሱ።
- ፲፯፻፺ ዓ/ም - በፓሪስ ከተማ፣ ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ጫማ ሽቅበት ላይ አንድሬ-ዣክ ጋርኔራን የተባለ ሰው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዝለያ ጥላ (parachute) ዘለለ።
- ፲፰፻፵ ዓ/ም - ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ የሸዋን ንጉዛት ወርሰው በዙፋኑ ተቀመጡ። ሸዋን ለሠላሳ ዐራት ዓመታት የገዙት አባታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ደብረ ብርሃን ላይ አረፈው በአንኮበር ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በኩባ ደሴት ላይ የሶቪዬት ሕብረት የኑክሊየር መሣሪያዎች ማስቀመጧን በስለላ መረጃዎች ካረጋገጡ በኋላ፤ በደሴቷ ዙሪያ በአየርም ሆነ በባሕር ላይ የእንቅስቃሴ እገዳ ትእዛዝ አስተላለፉ።
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - ግብጻዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ አርፈው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ፲፱፻፬ ዓ/ም - በቱርክና በኢጣሊያ መካከል በነበረው ጦርነት የቱርኮችን የጦር ግንባር ከአየር ለመሰለል የኢጣልያ አውሮፕላን ከሊቢያ ተነሳ። ይሄም ድርጊት አውሮፕላን በጦርነት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለበት ዕለት ነው።
- ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ፔሌ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የብራዚል እግር ኳስ ተጫውች ኤዲሶን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ተወለደ። ፔሌ በዓለም የኦሊምፒክ ሸምቡድ (International Olympic Committee) “የ፳ኛው ክፍለ ዘመን አትሌት” ብሎታል።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዚህ ዕለት በአሜሪካ ርዕሰ ከተማ ዋሺንግቶን ዲ.ሲ. ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የብሪታኒያ ቅኝ ግዛት የነበረችው የቀድሞዋ ‘ሰሜን ሮዴዚያ’፣ የዛምቢያ ሪፑብሊክ ተብላ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፺፩ዓ/ም - ተክሊት(ትዮ) የሚባል የከፍተኛ IQ ባለቤት በዓድዋ ውስጥ በዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፺፰ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊታ የሰብአዊ መብት ታጋይ ዕመት ሮዛ ፓርክስ በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ ዋና ተወካይ አድላይ ስቲቨንሰን፣ የሶቪዬት ሕብረት በኩባ ደሴት ላይ የኑክልዬር መሣሪያዎችን ማስቀመጧን የሚያሳዩ ከአየር የተነሱ ማስረጃ ምስሎችን ለጸጥታ ጉባዔው አቀረቡ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በአፍሪቃ ከብሪታንያ ነጻነቷን በመቀዳጀት ዘጠነኛዋ አገር፣ የቀድሞዋ የሰሜን ሮዴዥያ፤ አዲሷ ዛምቢያ ኬኔዝ ካውንዳን የመጀመሪያው ፕሬዚደንት አድርጋ መረጠች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ታይዋንን ከአባልነት አስወጥቶ የቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክን በአባልነት እንድትገባ የሚያስችለውን ድንጋጌ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ አጸደቀ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ስመጥሩው ኢትዮጵያዊ የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ አረፈ። አበበ በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም በሮማ የኦሊምፒክ ውድድርና በ፲፱፻፶፮ በቶክዮ የኦሊምፒክ ውድድር አሸናፊ ሲሆን በኦሊምፒክ ውድድር የወርቅ ሽልማት በማግኘት የመጀመሪያው የሰሃራ በታች አፍሪቃዊ ነው።
- ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - በ ካሬቢያን ባሕር ላይ በምትገኘው የግሬናዳ ደሴት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደበት ሣምንት ውስጥ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን “የአሜሪካን ዜጋዎች ደኅንነት” ለመጠበቅ በሚል ምክንያት ደሴቷን በአገራቸው ሠራዊቶች አስወረሩ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በረሀብ ለተጎዱት ወገኖች እርዳታ የአውሮፓ ሕብረት 1.8 ሚሊዮን ፓውንድ (£1.8 million) ዕርዳታ ለገሠ።
- ፲፱፻፲፪ ዓ.ም - የመጨረሻው የኢራን ንጉሠ ነገሥት ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ በዚህ ዕለት ተወለዱ
- ፲፱፻፵ ዓ.ም - የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ሚስትና ስድሳ ሰባተኛዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂላሪ ሮዳም ክሊንተን ተወለዱ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ.ም - በብሪታንያ ብሔራዊ ምርጫ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበሩት በዊንስተን ቸርቺል የሚመራው የኮንሰርቫቲቨ ፖለቲካ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቸርቺልም ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. - የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ቦይንግ 707 አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ ከኒው ዮርክ ከተማ ተነስቶ በፈረንሳይ አገር ፓሪስ ከተማ ድረስ በረረ።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም - ለ ሀያ ስድስት ዓመት በኢራን አልጋ ላይ ከተቀመጡ በኋላ ሞሐመድ ሬዛ ፓህላቪ በ፵፰ኛው የልደት በዓላቸው፣ በራሳቸው እጅ ዘውድ ጫኑ። የሚስታቸውን የንግሥት ፋራንም ዘውድ ጫኑላቸው።
- ፲፱፻፺፬ ዓ.ም - ብዙ ተችዎች በኢትዮጵያ በ ፳፻፩ ዓ.ም የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ መንግሥት ያጸደቀውን “ጸረ ሽብር” ሕግ ምሳሌ ሆኖለታል የሚባለው የአሜሪካው “ፔትርዮትስ አክት” (Patriots Act) ህግ ሆኖ ጸደቀ።
- ፲፱፻፱ ዓ.ም. - የወሎው ንጉሥ፤ የልጅ እያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤል የልጃቸውን ከሥልጣን መውረድ አዋጅ ተቃውመው በጦር ኃይል ለማክሸፍ ከነሠራዊታቸው ወደ አዲስ አበባ ሲዘምቱ በአልጋ ወራሹ ራስ ተፈሪ መኮንን መሪነት እና በጦር ሚኒስቴሩ በፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ አበጋዝነት የዘመተው ሠራዊት በሰገሌ ጠራ ሜዳ ወረዳ ላይ ገጥመው ከ፭ ሰዐት ውጊያ በኋላ የወሎ ሠራዊት ድል ሆነ። ንጉሡም ተማረኩ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. - በፓኪስታን የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ኢስካንደር ሚርዛ በ ጄኔራል አዩብ ካን በሚመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ስሟን ቀይራ ዛይር ተብላ ተሰየመች።
- ፲፱፻፸፩ ዓ.ም - ሦስተኛው የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሜናኽም ቤጊን የዓመቱ የኖቤል የሠላም ሽልማት ተሸላሚዎች መሆናቸው ይፋ ሆነ።
- ፲፭፻፳፬ ዓ.ም. - የአምባሰል ጦርነት፦ በአህመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ ግራኝ አህመድ የሚመራው የአዳል ሠራዊትና በኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ልብነ ድንግል ሠራዊት መኻል በተደረገው ጦርነት የግራኝ አህመድ ወገን አሸነፈ። የደቡብ ኢትዮጵያ ግዛቶችም በአዳሎች ቁጥጥር ስር ዋሉ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም - በአንደኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ፤ ለ ፫፻ ዓመታት በአውስትሪያ ሁንጋሪያ ሥር የነበረችው ቼኮስሎቫኪያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. - የሶቪዬት ሕብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቼቭ አገራቸው በኩባ ደሴት ላይ በድብቅ ያስቀመጠችውን የኑክሊዬር መሣሪያ እንዲወገድ ማዘዛቸውን አስታወቁ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ.ም - በሐረር ቢራ፤ በመብራት ኃይል፤ በኢትዮጵያ ቡና የ እግር ኳስ ቡድኖች እንዲሁም በየመን አል ሻአብ ቡድን በተከላካይነት መደብ የሚሰለፈው ኳስ ተጫዋች ሰሎሞን መልካሙ አንዳርጋቸውበዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፰፻፶፮ ዓ.ም. - ጀኔቭ ላይ የተሰበሰቡ የአሥራ ስድስት አገሮች ልዑካን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ለመመሥረት ተስማሙ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ተመሥርቶ በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. የዓለም አቀፋዊው ማኅበር አባል ሆነ።
- ፲፱፲፭ ዓ.ም. - የኢጣልያው ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሦሥተኛ ለፋሽሽት መሪው ለቤኒቶ ሙሶሊኒ የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ሥልጣን ሰጡ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም - በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሸነፈውና የተሠባበረው የኦቶማን ግዛት አክትሞ በቦታው የቱርክ ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሱዳን መሪ ጄኔራል ሞሐመድ አቡድ በኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ጉብኝታቸውን ጀመሩ። በዚህ ጉብኝትም በንጉሠ ነገሥቱ ፴ኛ የዘውድ በዐል አከባበር ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. - በምሥራቅ አፍሪቃ ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው የታንዛኒያ ሕብረት ሪፑብሊክን መሠረቱ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ሥልጣን ሲጨብጥ ቀርበው እንዲመረመሩ ባዘዛቸው መሠረት ባለመገኘታቸው የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ-ልጅ የልዑል መኮንን መኮንንን እና የትግሬውን አገረ ገዥ የልዑል-ራስ መንገሻ ሥዩምን ንብረት ወረሰ። እንዲሁም ደርግ ባስተላለፈው አዋጅ መሠረት በ”ብሔራዊ የሥራ ዘመቻ” ላይ ሳይሳተፉ የሚቀሩ ተማሪዎችን በጽኑ እንደሚቀጣ በዚሁ ዕለት አስታወቀ።
- ፲፱፻፵ ዓ.ም. - “የንግድና የዋጋ ስምምነት” (General Agreement on Tariffs and Trade (GATT)) ተመሠረተ። ይሄው ተቋም በ፲፱፻፹፰ ዓ.ም. በዓለም የንግድ ድርጅት (World Trade Organisation (WTO)) ተተካ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በኪንሻሳ ከተማ “የጫካው ጉርምርምታ” በተባለው የቦክስ ውድድር፣ ሙሐመድ አሊ በስምንተኛው ዙር ላይ ጆርጅ ፎርማንን በመዘረር አሸንፎ ‘የዓለም ቻምፒዮና’ ማዕርጉን አስመለሰ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) የቀድሞውን ንጉሥ ነገሥት ንብረት በዝርዝር የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ሠየመ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. - ቦናንዛ በሚባለው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ትርዒት ላይ ሊትል ጆን ካርትራይትን ሆኖ በመጫወት በዓለም ስመጥሩነትን ያተረፈው ተዋናይ ማይክል ላንደንበዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. - የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢንዲራ ጋንዲ በሁለት የሲክ የጥበቃ ወታደሮቻቸው እጅ ተገደሉ። ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ በኒው ዴሊ በፈነዳው የሕዝብ ሽብር ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ የሲክ ተወላጆች ሕይወታቸውን አጡ።
- ፲፭፻፭ ዓ.ም. - በቫቲካን ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራል፣ በልዩ ሲስቲን ጸሎት ቤት ጣሪያ ላይ በሚካኤል አንጀሎ የተሳለው ታሪካዊ ስዕል ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ታየ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ/ም - በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ፤ የታላቁ ንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ.ም. - አሜሪካ በዓለም የመጀመሪያውን የሃይድሮጅን ቦምብ በማፈንዳት ማርሻል ደሴቶች (Marshall Islands) ላይ ፈተነች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - በአሜሪካ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ዘመቻቸው ላይ ለዕጩነት የቀረቡት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ የሰላማዊ ተልእኮ ወይም (Peace Corps) በሚል ያቀዱትን ኃሣብ ይፋ አደረጉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ.ም.
- - የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ (ምሥራቅ ጀርመን) አዲስ አበባ ላይ ቤተ-ልዑካን (ኤምባሲ) ከፈተ።
- - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ቤጂንግ የበረራ መሥመር ጀመረ።
- - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት የዓመቱ ሽሽልማት ተቀባይ፣ የሴኔጋል ፕሬዚደንት ሊዮፖልድ ሴዳር ሴንግሆር አዲስ አበባ ገቡ።
- - የቆጵሮስ ደሴት ፕሬዚዳንት አቡነ መቃሪዮስ የንጉሠ ነገሥቱን ፵፫ኛ የዘውድ በዐል ያካተተ የአምስት ቀን ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. - የሠላሳ አራተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት የድዋይት ዴቪድ አይዘንሃወር ባለቤት ሜሚ አይዘንሃወር በተወለዱ በ ሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. - በካሪቢያ ባሕር ላይ የሚገኙት የአንቲጋ እና ባርቡዳ ደሴቶች ነጻነታቸውን ከብሪታንያ ተቀዳጁ።
- ፳፻ ዓ.ም - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መደምደሚያ ላይ ሂሮሺማ ላይ የአቶም ቦምብ የጣለውን የአሜሪካ አየር ኃይል ዠበብ ያበረሩት ብርጋዴር ጄኔራል ፖል ቲቤትስ (Brigadier Gen. Paul Tibbets) በተወለዱ በዘጠና ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፯ ዓ.ም. - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሩሲያ በኦቶማን ንጉዛት ላይ ጦርነት አወጀች።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ታዋቂው ደራሲ ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ላይ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. - በኢትዮጵያ፣ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በድንገተኛ ሞት ከአለፉ በኋላ አልጋ ወራሹ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን ተተክተው በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ ጭነው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተባሉ።
- ፲፱፻፶፯ዓ.ም. - የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ፤ በአዲስ አበባ አካባቢ ማሰራጨት ጀመረ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የዓመቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ሽልማት ከ ፵ሺ የኢትዮጵያ ብር ጋር ለብሪታኒያዊው የታሪክ ምሁር፣ ባዝል ዴቪድሶን (Mr. Basil Davidson) ተሰጠ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) የታወጀውን “ብሔራዊ የሥራ ዘመቻ” እንደምትደግፍ አስታወቀች።
- ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን በየዓመቱ የማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ቀን እንዲከበር የሚያስችለውን ብሔራዊ ሕግ ፈረሙ።
- ፳፻ ዓ.ም. - በሰሜን ሸዋ አስተዳደር፣ በሀገረ-ማርያም ከሰም ወረዳ፣ ኮረማሽ አጥቢያ የሚገኘው የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ መልክ ከተገነባ በኋላ ተመርቆ አገልግሎት ላይ ዋለ።
- ፲፬፻፹፮ ዓ.ም - የጄኖአው ተወላጅ ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ (Christopher Colombus) የአትላንቲክ ውቅያኖስን ከአውሮፓ ወደምዕራብ የማቋረጥ ሁለተኛው ጉዞው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሚኒካ ደሴትን አገኘ።
- ፲፰፻፹፮ ዓ.ም. -ፓናማ በአሜሪካ ማበረታታት ተነስታ ከኮሎምቢያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን አወጀች። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቴዎድሮስ ሩዝቬልት የፓናማ ቦይን ለመቅደድ ፈልገው ኮሎምቢያ ለዚሁ ሥራ መከፈል የፈለገችውን ዋጋ ስላልተስማሙበት ፓናማ ነጻ አገር እንድትሆን ጥረታቸው ተሳካ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ.ም - የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ አገርን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከያዙ በኋላ ራሳቸውን በዘውድ ያነገሡት ዣን ቢዴል ቦካሳ በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ወከር ቡሽ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ተመረጡ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም - የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በ እንጦጦ “መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም” ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዓ መንግሥት ተቀብተው፣ ዳግማዊ ምኒልክ ተብለው የንጉሠ ነገሥት ዘውድ ጫኑ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - በሁንጋሪያ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በኢምሬ ናጊ መሪነት የተነሳውን ብሔራዊ የሕዝብ ዐመጽ ለመደምሰስ የሶቪዬት ሕብረት ወታደሮች የቡዳፔስትን ከተማ ወረሩ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. - የኢራን ሻህ ሬዛ ፓህላቪ በሕዝብ ፍንቀላ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ አብዮታዊ ተማሪዎች የአሜሪካን ኤምባሲ በኃይል ደምሥሠው ገብተው ዘጠና የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥራቸው ስር አዋሉ።
- ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ እና በታላቋ ብሪታኒያ መኻል የስልክ ግንኙነት ተጀመረ። አገልግሎቱ በወቅቱ ከሰኞ እስከ ዓርብ ብቻ ከጧቱ ፭ ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ፮ ሰዓት ከሩብ ድረስ የተወሰነ ሲሆን ከብሪታኒያ በደቂቃ አንድ ፓውንድ ስተርሊንግ ከሩብ (£1.25) ይፈጅ ነበር።
- ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. - በደርግ ዘመን ሕይወታቸው የጠፋው የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ስርዐታቸው ተፈጸመ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን በአገራቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተመሠረተባቸው ክስ በሰው ዘር ላይ አድርገዋል በተባሉባቸው ወንጀሎች ኃላፊነታቸው ተረጋግጦ የስቅላት ሞት ተፈረደባቸው።
- ፳፻ ዓ.ም. - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ የመጀመሪያዋ የጠረፍ መንኲራኩር በጨረቃ ዙሪያ መንሳፈፏን ጀመረች።
- ፲፰፻፹፮ ዓ.ም. - የክላሲክ ሙዚቃ ፈጣሪና አቀናባሪ የሩሲያው ዜጋ ፒተር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ በፔትሮግራድ ከተማ አረፈ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. - በአሜሪካ ፕሉቶንዬም ለመጀመሪያ ጊዜ ለቦምብ መሥሪያ ተዘጋጅቶ “ፋት ማን” በመባል የሚታወቀውን በጃፓን ናጋሳኪ ላይ የተጣለውን የአቶም ቦምብ ተሠራበት።
- ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - የግብጽ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናሰር በወቅቱ በብሪታንያ እና በፈረንሳይ ቁጥጥር ስር የነበረውን የሱዌዝ ቦይ የግብጽ ብሔራዊ ንብረት ሲያደርገው የብሪታንያና የፈረንሳይ ሰራዊቶች በቦዩ አካባቢ ግዛቶች ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ፣ ሌጎስ እና አክራ ከተማዎች አዲስ የበረራ መሥመር አስመረቀ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - “ሚቸል ኮትስ” (Mitchell Cotts) የተባለው የብሪታንያ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር በአዋሽ ሸለቆ የተንዳሆን የጥጥ እርሻ ልማት የስምምነት ውል ለመፈራረም አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - በሆላንድ እና በኢትዮጵያ ኅብረት የተቋቋመው የመተሀራ ስኳር ፋብሪካ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - አምቺትካ ደሴት ላይ የአሜሪካ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት በምድር ውስጥ “ካኒኪን” በሚል ቅጽል ስም የተሰየመውን ኃይለኛ የሃይድሮጅን ቦምብ በማፈንዳት ፈተሸ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) እና የብሪታኒያ መንግሥት በወሎ ክፍለ-ሀገር የመጋቢ መንገዶችን ማሠሪያ ላይ የሚውል የ ፰ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ውል ተፈራረሙ።
- ፲፮፻፷፩ ዓ/ም - በዕለተ እሑድ ፀሐይ ደም መስላ እንደታየችና ሁለመናዋ በጉም እና ጭለማ እንደተከበበች (በግዕዙ፦”…ወተወለጠ ኵለንታሃ በኅብረ ጢስ ዘጸሊም” ይለዋል) የዘመኑ ‘ዜና-መዋዕል’ አስፍሮታል። ይህ የፀሐይ ግርደት በከፊል እስከ እንግሊዝ አገር ድረስም እንደታየ በፈረንጆቹ ተዘግቧል።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) በወቅቱ በብሪታኒያ ሕክምና ላይ የነበሩትን ፀሐፊ-ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስን እና ወንድማቸውን አቶ መኮንን ወልደ ዮሐንስን በሦስት ቀናት እጃቸውን እንዲሰጡ አዘዘ።
- ፲፱፻፹ ዓ.ም. - የቱኒዚያው ፕሬዚደንት ሀቢብ ቡርጊባ ከሥልጣናቸው ተፈንቅለው በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በዚኔ ኤል አቢዲን ቤን አሊ ተተኩ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. - የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዊሊያም ጄፈርሰን ክሊንተን ባለቤት፣ ሂላሪ ሮዳም ክሊንተን ለአሜሪካ ሴኔት አባልነት በኒው ዮርክ ግዛት ተመረጡ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. - በአሜሪካ ሰሜን ምዕራብ የሚገኘውና ስሙ ከስፓኝኛ ቋንቋ ሞንታኛ (ተራራ) የመጣው ሞንታና የተባለው ክልል የአሜሪካ ሕብረትን በመቀላቀል አርባ አንደኛው ክፍለ ግዛት ሆነ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. - በጀርመን ከተማ በሚዩኒክ የቢራ አዳራሽ ውስጥ የወደፊቱ መሪና የናዚ ቡድን ሊቀ መንበር አዶልፍ ሂትለር ውጤቱ ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አንቀሳቀሰ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - በአሜሪካ የፕሬዚደንታዊ ውድድር በጊዜው ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩትን ሪቻርድ ኒክሰንን በማሸነፍ ጆን ፊትዝጄራልድ ኬኔዲ የአገሪቱ ሠላሳ አምስተኛው ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአድአን አካባቢ በዘመናዊ ግብርና ለማልማት የሚያስችል፣ በ፵ ዓመት የሚከፈል የሦስት ተሩብ ሚሊዮን ብር (E$3.25 million) ብድር ውል ከአሜሪካ መንግሥት ጋር ተፈራረመ።
- ፲፰፻፵፰ ዓ/ም - የሸዋ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም አርፈው በደብረ በግዕ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - የጀርመን ቄሳር ዳግማዊ ዊልሄልም ከዙፋናቸው እንደሚወርዱ በይፋ አሰታወቁ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - በጀርመን እና በአውስትሪያ አገሮች ናዚዎች የይሁዳውያን መቅደሳትና መደብሮችን በዝብዘው በእሳት አጋዩ። ይሄም ታሪካዊ ምዕራፍ “Kristallnacht” የመስተዋት መስበሪያ ምሽት በመባል ይታወቃል።
- ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ግዛቶችና በካናዳ ለአሥራ ሦስት ሰዐት ተኩል ያህል ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ስምንት መቶ ሺህ ሰዎች በኒው ዮርክ ውስጠ መሬት ባቡር ላይ ተደንቅረው አመሹ። ችግሩ በግምት የሃያ አምስት ሚሊዮን ሕዝቦችን ኑሮ አዛብቷል።
- ፲፱፻፷፫ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአገራቸውን አርበኞች የመሩ እና ታዋቂው የፖለቲካ ሰው፣ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሻርል ደጎል በተወለዱ በ ሰባ ዘጠኝ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. - በኮሙኒስታዊ የምሥራቅ ጀርመን ሪፑብሊክ የበርሊን ግንብ ፈረሰ። አገሪቷም ዙሪያ ድንበሮቿን በመክፈት ሕዝቦቿ ወደምዕራብ በነፃ እንዲጓዙ አመቻቸች።
- ፲፰፻፷፩ ዓ/ም - በዓለም የመጀመሪያው የመንገድ ተሽከርካሪዎች መቆጣጠሪያ መብራት በእንግሊዝ ዋና ከተማ በለንደን ላይ የፓርላማ ሕንጻ (የዌስትሚንስተር ቤተ መንግሥት) ‘Palace of Westminster’ ፊት ለፊት ተተክሎ አገልግሎት ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በብሪታንያ በንጉሡ የፍቅረኛቸውን ምርጫ ምክንያት በተከሰተው ቀውስ፥ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ሥልጣናቸውንና ዘውዳቸውን መልቀቅ የሚያስችላቸውን ህግና ስምምነት ፈረሙ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ላይ በተካሄደ ሥነ ሥርዐት ላይ ጥቁር አሜሪካዊው የሰብአዊ መብት ዋና ተሟጋችና ሰማዕት ማርቲን ሉተር ኪንግ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - የብሪታንያው ቢ.ቢ.ሲ. በአሜሪካ አሥራ አምሥት ግዛቶች ውስጥ ‘ሰዶማውያን’ን የሚያጠቃ ያልታወቀ አዲስ በሽታ እንደገባ እና በእነኚሁ ግዛቶች ውስጥ ሰባ አምሥት ሰዎች፥ በእንግሊዝ አገር ደግሞ አንድ ሰው በዚሁ በሽታ መሞታቸውን ዘገበ። ይሄ በሽታ በኋላ ኤይድስ የተባለው በሽታ ሲሆን ሠላሣ ዓመታት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስት በዓለም ላይ ወደ ሃያ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት ወስዷል።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - የደቡብ አፍሪቃዊው ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም -በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ግዛት ውስጥ በአርሜኒያ ክልል ውስጥ በተከሰተው የምድር እንቅጥቅጥ አርባ አምሥት ሺህ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ መኖሪያ ቤታቸውን አጥተዋል። ስፒታክ የምትባል የሃያ አምሥት ሺህ ነዋሪዎች ከተማ በዚሁ እንቅጥቅጥ ፈጽማ ወድማለች።
- ፲፱፻፹፯ ዓ/ም -የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ይስሐቅ ራቢን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ሥምዖን ፔሬዝ በጋራ የተሰጡትን የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀበሉ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የሩሲያው ተወላጅና የሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ሶልዤኒትሲን በዛሬው ዕለት በኪስሎቮድስክ ተወለደ። ሶልዤኒትሲን በስታሊን ዘመን አድሀሪ በመባል ተወንጅሎ በሳይቤሪያ ግዛት ውስጥ በእሥራትና በግዞት በነበረበት ወቅት የጻፈው “የጉላግ አርቺፒላጎ” በተባለው ድርሰቱ በዓለም ታዋቂነትን ያተረፈ ጸሐፊ ነበር።
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ መንግሥት ኢትዮጵያ አገራችንን በግፍ ከወረረች በኋላ የተሰነዘረባትን ነቀፋ እና የንግድ እገዳ ምክንያት በማድረግ ከየዓለም መንግሥታት ማኅበር አባልነት ወጣች።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ሕጻናት ዕርዳታ ድርጅት (UNICEF] ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ታዋቂው የአብዮት መሪ ቼ ጉቬራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጉባዔ ላይ ንግግር ሲያደርግ ያልታወቀ ሽብርተኛ ከውጭ በሕንጻው ላይ የሞርታር ጥይት ተኮሰ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት የፔሩውን ተወላጅ ሃቪዬር ፔሬዝ ደ ኩዌያርን የድርጅቱ አምስተኛ ዋና ጸሐፊ እንዲሆኑ መረጣቸው።
- ይቺ ዕለት በኢትዮጵያ ታሪክ ሁነኛ ስፍራ አላት። ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክና የጦሩ ፊታውራሪ፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ያረፉበት ዕለት ናት። ዕለቱ ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ሁለቱ ያረፉት በተለያዩ ዓመታት ነው። ‹‹አባ ዳኘው›› የተባሉት፣ ዳግማዊ ምኒልክ ፳ኛው ምዕት ዓመት በባተ በስድስተኛው ዓመት ላይ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. ሲያርፉ ‹‹አባ መላ›› የተሰኙት ፊታወራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ደግሞ በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈዋል። ዓመታቱ ይለያዩ እንጂ ሁለቱም ያረፉት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር።
- ፲፰፻፲ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የዘመነ መሣፍንት ሲጀመር ከዙፋናቸው ወርደው አክሱም በስደት ላይ የነበሩት እና “ተፍጻሜተ ነገሥት” የሚባል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ቀዳማዊ ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ አረፉ።
- ፲፱፻፬ ዓ/ም - የቀድሞዋ የሕንድ ርዕሰ ከተማ ካልከታ በአዲሷ ደልሂ ተተካች። በዚሁ ዕለት የብሪታንያ ንጉሥ ጆርጅ አምሥተኛ (የዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ አያት) እና ንግሥታቸው የ ሕንድ ንጉሠ ነገሥት እና እቴጌ የሚል ማእረግ ተጨመረላቸው።
- ፲፱፻፮ ዓ/ም - መጀመሪያ የሸዋ ንጉሥ በኋላም የዘመናዪቱ ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፤ በአድዋ ጦርነት የኢጣሊያን ሠራዊቶች ድል የመቱት ታላቁ መሪ፤ “ዕምዬ ምኒልክ” ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ባደረባቸው ህመም በዛሬው ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፲፱ ዓ/ም - በዳግማዊ ምኒልክ፣ በልጅ ኢያሱ እና በንግሥት ዘውዲቱ ዘመናት የጦር ምኒስትር የነበሩት ፊታውራሪ ሁብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ የሚወዷቸው ዕምዬ ምኒልክ ባረፉበት ዕለት ሞቱ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተጠነሰሰው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተጀመረ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ በእሥራት ላይ ከነበሩት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር እቢሯቸው ተገናኝተው የተጠላውን የጭቆና ሥርዐት (አፓርታይድ)ን የሚወድምበትን ሁኔታ ተመካከሩ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት አባላት የጋናውን ተወላጅ ኮፊ አናንድን ሰባተኛው የድርጅቱ ዋና ጸሐፊነት መረጧቸው።
- ፲፱፻፺፮ ዓ/ም - የቀድሞው የኢራክ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን ከሥልጣናቸው ሸሽተው ከተደበቁ በኋላ በአሜሪካ ሠራዊቶች በተወለዱበት ቲክሪት ከተማ አካባቢ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤቱ በኒው ዮርክ ከተማ እንዲሆን ወሰነ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተሰነጸጸው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ዓላማውን ይፋ አደረገ። አብሮም የለውጥ ፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውንና አልጋ ወራሹን አስፋ ወሰንን (“አስገድደው”) በማስማማትም መንግሥት በቆረጠላቸው ደመወዝ እየተዳደሩ ለሕገ መንግሥት የሚገዙ ንጉሥ ሆነው እንደሚያገለግሉ እራሳቸው ለሕዝቡ በራዲዮ እንዲያስተላልፉ አደረጉ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም -ታንዛንያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - ዲክ ታይገር (ሪቻርድ ኢሄቱ) የሚባለው ናይጄሪያዊ ቦክሰኛ በተወለደ በ ፵፪ ዓመቱ በጉበት ነቀርሳ ምክንያት አረፈ። ዲክ ታይገር የባያፍራን የመገንጠል ሙከራ ደጋፊ ነው በሚል ወደአገሩ እንዳይመለስ ተከልክሎ በስደት አሜሪካ ይኖር ነበር።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - የደቡብ ኮርያው ተወላጅ፣ ባን ኪ ሙን ስምንተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሆኑ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተጠነሰሰው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥትን የሚቃረነው የነጄነራል መርድ መንገሻ ኃይል ዝግጅቱን ጨርሶ በዚያው ዕለት ከቀትር በኋላ በዓየር እና በታንክ ጭምር የተፋፋመ ውጊያ ሲጀምር መንግሥቱ ንዋይ መምሪያ ክፍላቸውን ወደ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት አዛወሩ።
- ፲፰፻፪ ዓ/ም የፈረንሲስ ንጉሠ ነገሥት ናፖሌዎን ቦናፓርት ከሚስቱ ከንግሥት ጆሴፊን ጋር ተፋታ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተሰነጸጸው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ኃይል እየተዳከመ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎቻቸው እያደር እየጎለመሱ መሄዳቸውን የተገነዘቡት ሽብርተኞች በቁጥጥራቸው ላይ የነበሩትን ሃያ መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ሚኒስትሮችንና መኮንኖችን ወደ አረንጓዴ ሳሎን ያዛውሩና አልጋወራሹንና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለብቻቸው እንዲጠበቁ ያደርጋሉ። ጄነራል ጽጌ ዲቡ ወዲያው ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰ ጥይት ሲገደሉ፣ እነ ጄነራል መንግሥቱ የያዟቸውን እስረኞት ረሽነው ለማምለጥ ወስነው ሜጄር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፤ ራስስዩም መንገሻ፤ ራስ አበበ አረጋይ፤ አቶ መኮንን ሀብተወልድ፤ አባ ሐና ጅማ፤ በጠቅላላው አሥራ አምስት ሰዎች ተረሽነው ሞቱ። የክብር ዘበኛ መኮንን የነበሩት ሻምበል ደረጀ ኃይለ ማርያም ሽብርተኞቹን በመቃወም የቤተ መንግሥቱን አጥር በታንክ ደምስሰው ሲገቡ ከሽብርተኞት ወገን በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ። ሻምበል ደረጀ የስመ ጥሩው አርበኛ የኃይለ ማርያም ማሞ ልጅ እና የንጉሠ ነገሥቱ የልጅ ልጅ የልዕልት ሶፊያ ደስታ ባል ነበሩ።
- ፳፻፫ ዓ/ም የኢትዮጵያና የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድኖች እግር ኳስ ተጫዋችና አሰልጣኝ የነበረው በኩሩና ኮከቡ መንግሥቱ ወርቁ፣ በ፸ ዓመቱ አረፈ። መንግሥቱ ወርቁ በስድስት የአፍሪካ ዋንጫዎች የፍጻሜ ግጥሚያዎች የተሳተፈ ሲሆን፣ በ፫ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ግብፅን ፬ ለ ፪ አሸንፋ ዋንጫ እንድታገኝ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረና በዚሁ በ፫ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ፫ ግብ በማስቆጠሩም የኮከብ ግብ አግቢነት ክብር አግኝቷል፡፡
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተሰነጸጸው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ኃይል ተደምስሶ ንጉሠ ነገሥቱ ከብራዚል ተመልሰው በአስመራ በኩል አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፹፰ ጋናዊው ኮፊ አናንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሆኑ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - ንጉሠ ነገሥቱ ገነተ ልዑል ይባል የነበረውን ቤተ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ማእከል እኒዲሆን ሰጥተው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መርቀው ከፈቱ።
- ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - አንድ ነጥብ ስምንት ኪሎ-ግራም የሚመዝነው የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር የዡልስ ሪሜ የወርቅ ዋንጫ ከብራዚል የእግር ኳስ ጥምረት ዋና መሥሪያ ቤት
ተሰረቀ። ታኅሣሥ ፲
- ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - የሀገር ፍቅር አዳራሽ የንጉሠ ነገሥቱን የአሜሪካ የመጀመሪያ ጉብኝት የፎቶ አውደ-ትርዒት ለማቅረብ በተወጠነ ዓላማ መሠረት በዚህ ዕለት ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፷፮ ዓ/ም "ኢትዮጵያ ትቅደም" የሚለውን መፈክር የነደፈውና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም፣ ከሥልጣን ያወረዳቸው ወታደራዊ ደርግ፣ ፷ዎቹን ከፍተኛ ሹማምንት ከገደለ ከአንድ ወር በኋላ፣ "የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብአዊነት"ን (የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም) በይፋ ያወጀበት ዕለት ነው፡፡
- ፲፰፻፲ ዓ/ም - በዘመነ መሳፍንት ፮ ጊዜ ከንጉሥነት ሥልጣናቸው የተሻሩት እና የነገሡት ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ በዚህ ዕለት በትግሬው መሥፍን በራስ ወልደ ሥላሴ ዘመን አርፈው፣ አክሱም ጨለቆት ሥላሴ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የጎጃሙ ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት አማቻቸው የነበሩትን ደጃዝማች አበራ ካሣን እና ወንድማቸውን ደጃዝማች አስፋ ወሰን ካሣን ‘አይዟችሁ አትነኩም’ ብለው አታለው ካስገቡ በኋላ አሳልፈው ለፋሺስት ኢጣልያ ኃይሎች አስረከቧቸው። የጣልያኖቹም ጄኔራል ትራኪያ ወንድማማቾቹን ፍቼ ላይ በዚህ ዕለት አስረሽኖ አንገታቸውን አስቆርጦ ገደላቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ የሱዳን ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት፤ የላይቤሪያ ምክትል ፕሬዚደንት እና የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ስለኢየሩሳሌም ከሮማው ጳጳስ እና ከኢጣልያ ፕሬዚደንት ሊዮኔ ጋር የሦስት ቀን ውይይት ለማካሄድ ሮማ ገቡ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት "የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብአዊነት"ን (የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም) በይፋ ካወጀ በኋላ፣ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው "ብሔራዊ የዕድገት በኅብረት የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ" የተሰኘ ፷ ሺ የሁለተኛ ደረጃ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን በመላ አገሪቱ አሰማራ። የጊዘውም መፈክር ፣"በዕድገት በኅብረት - እንዝመት፣ ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት" የሚል ነበር
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የጃንሆይ አጎት ደጃች ወልደ ሥላሴ ለመንግሥት ሥራ ደሴ ደርሰው ሲመለሱ አደጋ ተፈጥሮ ቀበቶ ሳያስሩ ቆመው ሲፎክሩ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ራሳቸውን በኃይል ስለመታቸው ከተሳፋሪዎቹ መካከል እሳቸው ብቻ በአደጋው ሞቱ። ስለኾነም በአይሮፕላን አደጋ በመሞት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እኒሁ የራስ መኮንን ወንድም ደጃች ወልደ ሥላሴ መሆናቸው ነው።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በሁለት የአስመራ ቡና ቤቶች ላይ በተወረወሩ ተወርዋሪ ፈንጂዎች በተከሰተው አደጋ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ በተያያዘ የኤርትራ ነፃነት ግንባር አሰብ ወደብ አካባቢ የሰነዘረው ጥቃት ሦስት የጭነት መኪናዎችን አውድሟል።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በ፲፱፻፳፪ ዓ/ም የተደነገገውን ‘የኢትዮጵያ ዜግነት’ ሕግ በመሻር የሚተካው፤ ስለኢትዮጵያ ዜግነት የወጣው አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፰/፲፱፻፺፮ ከዚህ ዕለት ጀምሮ ሕግ ሆኖ እንደሚጸና በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታወጀ።
- ፲፱፻፺፮ ዓ/ም ባም በምትባለው የደቡባዊ ፋርስ ከተማ አካባቢ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው ጉዳት የ፳፮ሺ ፪መቶ ፸፩ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ ወደ ፴ሺ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የጃፓን አልጋወራሽ (አሁን ንጉሠ ነገሥት) አኪሂቶ እና ባለቤታቸው ልዕልት (አሁን እቴጌ) ሚቺኮ በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ጉብኝታቸውን በዛሬው ዕለት ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኒካራጓ ርዕሰ ከተማ ማናጓ ላይ በደረሰው የመሬት እንቅጥቅጥ አደጋ ከ ፲ሺህ በላይ የሰው ሕይወት አለቀ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የብሔራዊ ዓመት በዓላት በአገሪቱ ታሪክ ዘገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓቢይ እስላማዊ በዓላትን እንደሚያካትቱ አውጀ።
- ፲፰፻፺፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የምድር ባቡር ኩባንያ (በኋላ የኢትዮጵያ-ፈረንሳይ የምድር ባቡር ኩባንያ) የሐዲድ ግንባታ በዚህ ዕለት አዲስ በተመሰረተችው ድሬዳዋ ከተማ ደረሰ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓብያት እስላማዊ በዓላት በመላ አገሪቱ እንዲከበሩ በተላለፈው ድንጋጌ መሠረት በዛሬው ዕለት የኢድ አል አደሀ (አረፋ) በዓል ተከበረ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፈረንሳይ መንግሥት የተለገሡትን ሄሊኮፕተር ተረከቡ።
- ፲፱፻፹ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ (ሴካፋ) ዚምባብዌን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ከፍ ያደረገችበት ነበር፡፡ ዋንጫውን ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ገብረ መድኅን ኃይሌ የሰጡት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ፕሬዚዳንት፣ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሲሆኑ፣ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ፻ ሺሕ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም ለመሥራት ቃል በመግባት ነበር፡፡
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በሕንድ ውቅያኖስ ሥር የተነሳው የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው ኃይለኛ የባሕር ሞገድ በስሪ ላንካ፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዚያ፣ ታይላንድ እና ማሌዚያ አገራት ከ፪መቶ ፴ሺ በላይ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፳፻ ዓ/ም - በኬንያ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ምዋይ ኪባኪ አሸናፊ ናቸው ተብሎ ሲታወጅ በመላ አገሪቱ የተከተለው የተቃውሞ ረብሻ በአገሪቱ ለተከሰቱት ፖለቲካዊ፤ ምጣኔ-ኃብት እና ሰብዓዊ ነውጦች ዋና መንስዔ ሆኗል።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ደርግ በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭት የወሰነውን ማሻሻያ ይፋ አደረገ። በዚህ መሠረት በራዲዮ የኦሮምኛ ሥርጭት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲወጠን በአንጻሩ የፈረንሳይኛ ሥርጭትን ሰረዘ። የእንግሊዝኛ ፕሮግራሞቹን ደግሞ በራዲዮም በቴለቪዥንም ቅነሳ እንደሚደረግ አስታወቀ።
- ፲፱፻፩ ዓ/ም - በሲሲሊ ደሴት፣ መሲና ከተማ አካባቢ የተነሣው የመሬት እንቅጥቅጥ ከ፸፭ሺህ በላይ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማኅበር ሊቀ መንበር፣ ጥላሁን ግዛው በፖሊስ ተገደለ። ይህ ድርጊት በርዶ የነበረውን የተማሪዎች አመጽ እንደገና አፋፍሞታል።
- ፳፻፩ ዓ/ም - በሶማሊያ የሥልጣን ትግል ውጊያ የአገሪቱ ጊዜያዊ ፌዴራላዊ መንግሥት ሠራዊት እና አጋሮቻቸው የኢትዮጵያ ወራሪ ኃይል የሞቃዲሹን ከተማ በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ።
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም - ልዑል አልጋ ወራሽ፣ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ኃይለ ሥላሴ እና ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ ሴት ልጅ መውለዳቸው፣ ከፓሪስ በቴሌግራም ስለተሰማ፣ ፳፩ ጊዜ የደስታ መድፍ ተተኩሶ በዓል ተደረገ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የየአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የመጀመሪያው ስብሰባውን የተ.መ.ድ ዋና ፀሐፊ ዳግ ሃመርሾልድ በተገኙበት ሥርዓት፣ በአዲስ አበባ ላይ አካሄደ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዕለት ተመሠረተ።
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የቀድሞው የሶቪዬት ኅብረት በይፋ አክትሞ ሕጋዊ መንግሥት እና ሉዐላዊነት ወደ አሥራ አምስቱ አባላት አገሮች ተላለፈ።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም - የሱዳን ሪፑብሊክ ነጻነቷን ከምስር ሪፑብሊክ እና ከታላቋ ብሪታኒያ እና የአየርላንድ ሕብረታዊ ንጉዛት ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የካሜሩን ሪፑብሊክ ነጻነቷን ከ ፈረንሳይ እና ከታላቋ ብሪታኒያ እና የአየርላንድ ሕብረታዊ ንጉዛት ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፹፭ ዓ/ም - የቀድሞዋ ቼኮዝሎቫኪያ በሰላማዊ ስምምነት ለሁለት ተከፍላ የቼክ ሪፑብሊክ እና ስሎቫኪያ በተባሉ ሉዐላዊ አገራት ተተካች። መገናኛ ብዙሀን ይሄንን ከፈላ ‘የሐር ፍች’ (Velvet Divorce) የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል።
- ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ተመሰረተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ፩ሚሊዮን ፱መቶ ሺ ኪሎ የመዳብ ሽያጭ ወደጃፓን ላከች። መዳቡ በኤርትራ ውስጥ ከሚገኘው የድባሮ ማዕድን የተቆፈረ ነው።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - ጋናዊው ዲፕሎማት ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፯ተኛው ዋና ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የአላስካ አስተዳደራዊ ክልል በዚህ ዕለት የአሜሪካ ኅብረት ፵፱ኛዋ አባል ህና ከኅብረቱ ጋር ተዋሐደች።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮሐንስ አሥራ-ሦስተኛ የኩባውን መሪ ፊደል ካስትሮን ከካቶሊክ ክርስቲያን ጉባዔ በውግዘት አስወገዱ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - የነፋስ ስልክ (Wirless) በኢትዮጵያ ተጀመረ፤ ቆመ፡፡
- ፳፻፪ ዓ/ም - በአሁኑ ጊዜ በ፰መቶ ፳፱ ነጥብ ፰ ሜትር ርዝመቱ በዓለም አንደኛው ሰማይ-ጠቀስ ሕንፃ የሆነው ቡርጅ ከሊፋ (Burj Khalifa (Arabic: برج خليفة)) ሕንፃ በዱባይ በዚህ ዕለት ተመረቀ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - የ፳ኤል መንግሥት ‘ኦፐሬሽን ሙሴ’ በሚል ሥያሜ ኢትዮጵያውያን ፈላሻዎችን ከኅዳር ፲፪ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ/ም ጀምሮ በድብቅ ወደ ፳ኤል ካጓጓዘ በኋላ የዚህ ምሥጢራዊ የአየር ውፅዓተ-ነገድ ወሬ በመሰማቱ በዛሬው ዕለት የማቆሚያ ትዕዛዝ ተላለፈ። በዚህ የስድስት ሳምንት ውፅዓት ፰ሺ ፈላሻዎች ሲሰደዱ ከ፮ ዓመት በኋላ በተደገመው ‘ኦፐሬሽን ሰሎሞን’ ደግሞ ፲፭ሺ አይሁዳዊ ኢትዮጵያውያን ወደ ፳ኤል ተሰደዋል።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድን አዲስ አበባ፣ አራዳ አካባቢ ላይ ተመሰረተ።
- ፲፰፻፸፱ ዓ/ም የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊትና የሐረሩ አሚር ዐብዱላሂ ሠራዊት በሜታ ወረዳ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ ውስጥ በምትገኘው ጨለንቆ ላይ ገጥመው ከ፴ ደቂቃ ውጊያ በኋላ የዐሚሩ ሠራዊትተሸንፎ ወደሐረር ሸሸ። ወዲያው ሐረር በሸዋው ንጉሥ እጅ ገባች።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ አረባዊ ነዳጅ አምራች አገሮች በወቅቱ የነዳጅ ምርታቸውን የፖለቲካ መሣሪያ በማድረጋቸው በአፍሪቃውያን አገሮች ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለማጥናት አዲስ አበባላይ ተሰበሰቡ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በግብጽ የታላቁ የአስዋን ግድብ ግንባታ በአገሪቱ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናስር በዚህ ዕለት ሲጀመር፣ ፕሬዚደንቱ በናይል ወንዝ የግራ-ዳርቻ ላይ የሚገኘውን ወደሃያ ቶን የሚገመት ጥቁር-ዓለት በአሥር ቶን ዲናሚት ፍንዳታ ከስክሰውታል።
ጥር ፩ ቀን
- ፲፰፻፸ ዓ/ም ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት የተመኟት እና የአድዋ ጦርነት እንዲጀመር ያዘዙት የኢጣልያ ንጉሥ ቀዳማዊ ኡምቤርቶ በዛሬው ዕለት ሲሞቱ ዳግማዊ ቪቶሪዮ ኢማኑኤል ዙፋኑን ወረሱ።
- ፲፱፻ ዓ/ም - ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ መንግሥት ዋና መላክተኛ ክሎቡኮውስኪ የንግድ እና ወዳጅነት ስምምነት አዲስ አበባ ላይ ተፈራረሙ
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም ኒው ዮርክ ከተማ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕንጻ ተመረቀ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ‘አፕል’ (Apple Computer Inc.) የተባለው የአሜሪካ የመቀምር ድርጅት ‘አይ ቲዩንስ’ (iTunes) የተባለውን የሙዚቃ ተሰኪ ስብስብ አካል (software) ሳን ፍራንሲስኮ ላይ አስተዋወቀ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም ‘አፕል’ (Apple Computer Inc.) “አይ ፎን” (iPhone) የተባለውን ተንቀሳቃሽ ስልክ አስተዋወቀ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኘውን ሕዝብ ለመርዳትና ለማስተማር፣ የመጀመሪያዎቹ "የእድገት በኅብረት የእውቀትና የሥራ ዘመቻ" ወጣቶች ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ዘመቱ።
- ፲፰፻፺፫ ዓ/ም - የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አርፈው በደብረ ማርቆስ ተቀበሩ።
ጥር ፬ ቀን፦
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በዛንዚባር ደሴት በጊዜው በሱልጣን ይመራ የነበረውን አረባዊ መንግሥት በጆን አኬሎ የሚመራ ሽብርተኛ ቡድን ፈንቅሎ የዛንዚባር ሪፑብሊክን መሠረተ።
- ፲፰፻፹፰ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የባቡር ኩባንያ የሀዲድ ሥራውን ውል ተፈራረመ።
ጥር ፮ ቀን
- ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ (የቀድሞው እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ) በካይሮ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ከእስክንድርያው ፓትርያርክ መዓርገ ጵጵስና ተቀብለው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኾነው ተቀቡ። ነገር ግን የፓትርያርክነቱን ማዕረግ የእስክንድርያው ፓትርያርክ ከሞቱ በኋላ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ነው የተሰጡት።
ጥር ፯ ቀን
- ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ በአዲስ አበባ አዲስ የተሠራውን የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴን ቤተ ክርስቲያን መርቀው፣ በአምስቱ ዓመት የፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ሰማዕት የኾኑ አርበኞችን ዐፅም አገቡ።
ጥር ፰ ቀን፣
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - በኦክላሆማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ((እንግሊዝኛ) Oklahoma State University) እርዳታ የተመሠረተው የዓለማያ እርሻ ኮሌጅ (ያሁኑ ሐሮማያ ግብርና ዩኒቨርሲቲ) ተመርቆ ተከፈተ፡፡
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኮንጎ የእርስ በእርስ መፈጃጀት በተፋፋመበት ወቅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ዳግ ሀመርሾልድ የኢትዮጵያን የሠራዊት ዕርዳታ ለማረጋገጥ ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ምጽዋ ላይ ተገናኙ።
ጥር ፱ ቀን
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዦርዥ ፖምፒዱ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ግብዣ ኢትዮጵያን ለሦስት ቀናት ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አልጋ ወራሽ የነበሩት መርድ አዝማች አስፋ ወሰን ኃይለ ሥላሴ በተወለዱ በ፹፩ ዓመታቸው በዩናይትድ ስቴትስ አረፉ። አልጋ ወራሹ የአንድ ወንድ እና የሦስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ። የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት አዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ጥር ፲ ቀን፣
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች በዚህ፣ የትልቁ የጥምቀት በዓል ሥነ ሥርዓት መጀመሪያ ዕለት የአጥቢያቸውን ታቦተ ሕግ በማጀብ ወደከተራው ተጉዘው እዚያው ያድራሉ።
- ፲፱፻፹፭ ዓ/ም በ አምሳዎቹም የአሜሪካ ሕብረት ግዛቶች አሁን በየዓመቱ በልደቱ አካባቢ የሚከበረው የጥቁር አሜሪካዊው መሪ የማርቲን ሉተር ኪንግ ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም እስከ ፭ መቶ ፳፭ መንገዶኞችን የሚያስተናግደው፣ ወደረ ቢሱ ኤየርባስ ኤ፫፻፹ (Airbus A380) የተሰኘው አየር ዠበብ በቱሉስ የፈረንሳይ ከተማ ለዓለም ተገለጸ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም በምዕራብ አውሮፓ አገሮች የተነሳ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ፣ በብሪታኒያ አሥራ አራት፤ በአለማኝ አሥራ ሦስት ሰዎችን ሲገል በሀያ አገራት ውስጥ አርባ አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ጥር ፲፩ ቀን፣
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በመጥምቁ ዮሐንስእጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ የጥምቀት በዓል ነው።
- ፲፱፻፶፰ ዓ/ም ኢንዲራ ጋንዲ በሕንድየመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ። አባታቸው ጃዋህራል ኔህሩ የአገሪቱ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ።
ጥር ፲፪ ቀን፣
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም የፋሺስት ኢጣልያ የጦር ዓለቃ ማርሻል ግራትዚያኒ በራሡ መሪነት የራስ ደስታ ዳምጠውን ሠራዊት በሲዳሞ እና የደጃዝማች ገብረ ማርያምን ሠራዊት በ ባሌ ለመውጋት ዘመተ።
ጥር ፲፫ ቀን፣
- ፲፰፻፷፬ ዓ.ም.፣ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ (አባ በዝብዝ) በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስመ መንግሥታቸው "ዮሐንስ ራብዓዊ" (ዮሐንስ ፬ኛ) ተብሎ፣ በጳጳሱ በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እጅ ተቀብተው በሥርዓተ መንግሥት ንጉሠ ጽዮን፣ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ። በታሪክ እንደተመዘገበው በዚሁ ንግሥ ምክንያት ሦስት ቀን በዓል ሆኖ፣ ለግብር ፬ ሺህ ሰንጋ ታርዶ፣ ፶ ጉንዶ ማር የፈጀ፣ ፻፶ ሺህ ገንቦ ጠጅ ቀርቦ፣ በደስታ ሲበላ ሲጠጣ ሰንብቷል።
- ፲፱፻፴፫ ዓ/ም የፋሺስት ኢጣሊያን ሠራዊት ጠራርጎ ለማስወጣት የተቀጣጠለውን ዘመቻ ከፍጻሜ ለማድረስ ከሱዳን ድንበር ወደ ኢትዮጵያ የዘለቁት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ አርበኞችና የእንግሊዝ ጦር፣ በኦሜድላ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የሆነውንና የይሁዳ አንበሳ ከመሐሉ የሚገኝበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ተከሉ፤ አውለበለቡ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ሕዝብ የውሃ አገልግሎት የሚሰጠው የገፈርሳ ግድብ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመረቀ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪቃ እግር ኳስ ውድድር የግብፅን ቡድን አራት ለ ሁለት አሸንፋ ዋንጫውን ተሸለመች። ለኢትዮጵያ ቀዳሚውን ግብ ያስቆጠረው የቴሌው ግርማ ዘለቀ ሲኾን፣ የጊዮርጊሱ መንግሥቱ ወርቁ በ፹፬ኛውና በ፻፲፯ኛው ደቂቃ ሁለተኛና አራተኛውን፣ ኢታሎ ቫሳሎ በ፻፩ኛው ደቂቃ ሦስተኛውን ለማስገባት ችለዋል። ያልተደገመውንና ሕዝቡም እየናፈቀ ያለው የአፍሪቃ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ያስገኙት ፩. ጊላ ሚካኤል ተስፋ ማርያም ፪. ክፍሎም አርአያ ፫. አስመላሽ በርሔ ፬. በርሔ ጎይቶም ፭. አዋድ መሐመድ ፮. ተስፋዬ ገብረ መድኅን ፯. ግርማ ዘለቀ/ተክሌ ኪዳኔ ፰. መንግሥቱ ወርቁ ፱. ሉቻኖ ቫሳሎ (አምበል) ፲. ኢታሎ ቫሳሎ ፲፩. ጌታቸው ወልዴ ሲሆኑ ተጠባባቂዎች ደግሞ ጌታቸው መኩሪያ፣ እስማኤል ጊሪሌ፣ ብርሃኔ አስፋው፣ ኃይሌ ተስፋ ጋብር፣ ነፀረ ወልደሥላሴ ነበሩ። አሰልጣኞች ይድነቃቸው ተሰማ፣ ፀሐየ ባሕረና አዳሙ ዓለሙ፣ ወጌሻው ጥላሁን እሸቴ ነበሩ፡፡
ጥር ፲፬ ቀን፣
- ፲፰፻፲፮ ዓ/ም - በቀድሞዋ 'ጎልድ ኮስት' (አሁን ጋና) የአሻንቲ ብሔረሰብ ሠራዊት የእንግሊዝን ሠራዊት በውጊያ አሸንፈው በአፍሪቃአኅጉር፣ የነጭ ቅኝ ገዥ ሠራዊትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ብሔረሰብ ሆኑ።።
- ፲፰፻፸፩ ዓ/ም - በዛሬዪቷ ደቡብ አፍሪካ በእንግሊዝ ሠራዊት እና በዙሉ ብሔረሰብ መኻል በተካሄደው የ'ኢሳንድልዋና'(Battle of Isandlwana) ውጊያ ዙሉዎች አሸናፊ ሆኑ።
- ፲፰፻፺፫ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ እና አየርላንድ ንጉዛት ዙፋን ላይ ለ፷፬ ዓመታት የነገሡት ንግሥት ቪክቶርያ በተወለዱ በ ፹፪ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም የቦይንግ 'ጃምቦ ጄት' በመባል የሚታወቀው ቢ ፯፻፵፯ (Boeing 747) አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞችን ጭኖ ከኒው ዮርክ ኬኔዲ አየር ጣቢያ ተነስቶ ሎንዶን ሂዝሮው አየር ጣቢያ አረፈ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም በአገር ውስጥ በረራ ከባህር ዳር ወደ ጎንደር በመብረር ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ DC-3 አየር ዠበብ በአራት የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት ተጠልፎ ሊቢያ ውስጥ ቤንጋዚ ከተማ አረፈ።
ጥር ፲፭ ቀን፣
- ፲፭፻፵፬ ዓ/ም - በታሪክ ዘገባ በብዛት የሰው ነፍስ የጠፋበት ታላቁ የ'ሻንግዚ' የመሬት እንቅጥቅጥ በቻይና ሲከሰት እስከ ፷ መቶ ፴ ሺህ ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የአዋሽ ፩ኛ እና ፪ኛ ግድቦች የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጫ ሥነ ሥርዓት ላይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መርቀው መሠረቱን ተከሉ።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ክልል ፤ በአሁኑ ታጂኪስታን ውስጥ የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ ፪፸፬ ሰዎች ገደለ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጃፓን ሠራዊት ውስጥ ተሰልፎ የነበረው ፶ ዓለቃ ሾዪቺ ዮኮይ ጦርነቱ ባከተመ በ ሃያ ሰባት ዓመቱ ተደብቆ በኖረበት በጉዋም ጫካ ውስጥ ተገኝቶ ወደአገሩ ሲመለስ «በሕይወቴ ስመለስ ትልቅ እፍረት እየተሰማኝ ነው።» ብሎ ተናገረ። ሾዪቺ ከተመለሰ በኋላ ለሃያ አምስት ዓመታት ኖሯል።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚዎችንና የፋሺስትን ሥርዓት በመጻረር ዝና ያተረፉት ታላቅ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ወታደር፤ የታሪክ እና የሥነ ጽሑፍ ምሁር እንዲሁም በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ተቀባይ የነበሩት ዊንስተን ቸርቺል በተወለዱ በዘጠና አንድ ዓመታቸው አረፉ ።
- ፲፭፻፷፯ ዓ/ም - የቡርቱጋል መርከበኛ ፓውሎ ዲያስ ደ ኖቬሽ የአንጎላን ዋና ከተማ ሉዋንዳ ቆረቆረ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - አንደኛው የዓለም ጦርነት ከተገባደደ በኋላ የዓለም መንግሥታት ማኅበር (The League of Nations) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የቀድሞው የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ በሲንጋፖር ላይ በሚካሄደው የጋራ ሀብት አገሮች ጉባዔ ላይ እንዳሉ በጄኔራል ኢዲ አሚን በተመራ ወታደራው መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።
- ፳፻፪ ዓ/ም - ከቤይሩት ከተማ ፹፪ መንገደኞችንና ፰ አብራሪዎችና አስተናጋጆችን ጭኖ ወአዲስ አበባ እያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ ፯፻፴፯ አየር ዠበብ፣ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ባልታወቀ ምክንያት ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ወድቆ ሲሰምጥ ፺ዎቹም ተሳፋሪዎች በሙሉ ተፈጅተዋል። ከነዚህ መኀል ፴፩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።
ጥር ፲፰ ቀን
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ዳግማዊት ንግሥት ኤልሣቤጥ የ'ፊልድ ማርሻል' (Field Marshal) ማዕርግ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሰጡ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ሌሊቱን በደም ቋጠሮ ምት ታመው በአስቸኳይ ወደእንግሊዝ አገር የእንግሊዝ የጦር አየር ዠበብ ለሕክምና እንዲወስዳቸው ተለመነ። የጦር አየር ዠበብ በማግሥቱ ይዟቸው ወደሎንዶን በረረ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ጉጅራት በሚባለው የሕንድ ግዛት የተከሰተው ዐቢይ የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፳ሺህ ሰዎችን ሕይወታቸውን አጥፍቷል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን በአስቸኳይ ለሕክምና በእንግሊዝ የጦር አየር ዠበብ ተሳፍረው ወደሎንዶን በረሩ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (የአሁኗ ዚምባብዌ) የነጻነት ትግል መሪ ሮበርት ሙጋቤ ከአምስት ዓመት ስደት በኋላ አገራቸው ተመልሰው ሲገቡ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
- ፲፱፻፹፰ ዓ/ም - በኒጄር ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዚደንት ማማን ኡስማን፣ በኮሎኔል ኢብራሂም ባሬ ማኢናሳራ የተመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን አወረዳቸው።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - ሕንዳዊው የሰላማዊ እንቅስቃሴ መሪ ማሀትማ ጋንዲ (Mohandas Karamchand Gandhi} በነፍሰ ገዳይ እጅ ተገደሉ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - ቻሌንጀር የተባለችው የአሜሪካ የጠረፍ መንኮራኲር ሰባት ጠፈረኞችን ጭኖ እንደተተኮሰ አየር ላይ ፈንድቶ ሲከሰከስ ሰባቱም አሜሪካውያን ሞተዋል።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም የኬንያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬ መቶ ፴፩ አይቮሪ ኮስት ጠረፍ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ሲወድቅ ፻፷፱ ሰዎች ሞቱ።
- ፲፰፻፶፫ ዓ/ም - ካንሳስ የአሜሪካ ኅብረት ፴፬ ኛዋ አባል ሆነች።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርቺል ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩ በስድስተኛው ቀን ዛሬ የቀብር ሥርዓታቸው ተፈጽሟል።
- ፲፮፻፸ ዓ/ም - በካቶሊኩ የኢትዮጵያ ንጉሥ ሱሰንዮስ ዘመን መንግሥት፣ በትግራይ የካቶሊክ ሚሲዮንን በማስፋፋት ላይ ተሰማርቶ የነበረው የኢየሱሳዊ ሚሲዮን አባል እና የቡርቱጋል ተወላጁ ጀሮኒሞ ሎቦ አረፈ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - ኮለምቢያ የተሰኘችው የአሜሪካ የጠፈር መንኲራኩር ከተልዕኮዋ ተመልሳ የምድር የአየር ክልል ውስጥ ስትገባ በደረሰባት የፍጻሜ አደጋ ሰባቱም አብራሪዎቿ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፰፻፺፫ ዓ/ም ከረጅም ዘመናት የብሪታንያ ንግሥትነትና የሕንደኬ ንግሥተ ነገሥትነት በኋላ ያረፉት ቪክቶሪያ በዚህ ዕለት ተቀበሩ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም የአፓርታይዳዊዋ ደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ ለሠላሳ ዓመታት በሕግ ተከልክሎ የነበረውን የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቡድን (African National Congress) ሕጋዊ መሆኑንና በወቅቱ በእሥራት ላይ የነበሩትን ኔልሰን ማንዴላ እንደሚፈቱ አስታወቁ።
- ፲፰፻፹፰ ዓ/ም - ወረሂመኑ ተንታ ላይ ልጅ ኢያሱ ከአባታቸው ከራስ ሚካኤል (በኋላ ንጉሥ) እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሸዋረጋ ምኒልክ (የዳግማዊ ምኒልክ ልጅ) ተወለዱ።
ጥር ፳፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፵፮ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፴፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፲፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ ተመረቀ። በሕንፃው መግቢያ ላይ የተለጠፈው ሰሌዳ እንዲህ ይላል፤
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመናገሻው ከተማ ለአዲስ አበባ ሕዝባቸው፣ ለማኅበራዊ ኑሮው፣ ለኤኮኖሜውና ለባህሉ ዕድገት አማካይ የአገልግሎት ቤት ይሆን ዘንድ ፈቅደው ያሠሩትን ይህን ሕንፃ፣ በሠላሳ አራተኛው ዘመነ መንግሥታቸው መርቀው ከፈቱ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክ በአዲስ አበባ ኤምባሲ ከፈተች።
- ፲፯፻፷፯ ዓ/ም - የሸዋው መስፍን መርዕድ አዝማች አምኃ ኢየሱስ፣ ሐር-አምባን እንደ እልፍኝ፤ አንኮበርን እንድ አዳራሽ አድርገው ለ፴፬ ዓመታት ከገዙ በኋላ አርፈው እሳቸው ባሠሩት የአንኮበር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ልጃቸው መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ተተክተው የሸዋ መስፍን ሆኑ።
- ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ካይሚ የተባለ የጣልያን የባህር ኃይል መኮንን ምጽዋ ወደብን ይዞ የአገሩን ሰንደቅ ዓላማ ካውለበለበ በኋላ፣ የግብጽ እና የብሪታኒያ መንግሥቶች ወደቡን እንድይዘው ፈቅደውልኛል ብሎ አወጀ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ዝነኛው የሬጌ ሙዚቀኛ ሮበርት ኔስታ ማርሊ ተወለደ።
- ፲፰፻፴፬ ዓ/ም - በዘመነ መሣፍንት፣ የራስ አሊ አሉላ ሠራዊት ደብረ ታቦር ላይ ከሰሜኑ ገዥ ደጃዝማች ውቤ ኃይለ ማርያም ሠራዊት ጋር በጦርነት ገጥሞ ድሉ የራስ አሊ ሆነ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - በፍልውሃ አቅራቢያ በዘመናዊ ዕቅድ አዲስ የተሠራው ኢዮቤልዩ (የአሁኑ ብሔራዊ) ቤተ መንግሥት ተመረቀ
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የአፍሪቃ ኢኮኖሚ ኮሚሲዮን ዋና መሥሪያ ቤትና በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረገው ልዩ ልዩ የአፍሪቃ መንግሥታት ጉባኤዎች መሰብሰቢያ፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት የተሠራውን የአፍሪካ አዳራሽ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፸፭ ዓ/ም - ለባንኮች የስፖርት ክለብ የእግር ኳስ ቡድን እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በመሀል ሜዳ መደብ የሚጫወተው ተሾመ አዳሙ ጌጡ በዚህ ዕለት ተወለደ። ተሾመ ወደ ባንኮች ከመዛወሩ በፊት ለመብራት ኃይል የእግር ኳስ ክለብ ይጫወት ነበር።
የካቲት
ለማስተካከልየካቲት ፩ ቀን
- ፫፻፹፮ ዓ/ም - በክርስትና ሃይማኖት የተከሰቱትን ተቃራኒ ትምህርቶች በጉባኤ ለመወሰን የቁስጥንጥንያው ንጉሥ ቀዳማዊ ቴዎዶስዮስ ባስተላለፈው ጥሪ መሠርተ ፩፻፶ ሊቃውንት፣ ኤጲስ ቆጶሳት በቁስጥንጥንያ ጉባኤ ተሳትፈው መቅዶንዮስን፤ አፖሊናሪዮስን እና ሌሎችን መናፍቃንን አወገዙ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ እና ሰሜን አየርላንድ ንጉዛት ልዕልት ኤልሳቤጥ አባታቸው ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ ሲያርፉ ዙፋኑን ተቀብለው ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ሆኑ።
የካቲት ፪ ቀን
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - ቡልጋ ጨመሪ ላይ እነ ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ እና ሌሎችም አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ገጥመው ትልቅ ውጊያ ተደረገ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - 'ቦይንግ ፯፻፵፮' (Boing 747) የተባለው አየር ዠበብ በዛሬው ዕለት የሙከራ በረራውን አገባደደ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ጨረቃ ላይ ለሦስተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሰዎችን ያሳረፈው አፖሎ ፲፬ መንኮራኩር ጉዞውን አገባዶ ወደምድር ተመለሰ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሶዩዝ ፲፮ የተባለችው የሶቪዬት መንኮራኩር የሕዋ ጣቢያ ላይ ለ፳፱ ቀናት ቆይታ ወደምድር ተመለሰች።
- ፲፯፻፰ ዓ/ም - በእስራት ላይ የነበሩት የ ፳፩ ዓመቱ ጎልማሳና የንጉሥ ኢያሱ አድያም ሰገድ ልጅ ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት እንደነገሡ አዋጅ ተነገረ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ (ዓፄ ቴዎድሮስ)ና ደጃዝማች ውቤ ቧሂት ላይ ድንኳን ተክለው ተገናኙ። ደጃዝማች ካሳም የእንግሊዙን ሊቀ መኳስ ዮሐንስን (John Bell)በመንጥር አይተህ ንገረኝ አሉት። የሸማ ድንኳን ባየ ጊዜ ነገራቸው። ደጃዝማች ካሳም «አያሳድረኝ አላሳድረውም» ብለው ተናገሩ። ያንግዜውንም ተነሣ አሉ። ባሰለፉትም ጊዜ እንዴህ ብለው በፍከራ ትንቢት ተናገሩ። «እንኳን ይህን ቁርጥማታም ወሎን፣ መትቼ የሻዋውን ንጉሥ እይዘዋለሁ። ስሜን ስሜን እንግርሀለሁ ያልሁህ ወታደር ስሜም ቴዎድሮስ ነው» አሉ። አስቀድሞ ገና በንጉሥ አምላክ በል። ስሜን ስሜን እነግርሀለሁ ብለው ነበርና። ያንጊዜውን እንዴህ አሉ። «ወታደር አይዞህ አትፍራ። የውቤ ነፍጥ የውቤ ነፍጥ ቢልህ የተለጎመው ጨርቅና ባሩድ ነው። አይነካህም» አሉት። እኔ የክርስቶስ በርያ ሁሉንም አሳይሀለሁ ወታደር ባሉ ጊዜ ሰልፍ ገጠመ። ደጃች ውቤም ተያዙ።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ንግሥት ዘውዲቱ፣ "ግርማዊት ዘውዲቱ፣ ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተብለው በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዐ መንግሥት ተቀብተው የንጉሠ ነገሥቱን ዘውድ ጫኑ።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ » በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የዳግማዊ ምኒልክ ባለቤት፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡል አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸውም በእንጦጦ መንበረ ፀሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ። በኋላ ግን አጽማቸው ተነስቶ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለአባታቸው ዳግማዊ ምኒልክ አጽም ማሣረፊያ ባሠሩት የታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በኢራቅ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ለተተካው የኮሎኔል አብዱል ሳላም አሪፍ መንግሥት ሕጋዊ ዕውቀት መስጠቱን አስታወቀ።
- ፲፮፻፹፭ ዓ/ም - ንጉሡ አጼ ኢያሱ ከጳጳሱ አባ ሲኖዳ እና እጨጌ ዮሐንስ ጋር አክሱም እንዳሉ ሙራድ የተባለ ታላቅ ግብጻዊ ነጋዴ በሕንድ ውቅያኖስ መጥቶ ከሆላንድ ንጉሥ ያመጣውን ሰላምታ እና ደብዳቤ አቀረበ።
- ፲፯፻፰ ዓ/ም - ማክሰኞ ዕለት የአጼ ኢያሱ አድያም ሰገድ ልጅ ንጉሥ ዳዊት፣ አጼ ዳዊት አድባር ሰገድ ተብለው ዘውድ ጭነው ነገሡ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ ደረስጌ ማርያም ላይ አቡነ ሰላማ ቀብተዋቸው ዘውድ ጭነው ዓፄ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተባሉ።
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም - የ ፲፪ ዓመቱ ልጅ ማር (ጌታ) ሠርፀ ድንግል፣ አባታቸው አጼ ሚናስ ሲሞቱ በስመ መንግሥት መለክ ሰገድ ተብለው ነገሡ። አጼ ሠርፀ ድንግል የመንግሥት ሥራቸውን የሚሠሩት በእናታቸው በእቴጌ አድማስ ሰገድ ሥሉስ ኃይላ አማካይነት ነበር።
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም ኢትዮጵያን ከአራት ዓመታት በንጉሥነት የመሯት አፄ ሚናስ (ስመ መንግሥት፣ ቀዳማዊ አድማስ ሰገድ) በዕለተ እሑድ አረፉ፡፡ አጼ ሚናስ የአጼ ገላውዴዎስ ወንድምና የአጼ ልብነ ድንግል ልጅ ነበሩ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ‘የዓለም አቀፍ የንግድ ሒሣብ መሣሪያዎች ድርጅት’ አይ.ቢ.ኤም(IBM) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም በዓለም የመጀመሪያው ሁለ-ገብ መቀምር (Electronic Numerical Integrator And Computer) ወይም ኮምፕዩተር ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የመከላከያ ንዑስ ሸንጎ አባላት አዲስ አበባ ላይ ስብሰባቸውን ጀመሩ።
- ፲፭፻፴፬ ዓ/ም - ኢትዮጵያን ሊረዳ የመጣው የቡርቱጋል ሠራዊት ጦር መሪ ዶም ክርስቶፍ ዳጋማ በአህመድ ግራኝሠራዊት ላይ አምባ ስንኢት በሚባል ሥፍራ ዘመተ።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - በሆለታ ገነት፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስም የጦር ተማሪ ቤት ተከፈተ።
- ፲፱፻፵፬ የታላቋ ብሪታኒያ የንግሥት ኤልሳቤጥ አባት ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ በዊንድሶር ግምብ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ውስጥ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - እቴጌ መነን አስፋው በዚህ ዕለት በተወለዱ ፸፫ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፰፻፹፱ ዓ/ም - ራስ አሉላ እንግዳ(አባ ነጋ) በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ የብሥራተ ወንጌል ራዲዮ ጣቢያን ለመትከል በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እና የሉተራውያን የዓለም ኅብረት መሃል የውል ስምምነት ተፈረመ።
- ፲፯፻፴፮ ዓ/ም - አጼ ኢያሱ ብርሃን ሰገድ ከጳጳሱ አባ ዮሐንስ እና ከ እጨጌ ኤውስጣቴዎስ ጋር ሆነው አንድ የሶርያ ተወላጅ ነጋዴ በሐሰት ጳጳሱ እኔ ነኝ እያለ ብዙ ሰዎችን በማሳሳቱ አስረው ወደአገሩ አባረሩት።
- ፲፯፻፷፪ ዓ/ም - የስኮትላንድ ተወላጁ ሐዋጼ አህጉር (explorer) ጄምስ ብሩስ በዕለተ ሐሙስ ጎንደር ገባ። እዚሁም እስከ ታኅሣሥ ወር ፲፯፻፷፬ ዓ/ም ድረስ ተቀመጠ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም - ታላቁ ደራሲና ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ራስ ቢትወደድ መኰንን እንዳልካቸው ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በጋቦን የተከሰተው መፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚደንት ሌዮን ምባን ከሥልጣን አስወረደ።
- ፲፫፻፳፬ ዓ/ም - ቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን በደቡብ ኢትዮጵያ እስላማዊ ግዛቶችን ለማስገበር ዘመቱ።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለራስ ወልደ ጊዮርጊስአቦዬ ዘውድ ጭነውላቸው ንጉሠ ዘቤጌምድርና ስሜን አድርገው ሾሟቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት የመምህራን አድማ ተደረገ። ከዚህም ጋር አብሮ የአዲስ አበባ ታክሲ ነጅዎች አድማ አደረጉ። የታክሲ ነጅዎቹ አድማ ለስድስት ቀናት ቆየ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትን መስከረም ፪ ቀን የገለበጠውን፣ የኅብረተ ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር (ደርግ) ለመገርሰስ፣ በቀድሞ አጠራሩ ተጋድሎ ሓርነት ሕዝብ ትግራይ (ተሓሕት"፣ በኋላም ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ተመሠረተ፤ በምዕራባዊ ትግራይ ደደቢት በተባለ ሥፍራም የትጥቅ ትግሉን ጀመረ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ደራስያን አንድነት ማኅበር (ኢደአማ) ስሙን ወደ ኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) የለወጠበት ዕለት።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ለኢጣሊያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ ምክንያት በጄነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ከተሰበሰቡት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ለፋሺስቶቹ ያደሩ ከሀዲ ባንዳዎችና መኳንንት፤ የፋሺስት ባለ ሥልጣናት ወታደሮች በተሰበሰቡበት መኻል፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የእጅ ቦምብ ወርውረው አደጋ ሲጥሉ ግራዚያኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል። ይኸንን ድርጊት በመበቀል ሰበብ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፈጨፉ፤ ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖችና ካህናት፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት በሙሉ እየተለቀሙ ተጨፈጨፉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ ቆልፈው ቤንዚን እያርከፈከፉ አቃጠሉአቸው። በአካፋ፣ በዶማ፣ በመጥረቢያ በተገኙበት ኢትዮጵያውያንን እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ፋሽስቶች የአዲስ አበባንና የአካባቢውን ሕዝብ በጅምላ ጨፈጨፉት። በሶስት ቀናት ፴ሺህ ሕዝብ መስዋዕትነት ተቀበለ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ-ኤ-ኤፍ ደብልዩ (ET-AFW) ዲሲ ፫ (Douglas C-47B-10-DK፤ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ በምትገኘው ባረንቱ ላይ በቦምብ ፍንዳታ ተከስክሶ ሲወድቅ አምስቱም ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የአዲሲቷን ቻይና የሰብዓዊ እና ኤኮኖሚካዊ ገጽታዎች በማነጽ አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን የያዘችውን የኤኮኖሚያዊ ኃያልነት ሥፍራ እንድትይዝ ያስቻሏት መሪዋ ዶንግ ዥያው ፒንግ በተወለዱ በ ፺፪ ዓመታቸው አረፉ።
- ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች የሁዳዴ (ዓቢይ) ጾም ይጀምራሉ።
- ፲፭፻፴፭ ዓ/ም - በዕለተ ረቡዕ አህመድ ግራኝ ወገራ ላይ የንጉሥ ገላውዴዎስን ሠራዊት ገጥሞ በቡርቱጋል ነፍጥ ተመቶ ሲሞት የተረፈው ሠራዊቱ ተሸንፎ ኮበለለ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ በፈነዳው አብዮት፣ የወጥቶ-እብስ ሠራተኞት የሦስት ቀን አድማቸውን ጀመሩ። በ[አዲስ አበባ]] በየቀበሌው እና በየመንገዱ የሚካሄደው ሽብር ቀጥሎ ዋለ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የአፍሪቃ፤ የካሪቢያን እና የሰላማዊ ውቅያኖስ አገሮች የንግድ ሚኒስቴሮች ከአውሮፓ የ ኤኮኖሚክ ኅብረት ጋር የንግድ ግንኙነትን ለማጠንከር አዲስ አበባ ላይ ስብሰባቸውን ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደቻይና የበረራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዝ አገር ሕክምና ላይ የነበሩትን አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰንን ለመጠየቅ ለአራት ቀን ቆይታ ሎንዶን ገቡ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ራስ ደስታ ዳምጠውቡታጅራ አካባቢ ላይ በትግራይ ተወላጁ በደጃዝማች ተክሉ መሸሻ ተይዘው በፋሺስት ኢጣልያእጅ ወደቁ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ግብጽ እና ሶርያ የአረብ ሪፑብሊ ኅብረትን (United Arab Republic) መሠረቱ። ይሄ የሁለቱ አገሮች ኅብረት ከሦስት ዓመታት በኋላ ቢፈርስም የግብጽ መጠሪያ ስሟ ሆኖ ለብዙ ዓመታት ቆይቷል።.
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ሎንዶን በሕክምና ላይ የነበሩትን የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ፣ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰንን ለመጠየቅ መጥተው የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በዛሬው ዕለት በባኪንግሀም ቤተ መንግሥት ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ የ’ሻይ’ ግብዣ አደረጉላቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ፍንዳታ የተፋፋመውን ሽብር ለመቆጣጠር በተወሰደው እርምጃ፣ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ወታደሮችን በአዲስ አበባ ከተማ ቀበሌዎችና ‘ቁልፍ’ ቦታዎች ለጥበቃ አሰማራ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በግራዚያኒ የሚመራ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በዝዋይ አካባቢ የጦር አዝማቾቹን የራስ ደስታ ዳምጠውን እና የደጃዝማች በየነ መርዕድን አርበኞት ድል አደረጉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች ሕይወታቸውን በዚህ ዕለት ሰዉ። ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ በጥይት ደበደቧቸው፡፡
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት አስገዳጅነት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የሕዝቡን ሸክም ለማቃለል የነዳጅ ዋጋ ቅነሳን የሚያካትት ኤኮኖሚያዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል አካባቢ ተኩስ ተከፈተ። በዚሁ ዕለት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ለወታደሮች የደሞዝ ጭመራ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።
- ፲፭፻፲፱ ዓ/ም - በምድረ አዳል (አሁን አፋር (ክልል)) የባሌው መኮንን ዴገልሃን ሠራዊት ከአህመድ ግራኝ ጋር ጦርነት ገጥሞ የዴገልሃን ሠራዊት በሙሉ ተጨፈጨፈ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የሉተራውያን ድርጅት በኢትዮጵያ ‘የወንጌል ድምጽ ራዲዮ’ (ብሥራተ ወንጌል ራዲዮ) ጣቢያ አገልግሎቱን ጀመረ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ሴቶችን የቅስና ሥልጣን ለመቀበል የሚያስችለውን ውሳኔ ከፍ ባለ የድምጽ ብዛት አጸደቀ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት እንቅስቃሴ የወታደሩ ዓመጽ በሐረር፣ ድሬ ዳዋ፣በደብረ ዘይት ዓየር ኃይል እና በምጽዋ የባህር ኃይል ውስጥ ተቀጣጥሎ ተስፋፋ። የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት መላክተኞች ከ፪ተኛ ክፍለ ጦር አባላት ጋር ለመደራደር ወደአስመራ በረሩ።
- ፲፯፻፸፪ ዓ/ም - በኢራን የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ ፪ መቶ ሺህ ሰዎችን አጠፋ።
- ፲፱፻፲፬ ዓ/ም - የብሪታኒያ ንጉዛት መንግሥት በራሱ ፈቃድ በግብጽ ላይ የነበረውን ሉዐላዊነት አቁሞ ነጻነትን ለግብጻውያን አሳልፎ ሲሰጥ የውጭ ጉዳይን፤ ግንኙነትን፤ የጦር ሠራዊትንና የግብጽ ሱዳንን አስተዳደር የሚመለከቱ ጉዳዮችን ግን በራሱ አስተዳደር ሥር አስቀረ።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - ለዱፖንት ኩባንያ ይሠራ የነበረው ዋላስ ካሮዘርስ ናይሎን (Nylon) ፈጠረ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ፍንዳታ፣ የወታደሩ አመጽ ተስፋፍቶ አዲስ አበባ የሚገኙ የ፬ተኛ ክፍለ ጦር፤ የጦር ሠራዊት፤ ዓየር ኃይል እና የዋና መሥሪያ ቤት ወታደሮች በከተማው ‘ቁልፍ’ ቦታዎችን በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ። ብዙዎችን የአክሊሉ ሀብተ-ወልድን ሚኒስቴሮች አስረው ያዙ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አቶ እንዳልካቸው መኮንንን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እና ጄኔራል አቢይ አበበን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ ሊካሄድ ተዘጋጅቶ የነበረው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ስብሰባ በረብሻው ምክንያት ተሰረዘ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የመሬት እንቅጥቅጥ በአርሜኒያ እና አዘርባይጃን አገሮች ፩ ሺህ ፩ መቶ ሰዎች ሲገል፣ በሰሜን ኢራን ደግሞ ፫ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
- ፲፯፻፴፫ ዓ/ም - የሸዋው መስፍን መርዕድ አዝማች አብዬ አረፉ። ቀብራቸውም በሐር-አምባ ሚካኤል ተከናወነ። ልጃቸው መርዕድ አዝማች አምኃ ኢየሱስ ተተክተው ምስፍናውን ያዙ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር ፪፻፷፩/፶፪ መሠረት ፀደቀ። የድርጅቱ ማቋቋሚያ የአደራ መስጫ ሰነድ (ቻርተር) በሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም በመንግሥት ማስታወቂያ ቁጥር ፪፻፶፫/፶፩ መሠረት ወጥቶአል። ይህ ድርጅት በጥቅምት ወር ፲፱፻፷፮ ዓ/ም የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት በአዋጅ እስከወረሰው ድረስ አገልግሏል።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በሞሮኮ የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ አጋዲር የተባለችውን ከተማ አወደመ።
- ፳፻፭ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ቤኔዲክት ፲፮ኛ «የዕድሜያቸው መግፋት የተደራረበ ሓላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ስላላስቻላቸውና በሚታይባቸው አካላዊ ድካምና አቅም ማጣት» በሚል ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ.ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ከሮማ አየር ዠበብ ጣቢያ ሊነሳ ሲዘጋጅ፣ ሽብርተኞች የጫኑት ቦምብ ተገኝቶ በጥበቃ/ፖሊስ ተወግዷል።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የሚንስትሮች ምክር ቤት ጉባዔ የኡጋንዳን ልዑካን በጉባዔው ላይ በመሳተፍ ጥያቄ ላይ ስምምነት ባለማግኘቱ ተበታተነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት የ፬ተኛ ክፍለ ጦር አስሯቸው የነበሩትን ሚኒስቴሮች ፈትተው ለንጉሠ ነገሥቱ አስረከቡ። በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ሲያካሂዱ፣ የክብር ዘበኛ ሠራዊት ደግሞ አመጻቸውን ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በብሪታኒያ እና በፈረንሳይ ትብብር የተሰራው ‘ኮንኮርድ’ አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈረንሳይ ከተማ ቱሉዝ ተነስቶ ለ ሃያ ሰባት ደቂቃ የበረራ ሙከራ አደረገ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - አሁን ዚምባብዌ የምትባለው የቀድሞዋ ሮዴዢያ ነጭ ዜጎች በመሪያቸው ኢያን ስሚዝ ሥልጣን አገሪቱን ከብሪታኒያ ዘውድ ጋር የነበራትን ሰንሰለት በጥሰው በሸፍጥ ሪፑብሊክ አደረጓት።
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የቀድሞው የሶቪዬት ኅብረት አባላት የነበሩት አርሜኒያ፤ አዘርባጃን፤ ካዛክስታን፤ ኪርጊዝስታን፤ ሞልዶቫ፤ ታጂኪስታን፤ ቱርክሜኒስታን እና ኡዝቤኪስታን እንዲሁም ሳን ማሪኖ በአንድነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባላት ሆኑ።
- ፲፱፻፪ ዓ/ም - እቴጌ ጣይቱ ብጡል ከሥልጣን ከመውረዳቸው ከሁለት ሣምንት በፊት፣ ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ዕለት ከሰጡት ሹመቶች አንዱ፣ የሐረርጌን ጠቅላይ ገዥነት ለደጃዝማች ተፈሪ መኮንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ነው።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - የቤጌምድር እና የስሜን ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ደብረ ታቦር ላይ አርፈው እዚያው ተቀበሩ።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - የዐቢይ ጾም ቅበላ ዕለት ዓፄ ኃይለ ሥላሴ መምህር ገብረ ጊዮርጊስን (በኋላ አቡነ ባስልዮስ) እጨጌነት ሾሟቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ፍንዳታ ሑከቱ ወደከርቸሌ እስረኞች ተሸጋግሮ በተከሰተው ረብሻ ፴፮ እስረኞች በጥይት ተገደሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በእንዳልካቸው መኮንን አስተዳደር ውስጥ አዲስ የተሾሙት ሚኒስትሮች ፓትርያርኩ አቡነ ቴዎፍሎስ ፊት ቀርበው ቃለ መኀላቸውን ሰጡ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መንግሥታት መሐል ውይይት ለማድረግ የኢትዮጵያን ልዑካን መርተው ወደካርቱም አመሩ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግሥቱን አጥንቶ የሚያሻሽል ቡድን መሠየማቸውን ይፋ አደረጉ።
- ፲፯፻፹፫ ዓ/ም - ቬርሞንት የአሜሪካ ኅብረት ፲፬ተኛዋ አባል ሆነች።
- ፲፰፻፺፩ ዓ/ም - የባየር መድኀኒት ኩባንያ አስፒሪን የተባለውን መድኀኒት በንግድ-ስም አስመዘገበ።
- ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - ‘ቴሌፎን’ ተብሎ የተሠየመው ፈጠራ የአዕምሯዊ ንብረትነቱ (patent) በአሌክሳንደር ግራሃም ቤል ስም ተመዘገበ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - ጋና ነጻ በወጣች ማግሥት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በወለጋ ጠቅላይ ግዛት የቅርፀ ምድር ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የቴክኒክ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በጃፓን መሀል ተፈረመ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በሱዳን ግዛት ውስጥ ባለችው ገላባት ላይ በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ የሚመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሱዳን 'ማህዲ' ሠራዊቶች በዚህ ዕለትጦርነት ገጥመው፣ ኢትዮጵያውያኖቹ በማሸነፍ ላይ ሳሉ ንጉሠ ነገሥቱ፣ መጀመሪያ እጃቸው ላይ፤ ቀጥሎም ደረታቸውን በጥይት ስለተመቱ የኢትዮጵያው ሠራዊት ከሥፍራው በማፈግፈግ ሲለቅ ድሉ የ'ማህዲዎቹ' ኾነ። ንጉሠ ነገሥቱም ማታውኑ አረፉ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት ባህር ዳር ላይ ፩ ሺህ ተማሪዎችን የሚያስተናገድ የቴክኒክ ትምህርት ቤት እንደምትሠራ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አስታወቀ
መጋቢት
ለማስተካከል- ፲፭፻፺፱ ዓ/ም - በጎጃም ምድር ጎል በተባለ ሥፍራ የንጉሥ አጼ ያዕቆብ እና የአጼ ሱስንዮስ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው ድሉ የሱስንዮስ ሆነ። አጼ ያዕቆብ እና ጳጳሱ ዳግማዊ ጴጥሮስ በዚሁ ጦርነት ላይ ሞቱ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በትልቅ ጦርነት ከደርቡሾች ጋር ሲዋጉ መተማ ላይ በእነሱ ውጅ ወደቁ። ሱዳኖቹ አንገታቸውን ቆርጠው እንጨት ላይ ሰክተው ገበያ ለገበያ ለሕዝባቸው አሳዩት።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአልቃይዳ መሥራችና መሪ ኦሳማ ቢን ላደን በዚኡ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ከኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበራት ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቁ።
- ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር (Civil Aviation Administration) ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ ፯መቶ፯ አየር ዠበብ ላይ ፍራንክፈርት አየር ማረፊያ ጣቢያ ላይ ቦምብ አፈነዱ።
መጋቢት ፬
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - መሬት አልባነትን ለማስወገድ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች በፓርላማው ፊት ለፊት ተሰልፈው «መሬት ለአራሹ የምትሹ፤ ተዋጉለት አትሽሹ» የሚለውን መዝሙራቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አሰሙ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የተመደቡ (ሦስት የሩሲያ ጋዜጠኞችና ሦስት የቼኮዝሎቫኪያ ዲፕሎማቶች)፤ ለተማሪዎች እንቅስቃሴ የገንዘብ እርዳታ አድርገዋል በሚል ወንጀል ከአገር እንዲባረሩ ተደረገ።
- ፳፻፭ ዓ/ም - የአርጀንቲናው ተወላጅ፣ ካርዲናል ጆርጅ ማርዮ በርጎግልዮ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጴጥሮስ ፪መቶ፷፮ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፓፓ) ኾነው ቀዳማዊ ፖፕ ፍራንሲስ ተብለው ተመረጡ።
- ፲፰፻፲፪ ዓ/ም - የሜይን ግዛት የአሜሪካ ኅብረት ፳፫ተኛዋ ዓባል ሆነች።
- ፳፻፪ ዓ/ም - ታዋቂው የቀድሞ የክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ግጥምና ዜማ ደራሲ/አቀናባሪ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ አረፉ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና ልዑል አልጋ ወራሽ መርድ አዝማች አስፋ ወሰን በደቡብ ኢትዮጵያ የእርሻ ልማት ሊጎበኙ ሄደው፣ የተሳፈሩበት የሩሲያ ኤም ፰ ሄሊኮፕተር ተሽከርካሪው በድንገት ተሰብሮ ሲከሰከስ ሦስት ተመልካቾች ሞተዋል፡ ንጉሠ ነገሥቱ እና አልጋ ወራሹ ግን ምንም ሳይሆኑ ተርፈው ጉዟቸውን በመኪና ቀጥለዋል።
- ፲፸፻፶፭ ዓ/ም - በባሊ ደሴት ላይ የሚገኘው ሦስት ሺ ሜትር ቁመት ያለው የአጉንግ ተራራ በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እስከ አሥራ አንድ ሺ ሰዎችን ፈጅቷል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በእርሻ ልማት መስክ ለአዋሽ ሸለቆ ማልሚያ ሁለት ስምምነቶችን ፈረሙ። በተጨማሪ የዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (IDA) በኢትዮጵያ ለከብት እርባታ የሚውል የአምሥት ሚሊዮን ዶላር ዋስትና እንደሚሰጥ አስታወቀ።
- ፲፱፻፹ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር ሠራዊት በአፋበት ግንባር በተሰማራው የ’ናደው እዝ’ ጦር ላይ ከጎንና ከኋላም አስርጎ ሲያጠቃ በኮሎኔል ጌታነህ ኃይሌ የሚመራው የናደው እዝ በከፍተኛ ሽብር ሊሸነፍ ቻለ።
- ፳፻፬ ዓ/ም - በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ፓትርያርክ ሆነው ከ፲፱፻፷፬ ዓ/ም ጀምሮ ለ፵ ዓመታት የእስክንድርያ (ኮፕት) ቤተ ክርስቲያንን የመሩት መንፈሳዊ አባት አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በዛሬው ዕለት በተወለዱ በ፹፰ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እንግሊዞች በዳርዳኔል ቱርክ ላይ ሲወረሩ አልተከናወንም።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በቱርክ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የ ፪መቶ፶ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - በምሥራቃዊ ጀርመን ለመጀመርያ ጊዜ የነጻ ምርጫ ተካሄደ።
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - ስመ ጥሩው አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር አረፉ፡፡
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የናዝሬት ትምህርት ቤት አዲስ አበባ ላይ ተከፈተ፡፡
- ፲፭፻፳፪ ዓ/ም - ከአህመድ ግራኝ ጋር ሽምብራኩሬ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ጦርነት ራስ ኅዱግ፣ ራስ ማኅፀንቶ፣ ገብረ መድኅን እና ብዙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አለቁ።
- ፲፱፻፵፮ ዓ/ም - የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ተመርቆ ተከፈተ፡
- ፳፻፪ ዓ/ም - የአፍሪቃ ኅብረት የሠላምና ጸጥታ ምክር ቤት በማዳጋስካር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በለወጡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ፡፡
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በአፓርታይዳዊ ደቡብ አፍሪቃ፣ በታሪክ ዘገባ ‘የሻርፕቪል ፍጅት’ (Sharpeville Massacre) በሚባለው ክስተት ፖሊሶች በጥቁር ሕዝብ ላይ ተኩስ ሲከፍቱ ፷፱ ጥቁሮች ሲገደሉ ፻፹ ሰዎች በጥይት የቁስል አደጋ ደርሶባቸዋል።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - የደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ ትባል የነበረችው አገር ከሰባ አምሥት ዓመታት የቅኝ ግዛትነት በኋላ ናሚቢያ ተብላ ከአፓርታይዳዊ ደቡብ አፍሪቃ ነጻ ወጣች
- ፲፰፻፵፱ ዓ/ም - በጃፓን የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ የ ፻ ሺህ ሰዎችን ነፍስ አጠፋ
- ፲፰፻፺፰ ዓ/ም - ልዑል ራስ መኮንን ቁልቢ ላይ አርፈው ቀብራቸው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተከናወነ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - በጣልያን ከተማ ሚላኖ፣ ቤኒቶ ሙሶሊኒ የፋሺስት ፓርቲን መሰረተ።
- ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የአለማኒያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዶልፍ ሂትለር የሚመራው የሚንስትሮች ሸንጎ በራሱ ሥልጣን ሕግ መደንገግ የሚያስችለውን ሕግ (ሕጋዊ አምባ ገነንነት) ደነገገ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በአይሮፍሎት በረራ ቁጥር ፭፻፺፫ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ፸፭ ሰዎች፤ የአብራሪው የ ፲፭ ዓመት ልጅ አየር ዠበቡን በ’ስህተት’ ከአውቶ-ፓይለት በመሰረዙ ሳይቤርያ ውስጥ ተከስክሰው አለቁ።
- ፲፰፻፺፪ ዓ/ም - ራስ ዳርጌ ሣህለ ሥላሴ በተወለዱ በ ፸ ዓመታቸው አርፈው በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ። ራስ ዳርገ የዳግማዊ ምኒልክ አጎት ነበሩ።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የመጀመሪያውና ሦስተኛው ፕሬዚደንት ዴቪድ ዳኮቡሺያ በምትባል መንደር ተወለዱ
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ እና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ራስ ተፈሪ መኮንን «ስለ ባሮች አስተዳደርና ነፃነት የቆመ ደንብ» በሚል ርእስ የተጻፈ ባለ አሥር ገጽ መመሪያ አሳተሙ። በአገሪቱም “ባሪያ” እንዳይሸጥ፣ እንዳይገዛ የሚከለክል አዋጅ መጋቢት ፳፪ ቀን ታወጀ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ንቅንቅ፣ በኮሎኔል የዓለም ዘውዴ የተመራ የአየር ወለድ ሠራዊት በደብረ ዘይት የአየር ኃይል ረብሸኞችን በመምታት በቁጥጥር ስር አዋለ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የባለ ሥልጣናትን አቋም እና ወንጀል የሚያጠና አጣሪ ሸንጎ እንደመሠረቱ አስታወቁ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ምናኽም ቤጊን በአሜሪካ ርዕሰ ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የሰላም ውል ተፈራረሙ።
- ፲፰፻፸ ዓ/ም - ዓፄ ዮሐንስ እና የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ወሎ፣ ቦሩ ሜዳ ላይ ተገናኝተው ንጉሥ ምኒልክ የንጉሠ ነገሥቱን የበላይነት መቀበላቸውን እና ዓፄ ዮሐንስ ደግሞ የምኒልክን በሸዋ ላይ ንጉሥነታቸውን በመቀበል በመሐላ ታረቁ። ንጉሠ ነገሥቱ ለንጉሥ ምኒልክም ዘውድ ጫኑላቸው።
- ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - የሆላንድ 'ኬ.ኤል.ኤም' 'ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ እና የ'ፓን-አም' ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ በ'ካናሪ ደሴቶች፤ ቴኔሪፍ ጥያራ ጣቢያ ማኮብኮቢያ ላይ በጉም ምክንያት ተጋጭተው፣ የ'ኬ.ኤል.ኤሙ' ፪መቶ፵፰ ተሣፋሪዎች በሙሉ ሲሞቱ ከ'ፓን-አሙ' ተሣፋሪዎች መኻል ፫መቶ፴፭ ሞተው ፷፩ ሰዎች ተርፈዋል። ይኼ አደጋ በታሪክ ከተከሰቱት የጥያራ አደጋዎች በሙሉ እጅግ የባሰ አደጋ በመሆን ይታወቃል።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የንግድ እና ኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የቱርክ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ‘አንጎራ’ ስሟ ተለውጦ አንካራ ስትባል፤ የአገሪቱ አንደኛ ከተማ እና በሮማይስጡ ቄሳር ቁስጥንጢኖስ የተመሠረተችው ቁስጥንጢንያ ወይም ኮንስታንቲኖፕል (Constantinople) ስሟን ቀይራ ኢስታንቡል ተባለች።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ ከተሰነዘሩት ዐበያት ሕዝባዊ እሮሮዎች አንዱ በመሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ግፈኝነት እና ሙስና ስለነበር ይሄንኑ ጉዳይ እንዲያጠና የተመሠረተው ኮሚሲዮን አባላት ተሠየሙ።
- ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - ለ መብራት ኃይል የእግር ኳስ ክለብ፤ የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ እና የድሬ ዳዋ ባቡር የእግር ኳስ ክለብ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ ለየመን የአል ሳቅር የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቹ ዮርዳኖስ አባይ በዚህ ዕለት ተወለደ
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ፤ በጆሃንስበርግ ከተማ፣ በዙሉዎችና ‘የአፍሪቃ ብሔራዊ ሸንጎ’ (African National Congress) ደጋፊዎች መኻል በተከሰተው ሽብር አሥራ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - ክቡር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ።
- ፲፱፻፬ ዓ/ም የሞሮኮ መሪ ሱልጣን አብደልሃፊድ አገሪቱን በፈረንሳይ ጥላ ሥር ያደረገውን ስምምነት ፈረሙ። ሞሮኮ ከ ፵፬ ዓመት በኋላ መጋቢት ፳፱ ቀን ፲፱፻፵፰ ዓ/ም በ ግርማዊ ዳግማዊ ሀሰን መሪነት ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የታኅሣሥ ግርግር በመባል በታሪክ መዝገብ የሚታወቀውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በግንባር ቀደምነት ያካሄዱት የክብር ዘበኛ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ በተቀበሉት ፍርድ መሠረት በስቅላት ተቀጡ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም፣ ልዑል አልጋወራሽ ተፈሪ መኰንን የባርያ ነፃነትን ደንብ አቆሙ/ደነገጉ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ.ም.፣ ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አዝማችነት ከኢጣሊያን ሠራዊት ጋር በማይጨው ጦርነት ገጠመች
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የዓፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት፣ የታኅሣሥ ግርግር መሪ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ በተሰቀሉ ማግሥት በተደረገው ሹም ሽር ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ፣ በጊዜው በሎንዶን አምባሳዶር የነበሩት ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ደግሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ልጅ እንዳልካቸው የ ስድሳ ስድስቱ አብዮት ሲፈነዳ ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉን በመተካት ከ ሠላሳ ሦስቱ ድል በኋላ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስቶች በዚሁ አብዮት ተገድለዋል።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ፓሪስ የመንገደኛ መሥመር፣ የመጀመሪያውን በረራ አከናወነ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም በኢትዮጵያ በሆቴሎች እና በቱሪዝም የሥራ ዘርፍ ፋና ወጊ በመሆን ሀገራቸውን ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በቀለ ሞላ በተወለዱ በ፹፯ ዓመታቸው ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
- ፲፮፻፩ ዓ/ም – አጼ ሱስንዮስ የደብረ ዘይት ዕለት በአክሱም ጽዮን (ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፅዮን) ቤተ ክርስቲያን፣ በስመ መንግሥት ሥልጣን ሰገድ ተሰይመው ነገሡ።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በንጉሠ ነገሥት ዙፋን ተቀመጡ፡፡
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በነገሡ በአሥራ ሦሥት ዓመት ተኩል በ፶፬ ዓመት ዕድሜያቸው ዐረፉ። አባታቸው ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በተቀበሩበት በታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ዳግማዊ አቡነ ዮሐንስ-ጳውሎስ በ፹፬ ዓመት ዕድሜያቸው አለፉ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የዓፄ ቴዎድሮስ ትልቁ መድፍ፣ 'ሴባስቶፖል' ከስድስት ወራት ጉዞ በኋላ በዚህ ዕለት መቅደላ ምሽግ ስር ሰላምጌ ደረሰ።
- ፲፰፻፹፫ ዓ/ም - የግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው ልደት።
- ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል።
- ፲፱፻፵፩ ዓ/ም - አሥራ ሁለት ምዕራባውያን አገሮች፤ የአሜሪካ ኅብረት፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ፈረንሲስ፣ ቤልጂግ፣ ሆላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኢጣልያ፣ ሉክሳምቡርግ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ካናዳ እና ብርቱጋል በስምምነት የሰሜን አትለንቲስ የውል ድርጅት (North Atlantic Treaty Organization (NATO) ) መሠረቱ
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኒው ዮርክ መንታ ሰማይ-ጠቀስ ፎቆች (‘የዓለም የንግድ ማዕከል’ World Trade Center ) ሕንፃ ግንባታ ተጠናቀቀ። እነዚህ መንታ ፎቆች መስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም በአመጽ የአየር ዠበብ ግጭት ወድመዋል።
- ፲፭፻፶፩ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በአዋሽ አካባቢ ከአዳሉ አሚር ኑር ጋር በተደረገ ጦርነት ላይ ዓፄ ገላውዴዎስ እና የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ዮሐንስ ተገደሉ። በሐረሩ ዘእና መዋዕል ዘገባ አሚር ኑር የንጉሠ ነገሥቱን ጭንቅላት ወደይፋቱ ሡልጣን ሳዳዲን ልኮ ዘመቻውን ቀጠለ። ወንድማቸው ዓፄ ሚናስ በስመ መንግሥት አድማስ ሰገድ ተብለው በኢትዮጵያ አልጋ ተክተዋቸው ነገሡ።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የብሪታንያ ቅኝ ገዚዎች በሕንድ ሕዝብ ላይ ጭነውት የነበረውን የ’ጨው ቀረጥ’ ሕዝቡ በማህተማ ጋንዲ መሪነት በሠላማዊ ሰልፎች መቃወሙን ቢያሳይም ትግሉ አልተሳካለትም ነበር። ነገር ግን ጋንዲ ወደ ጨው-ባሕር ወርደው ከባሕር ውሐ ጨው በነጻ ማውጣት በመቻላቸው ቅኝ ገዥዎቹ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በሕዝቡ ላይ አውጀውት የነበረውን የጨው ፍብረካ ባለቤትነት የግዳጅ ቀንበር ሰብሮታል።
- ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከስደት ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ አርበኞች ትግል እና በብሪታኒያ ሠራዊት እርዳታ የጣሊያንን ሠራዊት ድል እየመቱ ደብረ ማርቆስ ከተማ ገቡ፡፡ በምሥራቅ ኢትዮጵያ የተንቀሳቀሱ አርበኞችም አዲስ አበባን በዚሁ ዕለት ያዙ፡፡
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - የርዋንዳ እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንቶች አብረው የተሳፈሩበት አየር ዠበብ በርዋንዳዋ ርዕሰ ከተማ ኪጋሊ አካባቢ ላይ በደረሰበት አደጋ ሁለቱም ፕሬዚናንቶች ሞተዋል።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሥሩ የሚተዳደር ዓለም አቀፍ የሕዝብ ጤንነት ባለ ሥልጣን ድርጅት - ‘የዓለም ጤንነት ድርጅት’ን ( The World Health Organization (WHO)) መሠረተ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በርዋንዳ በጎሳ ልዩነት ላይ የተመሠረተው የእርስ በእርስ ፍጅት፣ የሁቱ ጎሠኞች እስከ ፰ መቶ ሺ የሚሆኑ የቱትሲ ብሔር ተወላጆችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ ፈጇቸው። የውጭ መንግሥታትን በጉዳዩ ጣልቃ እንዳይገቡ በተጤነ ዕቅድ፣ የርዋንዳ ሠራዊት በዚሁ ዕለት አሥር የቤልጂግ ጸጥታ አስከባሪ ወታደሮችን ገድለዋል።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀሜሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ በረራውን ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በአስመራ በኩል በምስር ርዕሰ ከተማ ካይሮ ላይ አከናወነ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በኬንያ ‘የአፍሪቃ ኅብረት እንቅስቃሴ’ መሪ የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ድርጅቱ በቅኝ ገዝዎቻቸው ላይ የ’ማው ማው’ ሽብርን አካሂዷል በሚል በተሰነዘርበት ክስ ኃላፊነት አለብዎ ተብለው ለሰባት ዓመት የጽኑ እሥራት ቅጣት ተፈረደባቸው።
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አቡነ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ ‘ባዚሊካ’ የዓለም መሪዎችና ምዕመናን በተገኙበት ተከናወነ።
ሚያዝያ
ለማስተካከል- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የአሜሪካ የጠፈር በረራና ምርመራ ባለሥልጣን (NASA the National Aeronautics and Space Administration) ’መርኩሪ’ በሚባለው የአገሪቱ የመጀመሪያ የሰው አሳፋሪ መንኮራኩር መርሐ-ግብር የሚሳተፉትን ጠፈርተኞች ለዓለም አስተዋወቀ። እነርሱም፦ ስኮት ካርፔንተር፣ ጎርደን ኩፐር፣ ጆን ግሌን፣ ቨርጅል ግሪሰም፣ ዎልተር ስኪራ፣ አላን ሼፈርድ እና ዶናልድ ስሌይተን ነበሩ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ሁለት የብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ብራያን ሃሪሶን (Brian Harrison) እና ጄምስ ስሌተር (James Slater) ለጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። ከንጉሠ ነገሥቱም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - የጥቁር አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት መሪ የዶክቶር ማርቲን ሉተር ኪንግ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተወለዱበት ከተማ በአትላንታ ተከናወነ። የጆርጂያ ክፍለ-ሀገር ገዥ ሌስተር ማደክስ ዶክቶር ኪንግ የ’ሀገር ጠላት’ ነበሩ በሚል አቋም እቀብሩ ላይ አልሳተፍም ብለው መቅረታቸው ሳይበቃ ለሟቹም ክብር የክፍለ ሀገሩን መንግሥታዊ ቢሮዎች እንደማይዘጉ አስታወቁ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የቡልጋሪያ ባለ ሥልጣናት ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር በሁለቱ አገሮች መኻል የባህላዊ ግንኙነት እና ልውውጥ ለመወያየት አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓትን ለመመሥረት የታዘዘውን አጥኒ ሸንጎ በማንኛውም ጉዳይ እንደሚተባበረውና እንደሚረዳው አረጋገጠ። አያይዞም መሬትን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ማንም ሰው ለማልማት ከሚችለው በላይ መሬት መያዝ እንዳይችልና ለወደፊት ከአርሶ አደሮች በስተቀር የእርሻ መሬት ለማንም እንደማይሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ እንደሚወጣ አስታወቀ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት ኢትዮጵያን አጥቅቶ ወረራ በመጀመሩ የብሪታኒያ መንግሥት በኢጣልያ ላይ ቅጣት እንዲጣል በመገፋፋትና እና በራሱ በኩልም በአውሮፓ ጦርነት የሚያቀጣጥል ቢሆንም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - ‘ቢትልስ’ (Beatles) የሚባለው የሙዚቃ ቡድን አባላት እርስ በእርስ ባለመስማማታቸው እንደተበተኑ የቡድኑ አባል የነበረው ፖል መካርትኒ ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - በደቡብ ኢራቅ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፭ ሺህ ፫ መቶ ሰዎችን ነፍስ አጥፍቷል።
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በ ሎርድ ናፒዬር የሚመራው የእንግሊዝ ሠራዊት እና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በመቅደላ ተራራ ሥር በምትገኘው እሮጌ በምትባል ሥፍራ ላይ ጦርነት ገጥመው የዓፄ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገብርዬ ሞቱ።
- ፲፱፻፫ ዓ/ም - የልጅ ኢያሱ ሞግዚት የነበሩትራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው አልፈው በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - የአዲስ አበባው ሊሴ ገብረ ማርያም ትምሕርት ቤት ተመረቀ፡፡
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤት ጭቆና ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሰብዓዊ መብት ሕግ አጽድቀው ፈረሙ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ ስለ ጋራ ጉዳዮች ለመወያየት የሰሜን አፍሪቃ አገሮችን መጎብኘት ጀመሩ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በታንዛኒያ መንግሥት ድጋፍ የተንቀሳቀሱ የኡጋንዳ ታጋዮች የአገሪቱን በትረ-ሥልጣን ከአምባ ገነኑ ኢዲ አሚን እጅ ፈልቅቀው ጨበጡ። አሚን ሸሽቶ ወደሊቢያ ኮበለለ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም ለአሥራ ሁለት ዓመታት አገራቸውን በፕሬዚደንትነት የመሩት አሜሪካዊው ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት በዛሬው ዕለት አለፉ። ሩዝቬልት የአሜሪካ ፴፪ኛው ፕሬዚደንት ነበሩ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የመጀመሪያውን ጠፈርተኛ፣ የ፳፯ ዓመት የአየር ኃይል አባል ዩሪ ጋጋሪንን በመኖራኩር ተኮሰች። ጋጋሪን በጠፈር በረራ ምድርን ለአንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ያህል ከዞረ በኋላ ወደመሬት ተመልሷል።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የአሜሪካ የበረራ እና የጠፈር አስተዳደር ድርጅት (NASA) ‘ስፔስ ሻትል’ በመባል የሚታወቀውን አየር ዠበብ/የጠፈር መንኮራኩር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደጠፈር ተኮሰ። ይኽ የመጀመሪያው አየር ዠበበ/መንኮራኩር ‘ኮለምቢያ’ (Columbia) የተባለው ሲሆን ሃያ ሰባት ጊዜ ወደጠፈር ተተኩሶ ከተመለሰ በኋላ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ/ም ተመልሶ ወደምድር ሲገባ ተቃጥሎ ተሰባበረ።
- ፭፻፭ ዓ.ም.፣ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ተወለደ።
- ፲፱፻፲፰ ዓ.ም.፦ ቤተ ሳይዳ (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል ፣ አሁን የካቲት ፲፪ የተባለው) ሆስፒታል ተቋቋመ፡፡
- ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ፦ ፪ ሺህ ፻፷፰ ወታደር ያሰለፈው የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ ሠራዊት፣ ቃኘው የሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ። ከዘማቾቹ ማህል አንዱ የነበረው ‘የክራሩ ጌታ’ የ፶ ዐለቃ ካሣ ተሰማ "እልም አለ ባቡሩ" በሚለው ዘፈኑ ይሄንን ዕለት አወድሶታል።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - አንጋፋው የፊልም ተዋናይ ሲድኒ ፗቲዬር ‘ሊሊስ ኦፍ ዘ ፊልድ’ (Lilies of the Field) በተባለው ፊልሙ የ’ኦስካር’ ሽልማት ሲቀበል የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ነው።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አ. አ.ድ) ((እንግሊዝኛ)፡ Organisation of African Unity (OAU)) የአፍሪቃ የሠራተኞች ማኅበራት የአንድነት ውል አዲስ አበባ ላይ ተፈረመ።
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የፋሲካ ማግሥት ዕለት መቅደላ አምባ ላይ የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት እና በሎርድ ኔፒዬር የተመራው የእንግሊዝ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው፣ ድሉ የእንግሊዞች ሆነ። ንጉሠ ነገሥቱ ዓፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ከመውደቅ እራሳቸውን ማጥፋትን መርጠው ሽጉጣቸውን ጠጥተው ሞቱ። ቀብራቸው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተከናወነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ከተጀመረ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየልጅ ልጃቸው ልዑል ዘርዓ ያዕቆብ በወቅቱ በሕክምነ ላይ ለነበሩት መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ተጠባባቂ አልጋ ወራሽ እንደሆኑ በይፋ አስታወቁ። ይሄም ማብራሪያ የንጉሠ ነገሥቱ የሁለተኛ ወንድ ልጅ የነበሩት የሟቹ የልዑል መኮንን ወንዶች ልጆች በዕድሜ የዘርዓ ያዕቆብ ታላላቆች ቢሆኑም ለዘውዱ ውርስ ቅደም ተከተል ግን ከአስፋ ወሰን ወንድ ልጅ ተከታይ እንደሆኑ አረጋግጧል።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - የኡጋንዳው አምባ ገነን ኢዲ አሚን በታንዛኒያ ሠራዊት እርዳታ ከተገለበጠ በኋላ ዩሱፍ ሉሌ የአገሪቱ አዲስ ፕሬዚደንት በመኾን ቃለ መሀላቸውን ፈጸሙ።
- ፲፰፻፶፯ ዓ/ም - አሥራ ስድስተኛው የአሜሪካው ፕሬዚደንት አብርሀም ሊንከን የመድረክ ትርዒት በሚያዩበት የፎርድ ቴአትር ውስጥ ነፍሰ ገዳዩ ጆን ዊልክስ ቡዝ በጥይት መታቸው። ሕይወታቸው በማግሥቱ አለፈች።
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪቃ ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል እንደምትሰጥ በጋና ከተማ አክራ ጉባኤ ላይ የተገኙት ክቡር አቶ አበበ ረታ አስታወቁ፡፡
- ፲፰፻፶፯ ዓ/ም ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አብርሀም ሊንከን በነፍሰ ገዳይ ጥይት በተመቱ በማግሥቱ አረፉ።
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም - አንድ ሺ አንድ መቶ ሃምሣ ሦስት (፩ሺ ፻፶፫) መኮንኖችና ወታደሮች ያካተተው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የሻለቃ ጦር በተ.መ.ድ. ሥር ተሰማርቶ በኮሪያጦርነት ለመሳተፍ በዚህ ዕለት ከጂቡቲወደብ ተሣፈረ።
- ፲፭፻፴፬ ዓ/ም - በግራኝ መሀመድ እና በብርቱጋል ሠራዊት መኻል ብርቱ ጦርነት ተካሄደ። ብዙ ሰዎች በጥይት ቀኦሰሉ፣ ሞቱ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለሚቀጥለው ዓመት የወጪ እቅድ (Budget) ፮ መቶ ፴፫ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር እንደሚሆን ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ትግል ድሬ ዳዋ ላይ ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ ከፍተው ስድስት ሰዎችን አቆሰሉ። በምጽዋ እና አስመራ የባሕር ወደብ እና የምድር ባቡር ሠራተኞች አድማቸውን ጀመሩ።
- ፲፱፻፵፮ ዓ/ም - በግብጽ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ኮሎኔል ጋማል አብደል ናስር ሥልጣን ጨበጡ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ስመጥሩው ኢትዮጵያው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በአርሲ፣ አሰላ ከተማ ተወለደ።
- ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - የጀርመን ተወላጁ የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናት ሊቅ አልበርት አይንስታይን በተወለደ በሰባ ስድስት አመቱ አረፈ።
- ፲፭፻፶፫ ዓ/ም የ፲፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ታላቅ ደራሲ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ዕንባቆም አረፉ።
- ፲፮፻፹፰ ዓ/ም - የሆሣዕና በዓል ማግሥት የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ በነበረችው በጎንደር ከተማ በአንዲት ሴት-አዳሪ ቤት የተነሳ እሳት በ’ግራ ቤት’ አካባቢ ያሉትን ቤቶች በሙሉ ከመፍጀቱም ባሻገር፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናትም ተቃጥለዋል።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት እንቅስቃሴ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን የፖሊስ ሠራዊት አባላትን አነጋገሩ። በዚሁ ዕለት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አክሊሉ ኃብቴ ሥራቸውን ለቀቁ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የቡሩንዲን ንጉዛት የሁለት ቀን ጉብኝት ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት ቃጠሎ ወደ ፴ሺ የሚጠጉ የእስልምና ተከታዮች አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - የጀርመን የናዚ ፖለቲካ ቡድን መሥራችና መሪ የነበረው አዶልፍ ሂትለር በዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፲፰ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ በሎንዶን ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጃማይካን ለመጎብኘት ኪንግስተን ሲገቡ ከመቶ ሺ የማያንሱ ሰዎች የደመቀ አቀባበል አደረጉላቸው። ይሄን ዕለት የ’ራስ ተፈሪያን’ ተከታዮች በየዓመቱ የዚያን የጉብኝት ማስታወሻ አድርገው ያከብሩታል።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - መቶ ሺ ተማሪዎች በቤይጂንግ ከተማ ‘ቲያናንመን’ አደባባይ ላይ የቻይናን የፖለቲካ ሥርዓት በመቃወም የሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
- ፲፱፻፳ ዓ/ም በመካከለኛው የግሪክ ግዛት ውስጥ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ አደጋ የቆሮንጦስን ከተማ አወደመ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - በላይቤሪያ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የሃምሣ ዓለቃ ዶ ተከታዮች፣ የቀድሞውን ፕሬዚደንት የዊሊያም ቶልበርትን ታላቅ ወንድም ጨምሮ ብዙ የቀድሞ ባለሥልጣናትንና ሚኒስቴሮች ረሸኗቸው።
- ፳፻፫ ዓ/ም - በመላው ዓለም የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በዛሬው ዕለት የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለተ ዓርብ በማስታወስ ይዘክራሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአብዮቱ ፍንዳታ እይተካሄዱ ያሉትን አድማዎችና ሰላማዊ ሰልፎችን ለመግታት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አስታወቀ። የፖስታ ሠራተኞች የአራት ቀን አድማቸውን ጀመሩ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ናሚቢያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መቶ ስልሳኛ አባል ሆነች።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - የሩሲያ ኅብረት መንግሥት (Russian Federation) የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የነበሩት ቦሪስ የልስቲን በተወለዱ በሰባ ስድስት ዓመታቸው አረፉ
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ በሀገራቸውና በጎረቤት አገር ሶማሊያ ጋር ያለውን ጸብ በሰላም ለመፍታት ተልከው ሞቃዲሹ ገቡ።
- ፳፻፫ ዓ/ም - በመላው ዓለም የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእምነታቸው ዋና ምሠሶ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን መነሳት መታሰቢያ - የትንሳዔ በዓል አከበሩ።
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የአውስትራልያ፤ ብሪታኒያ፤ ፈረንሳይና የኒው ዚላንድ ሠራዊት በጋሊፖሊ በኩል ቱርክን ወረሩ።
- ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - በአዲስ አበባ አዲሱ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፹፯ ዓ/ም - በአሜሪካ የኦክላሆማ ከተማ ውስጥ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ላይ የተለቀቀ፣ በፈንጂ የተሞላ ተሽከርካሪ ሲፈነዳ በጥቂቱ ሰማንያ ሰዎች ሞተዋል። ከመቶ የማያንሱ ሰዎችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙት ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው አንድ አገር መሠረቱ። ይሄም የተዋሕዶ አገር ከሁለቱም ስም በተውጣጣው አዲሱ ስም ታንዛኒያ ተብሎ ተሰየመ።
- ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - የኡዝቤኪስታን ርዕሰ ከተማ ታሽኬንት በትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ክስተት ስትወድም ሰብ ስምንት ሺ መኖሪያ ቤቶች በመጥፋታቸው ከሦስት መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿ መኖሪያ ቢስ ሆነዋል።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ ክፉ አደጋ ተከሰተ። የዚህን አደጋ ክስተት የስካንዲናቪያ አገሮች ይፋ እስካደረጉት ድረስ የሶቪዬት ሕብረት ባለ ሥልጣናት ደፋፍነውት ነበር።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች ሃይማኖታዊ በዓላትን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር መሠረት ለማክበር መወሰናቸው ተገለጠ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእስፓኝ የሁለት ቀን ጉብኝታቸውን ጀመሩ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በብሪታኒያ በሚገኘው የሊቢያ ቋሚ ልዑካን መሥሪያ ቤት ደጅ ላይ አንዲት እንግላዚዊት የፖሊስ ባልደረባ በመገደሏ ምክንያት የብሪታኒያ መንግሥት ከሊቢያ ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነቱን ከማቋረጡም ባሻገር፣ በዛሬው ዕለት የሊቢያን ልዑካን ካገር አስወጡ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁር ዜጎችን አሳትፎ በተካሄደው ምርጫ ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - የዛምቢያ የመጀመሪያ ፕሬዚደንት የነበሩት ኬኔዝ ካውንዳ ተወለዱ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሺስት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ ከነውሽማው ክላራ ፔታቺ ጋር በቀበሌ ታጣቂዎች ተይዞ በኮሎኔል ካሌሪዶ ከተረሸነ በኋላ አደባባይ ላይ ቁልቁል ተሰቀለ።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው ቡጢኛ ሙሐመድ አሊ ወደአገሪቱ ጦር ሠራዊት ገብቶ በቪየትናምጦርነት ላይ የማገልገል ግዴታውን እንዲወጣ ቢጠየቅም አሻፈረኝ አለ። የዚያኑ ዕለት የዓለም ቻምፒዮናነቱን ማዕረግ በኒው ዮርክ የአትሌቲክ ባለ ሥልጣን ተገፈፈ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የአገራቸውን አርበኞች የመሩትና ከነጻነት በኋላም የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሆነው ለ አሥራ አንድ ዓመታት ያገለገሉት ሻርል ደጎል በፈቃድቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በስዊድን፤ ፊንላንድ እና ኖርዌይ የሚገኙ የኑክሊዬር ምርመራ ማዕከላት ያልተለመደ የጨረር ጉዳት በከላ በምድር ጠፈር ላይ እንዳገኙ ባስታወቁ በሁለተኛው ቀን የሶቪዬት ኅብረት ባለ ሥልጣናት ቸርኖቢል የሚባለው የኑክሊዬር የመብራት ኃይል ማምረቻ አደጋ እንደደረሰበት ይፋ አደረጉ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - አዶልፍ ሂትለር እና የብዙ ዘመን ውሽማው ኤቫ ብሮን በበርሊን ምሽግ ውስጥ ተጋቡ። ሂትለር አድሚራል ካርል ዶኒትዝን የሥልጣን ተተኪው እንደሆነ አስታወቀ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ‘ቺታጎንግ’ በተባለ የደቡብ-ምሥራቅ የባንግላዴሽ ግዛት ላይ የተነሳ አውሎ-ነፋስ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺ ሰዎችን ሲገድል እስከ አሥር ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች የመኖሪያ ቤታቸው ወድሞባቸዋል።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ የሚመራው የክብር ዘበኛ ሠራዊት በሱሉልታ አካባቢ የጦር ታክቲክ ልምምድ አካሄደ። ይሄንን ልምምድ ብዙዎች የታኅሣሥ ግርግር ዝግጅት እና ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደውል መሆኑን ይገምታሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ የ፪ተኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት የአስመራ ከተማን በቁጥጥሩ ስር አዋለ። የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የፖስታ እና ቴሌኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ሌተና ጄኔራል አሰፋ አየነ በአብዮታዊ ወታደሮች በዚህ ዕለት እስር ላይ ሲውሉ፤ የመከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበርን ሕገ-ወጥ አድማ ማካሄዱን ካላቆመ እንደሚዘጋ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
- ፲፯፻፺፭ ዓ/ም - የአሜሪካ ኅብረት መንግሥት የኦርሊአንስ ግዛት የተባለውን ክፍል ከፈረንሳይ ላይ በ አሥራ አምስት ሚሊዮን ዶላር ገዛ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ፥ የኅብረተ ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ አብዮት ፕሮግራምን አወጣ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - ‘ደ ሀቪላንድ-ኮሜት’ የተባለው የዓለም የመጀመሪያው የተሳፋሪ ጄት አየር-ዠበብ የመጀመሪያ በረራውን ከሎንዶን እስከ ጆሃንስበርግ ድረስ አከናወነ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ መንግሥት ኢትዮጵያን ወሮ ለአምሥት ዓመታት በጦር ኃይል ላጠቃበት በከፈለው ካሣ ገንዘብ የተገነባው የቆቃ የመብራት ኃይል ማመንጫ ግድብ በንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመረቀ።
- ፲፰፻፺፮ ዓ/ም - በአሜሪካ መንግሥት የተሠራው የፓናማ ቦይ ግንባታ ተጀመረ።
በአገራችን ታሪክ ሁለት የሐዘንና የደስታ ቀኖችን ትዘክራለች። ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም የፋሽሽት ኢጣልያ ጄነራል ባዶሊዮ በጊዚያዊ ድል አድራጊነት አዲስ አበባን ከቁጥጥሩ ሥር ያደረገበትና ነጻነታችንን ያጣንበት ዕለት ሲሆን ልክ በአምስት ዓመቱ በ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ደግሞ ንጉሠ ነገሥቱ በአርበኞች አባት እናቶቻችን ትግል፣ በእንግሊዝ እና ግብረአበሮቿ ዕርዳታ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገቡበት ዕለት ነው።
- ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ዓፄ ኃይለ ሥላሴ በድል አድራጊነት መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የጄኔራል ዊንጌት ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትየፋሺስት ኢጣልያ የራዲዮ ጣቢያ በነበሩ በተበታተኑ አሮጌ ቤቶች ውስጥ፣ ከመላው አገሪቱ ጠቅላይ ግዛቶች ለመጡ ፳፰ የመጀመሪያ ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎት መስጠቱን ጀመረ።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም የአውሮፓ ሸንጎ (The Council of Europe) ይሄንን ዕለት “የአውሮፓ ቀን” ብሎ ሰይሞታል
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በብሔራዊ የድል በዐል ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በአገሪቱ የተለኮሰውን የአብዮት እሳት በተመለከተ ከውጭ የሚራገብ ነቀርሳ እንደሆነና ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሕብረት እንዲቃወሙት ጥሪያቸውን አሰሙ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፳፭ኛ የልደት በዐሉን አከበረ።
ሚያዝያ ፳፱
- ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በፓሪስ ከተማ ለስድስት ወራት የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ አውደ ርዕይ በዚህ ዕለት ተመርቆ ሲከፈት ግንባታው ገና ያላለቀውን የ’አፌል ቅስት’ (La Tour Eiffel) ሕዝብ እስከ ሁለተኛው ፎቅ ድረስ እየወጣ መጎብኘት ጀመረ።
- ፲፱፻፯ ዓ.ም. - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የንምሣ ባሕር-ሰመጥ የጦር መርከብ፣ ሉሲታኒያ የተባለችውን የእንግሊዝ መርከብ በአየርላንድ አጠገብ አጥቅታ ስታሰምጥ ፩ሺ፩መቶ፺፰ ተሣፋሪዎች ሞቱ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ንምሣ በአውሮፓ ለስድስት ዓመታት በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሸናፊነቷን አምና የምርኮኛ ውል ፈረመች።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ።
- ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ ላይ የእንግሊዝን ቅኝ አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ስርዓተ ሲመት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተጨፍልቀው ሕይወታቸውን አጡ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ለሃያ ሰባት ዓመታት በእሥራት የቆዩት ኔልሰን ማንዴላ ለአገራቸው ደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት በመሆን ቃለ-መሐላቸውን ፈጸሙ።
- ፲፱፻፹ ዓ/ም በኢራን የኮራሳን ግዛት ውስጥ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ አንድ ሺ አምሥት መት ስድሳ ሰባት ሰዎችን ሲገድል፣ ሁለት ሺ ሦስት መቶ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ሴባዎች ሆነዋል። ወደ አሥራ አምሥት ሺ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች ሲወድሙ አምሣ ሺ የሚሆኑ ዜጎች የመኖሪያ ቤት አልባ ሆነዋል
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ሁለቱ ጀርመናውያን ተሽከርካሪ አምራቾች፣ ጎትሊብ ዴይምለር እና ካርል ቤንዝ ኩባንያዎቻቸውን አዋሕደው አዲሱን የመርሴዲስ-ቤንዝ (Mercedes-Benz) ኩባንያ መሠረቱ።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም- የብሪታኒያ የቅኝ ግዛቶች ሚኒስትር የምዕራብ አፍሪቃዋ ጎልድ ኮስት (በኋላ ጋና) ነጻነቷን እንደምትሰጥ መወሰኑን ለሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ አስታወቀ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጣልቃ ገቦች በአገሪቱ ጉዳይ ውስጥ እየገቡ አስቸግረዋል በሚል መነሻ የፈረንሳይን፤ አሜሪካን፤ ግብጽን፤ የሶቪዬት ሕብረትን፤ የብሪታኒያን እና የዩጎዝላቪያን የልዑካን አለቆች ሰብስበው አነጋገሩ። በማግሥቱ ይፋ የተደረገው ጽሑፋዊ ቃለ-ጉባኤ አምባሳደሮቹ የተጠሩት «የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት በብርቱ እንደሚቃወም እና በኢትዮጵያ ግዛትና ሉዐላዊነት ላይ የሚሰነዘሩትን ማናቸውንም እርምጃዎች ለመከላከል ቆራጥ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው።» ይላል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከግብጽ ፕሬዚደንት ሳዳት ጋር ለውይይት ወደካይሮ ሲጓዙ፣ እግረ መንገዳቸውን ካርቱም ላይ አርፈው ከፕሬዚደንት ኒሜሪ ጋር ተለወያዩ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የዮርዳኖስ ንጉሥ ሁሴን ለአራት ቀን ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
- ፳፻ ዓ/ም በሲቹዋን፣ ቻይና የተከሰተው ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ከ፷፱ ሺ በላይ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፲፰፻፸፫ ዓ/ም - የፈረንሳይ ቅኝ ገዝዎች የተቃራኒ አመጸኞች ቡድን ከቱኒዚያ ተነስቶ በግዛታቸው አልጄሪያ ጥቃት አድርሷል በሚል መነሻ ቱኒዚያን ከወረሩ በኋላ በሰንደቅ ዓላማቸው ጥላ ሥር እንድትስተዳደር አስገደዷት።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች አድማ መቱ።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ ብዙ ሺ ሕዝብ በተሰበሰበበት በ’ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ’ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለው ወደህክምና ተወሰዱ።
- ፲፱፻፺ ዓ/ም - ሕንድ ግንቦት ፫ ቀን ያፈነዳቸውን ሦስት የኑክሊዬር ቦንቦች አስከትላ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት ቦንቦች አፈነዳች። በዚህ ምክንያት የአሜሪካ እና የጃፓን መንግሥታት በሕንድ ላይ የምጣኔ ኃብት ዕቀባ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - እስራኤል ነጻ እና ሉዐላዊ አገር ተብላ ስትታወጅ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ወዲያውኑ ጎረቤት የአረብ አገራት አዲሲቱን አገር በጦር ኃይል ሲያጠቋት የ፲፱፻፵ው የአረብ እና እስራኤል ጦርነት ተጀመረ።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም የግብጽ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናስር እና የሶቪዬት ሕብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቼቭ በአስዋን ግድብ ሥራ የዓባይን ወንዝ ፈሰሳ የመለወጥ የመጀመሪያ ምዕራፍ በተዘጋጀው ፈንጂ በአንድነት አፈነዱ። በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢራቅ ፕሬዚደንት አሪፍ እና የየመን ፕሬዚደንት ሳላል ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም - ታላቋ ብሪታኒያ በፍልስጥኤም ላይ የነበራት የአስተዳደር ሥልጣን ሲያከትም፤ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ፣ [ሊባኖስ]]፣ ሶርያ፣ ኢራቅ እና ሳውዲ አረቢያ ተባብረው አዲስ የተመሠረተችውን እስራኤልን ወረሩ። ይኼም ድርጊት የመጀመሪያውን የአረብ እና እስራኤል ጦርነት ለኮሰ።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን በሀገራቸው ጦር ሠራዊት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አና ሄይስ (Anna Mae Hays) እና ኤልሣበጥ ሆይሲንግቶን(Elizabeth P. Hoisington) የተባሉ ሁለት ሴት መኮንኖችን ወደጄነራልነት ማዕርግ አሳደጉ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ፈረንሳዊቷ ኢዲዝ ክሬሶን (Édith Cresson) የሀገራቸው የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ተወለዱ።
- ፲፱፻፺ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት በተወለዱ ፷ ዓመት እድሜያቸው አረፉ።
- ፲፱፻፵፮ ዓ/ም - የአሜሪካ የበላይ ፍርድ ቤት (Supreme Court) በአገሪቱ ይካሄድ የነበረውን በቀለም ልዩነት የተመሠረተ የትምህርት አቋም ፀረ-ሕገ-መንግሥት ነው ብሎ ፈረደ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የአዲስ አበባው ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የተመሠረተበትን ፳፭ኛ ዓመት በዓል ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተገኙበት አከበረ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - በሎረንት ካቢላ የተመራው ሠራዊት የዛይር ርዕሰ ከተማ ኪንሻሳ ሲገባ የአገሪቱም ስም ተለውጦ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተባለች።
- ፲፱፻፲፪ ዓ/ም - የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ (የቀድሞው ካሮል ዮሴፍ ዎይቲላ) በፖላንድ ክራካው ከተማ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ‘ፈገግተኛው ቡዳ’ በሚል መርሀ-ግብር ሕንድ የመጀመሪያዋን የኑክሊዬር ቦምብ በስኬታማነት አፈነዳች። በዚህ ተግባር በዓለም ስድስተኛዋ ባለ ኑክሊዬር ኃይል ሆነች።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ሰሜናዊ ሶማሊያ ከዋናው አገር ተገንጥላ ነጻነቷን አወጀች። ሆኖም ይሄንን ድርጊት ማናቸውም የዓለም ቤተሰብ ዕውቀት አልሰጠውም።
- ፲፯፻፺፮ ዓ/ም - አምባገነኑ የፈረንሳይመሪ ናፖሌዮን ቦናፓርት እራሱን በእራሱ የአገሪቱ ቄሳር (Emperor) ማድረጉን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኤርትራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያጸደቀውን ሕገ-መንግሥቱን በመለወጥ አገሪቱን ከ’ኤርትራ መንግሥት’ ወደ ‘የ ኤርትራ አስተዳደር’ በመለወጥ ወደፊት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለማድረግ የሚያስችላትን ውሳኔ አጸደቀ።
- ፲፬፻፹፮ ዓ/ም - ዓፄ እስክንድር በነገሡ በ፲፮ ዓመታቸው አረፉና በደብረ ወርቅ ተቀበሩ። ሥልጣነ መንግሥታቸውም ወደ ፯ ዓመቱ ልጃቸው ዓምደ ጽዮን ሣልሳዊ ተዘዋወረ። ሆኖም ዓምደ ጽዮን በነገሡ በ፯ ወራቸው ድንገት ስለሞቱ አልጋው ወደ አባታቸው ወንድም አጼ ናዖድ ተላልፏል።
- ፲፯፻፲፫ ዓ/ም - አፄ ዳዊት ሣልሳዊ በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፰፻፺፮ ዓ/ም - የዓለም እግር ኳስ ማኅበር ፊፋ (FIFA) ፓሪስ ከተማ ላይ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት (አሁን አርሲ) እንደራሴ ሆነው የተሾሙትን አቶ ተስፋ ቡሸን የጠቅላይ ግዛቱ ሕዝብ አባሮ አስወጣቸው።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የኢሕዲሪ (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ) ፕሬዚዳንትና የኢሠፓ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) ዋና ጸሐፊ የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገር ጥለው በመኮብለል ወደዚምባብዌ ተሰደዱ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም በሰሜናዊ አልጄሪያ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎችን አጥፍቷል።
ግንቦት ፲፬ ቀን
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በዓለም የመሬት እንቅጥቅጥን ኃይል መመተር ከተጀመረ ጀምሮ ከሁሉም የበለጠ የሆነው በዚህ ዕለት በደቡብ ቺሌ የተከሰተው የመሬት ነውጥ ነው።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበት አሥረኛው ዓመት በዓል የሁለት ቀን ክብር ተጀመረ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ፴፬ የእስራኤል አየር ዠበቦች ፲፬ሺ ፫፻፳፭ የቤተ-እስራኤል ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ፈላሻዎችን በ፴፮ ሰዓት ውስጥ ጭነው እስራኤል ገቡ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የ፴፪ ነጻ የአፍሪቃ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን መሠረቱ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ፤ በከተማው ወጥቶ-እብሶች እና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሱ። በዚህም ምክንያት አሥር ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ተዘጉ።
- ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - በሲዬራ ሌዎን፣ በሻምበል ጆኒ ፖል ኮሮማ የተመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚደንት አህመድ ቴጃን ካባህን ከሥልጣን አወረደ።
- ፲፯፻፲፫ ዓ/ም - ከወህኒ በወረዱ በሁለተኛው ቀን የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ልጅ አፄ በካፋ ጎንደር ላይ በጳጳሱ አባ ክርስቶዶሉ እና እጨጌ ተክለ ሃይማኖት ተቀብተው ነገሡ።
- ፲፱፻ ዓ/ም - ለብሪታኒያዊው ሥራ-ፈጣሪ ዊሊያም ኖክስ ዳርሲ የሚሠሩ መሐንዲሶች ‘ማስጂዲ ሱሌይማን’ በተባለ በአሁኗ ኢራን የሚገኝ ስፍራ ላይ በመካከለኛው ምሥራቅ የመጀመሪያውን ትልቅ የነዳጅ ክምችት አገኙ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የኢንዱስትሪ እና የቴክኒክ ምርቶች አውደ ርዕይ አዲስ አበባ ላይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አሥረኛው የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ተከፈተ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - የአውሮፓ ሰንደቅ ዓላማ በአውሮፓ ኅብረት አባላት ጸደቀ።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - በኒው ዮርክ ከተማ የ፩ሺ፵፮ ጫማ (፫መቶ ፲፱ ሜትር) ቁመት ያለው የ’ክራይዝለር’ ሕንፃ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት ጊንዳ ውስጥ በሉተራን ሚሲዮን ሆስፒታል ውስጥ የሚሠራ ዶክቶርን የመጥለፍ ሙከራ ሲያደርጉ አንዲት አስታማሚ (ነርስ) ተገደለች።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች በአድማ ሥራቸውን አቆሙ።
- ፲፰፻፹፯ ዓ/ም - የአየርላንድ ተወላጁ ደራሲና ባለቅኔው ኦስካር ዋይልድ (Oscar Wilde) በግብረ ሰዶማዊነት ተፈርዶበት ታሰረ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት የሚኒስትሮችን ለውጥ ይፋ አደረገ። ከነዚህም አንዱ የአገር ግዛት ሚኒስትር የነበሩትን ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴን ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዛወር ያካትታል።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ኢሕአዴግ በዘመቻ ወጋገን አዲስ አበባን ተቆጣጠረ። አቶ መለስ ዜናዊ የሽግግሩ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፮፻፺፭ ዓ/ም - የሩሲያ ቄሳር ታላቁ ጴጥሮስ (Tsar Peter the Great) በስሙ የሠየማትን የፔትሮግራድን ከተማ ቆረቆረ።
- ፲፰፻፺፪ ዓ/ም - የቻድ ርዕሰ ከተማ ንጃሜና በፈረንሳዩ አዛዥ ኤሚል ጀንቲል ፎርት ላሚ ተብላ ተቆረቆረች።
- ፲፱፻፶፰ - ዓ/ም የቀድሞው የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤባሪስቴ ኪምባ እና ሌሎችም የፖለቲካ ሰዎች በአምባገነኑ ፕሬዚደንት ዮሴፍ ሞቡቱ ትዕዛዝ በሕዝብ ፊት በሞት ተቀጡ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽ ቆስቋሽነት የተሠየመው የሙስና እና የሥልጣን በደል መርማሪ ሸንጎ ሥራውን የሚመራበት ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ።
- ፲፱፻፯ ዓ/ም - ልጅ ኢያሱ አባታቸውን ራስ ሚካኤልን ደሴ ላይ ንጉሠ ወሎ ወ ትግሬ ብለው አነገሧቸው።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - በዛሬይቷ ፓኪስታን፣ ኬታ በሚባል ሥፍራ የተከሰተ ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ የ ፵ ሺ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።
- ፲፯፻፹፬ ዓ/ም - ኬንታኪ፣ የአሜሪካ ኅብረት ፲፭ኛዋ አባል ሆነች።
- ፲፯፻፹፰ ዓ/ም - ሚሲሲፒ፣ የአሜሪካ ኅብረት ፲፮ኛዋ አባል ሆነች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባ፦ አስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከዘጠኝ ወራት በኋላ ነጻነቷን የተቀዳጀችው ኬንያ፣ በዛሬው ዕለት እራሷን የማስተዳደር መብት ተፈቀደላት። ይሄንን ዕለት በየዓመቱ “የማንዳራካ ቀን” በሚል ስያሜ ኬንያ ታከብረዋለች።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - ‘ሲ. ኤን. ኤን.’ (CNN) የተባለው የዜና ማሠራጫ ድርጅት ሥራውን ጀመረ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - የኔፓል አልጋ ወራሽ ልዑል ዲፔንድራ አባታቸውን ንጉሥ ቢሬንድራን፤ እናታቸውን ንግሥት አይስዋርያን እና ሌሎችንም ንጉሣዊ ቤተ ሰባቸውን ረሽነው ከገደሉ በኋላ እራሳቸውንም በጥይት አጠፉ።
- ፲፯፻፹፰ ዓ/ም - አመድ ከሰማይ ዘነበ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዎቹን አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት (አቡነ አብርሓም - የጎንደር እና የጎጃም፤ አቡነ ይስሐቅ - የትግሬ እና የስሜን፤ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ እና የላስታ፤ አቡነ ሚካኤል - የኢሉባቡር እና የምዕራብ ኢትዮጵያ) ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስ)ጋር ካይሮ ላይ ተቀብተው ተሾሙ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ በዚህ ዕለት ቅብዐ ቅዱስ ተቀብተው ከአባታቸው ከንጉሥ ጊዮርጊስ ሳድሳዊ የወረሱትን ዘውድ ጫኑ። የዘውዱ ሥነ ሥርዓት በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የራዲዮ አድማጮች የተሠራጨ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያም ጊዜ በአዲሱ የትዕይንተ መሳታዋት (television) ታይቷል።
- ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ሕዝብ በጣለው የድምጽ ምርጫ የንጉዛታዊ ሥርዓትን ትቶ አገሪቱ የሪፑብሊካዊ አስተዳደር እንድትከተል አደረገ። የቀድሞው ንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ አገር ለቅቀው ተሰደዱ።
- ፲፯፻፷፭ ዓ/ም - የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ በዚህ ዕለት አርፈው በቁስቋም ደብረ ጸሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የ’ኤየር ፍራንስ’ ‘ቦይንግ’ ፯፻፯ አየር ዠበብ ከፓሪስ ኦርሊ ማረፊያ ተነስቶ ወደ አትላንታ ለመብረር ሲነሳ በደረሰበት አደጋ ፻፴ መንገደኞችና የዓየር መንገዱ ባልደረቦች ሞተዋል።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የአሜሪካው ‘ኖርዝ ዌስት ኤየርላይንስ’ (Northwest Airlines) ዲ-ሲ-፯ አየር ዠበብ በረራ በሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ ወድቆ ሲሰምጥ ፻፩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኮንኮርድ አየር ዠበብ አምሳል የተሠራው የሶቪዬት ቱፖሌቭ ቲ-ዩ-፻፵፬ (Tupolev Tu-144) ፈረንሳይ ላይ በደረሰበት የበረራ አደጋ ሲከሰከስ ፲፬ ሰዎች ሞተዋል።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አካላት የነበሩት ሰርቢያ እና ሞንቴኔግሮ የውሕደት ስምምነታቸውን በሞንቴኔግሮ የሉዐላዊነት አዋጅ ምክንያት ሰረዙ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሊዩቢቺክ የሚመራ የዩጎዝላቪያ ወታደራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር አዲስ አበባ ላይ ያካሄደውን የአራት ቀን ውይይት ጀመረ።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በቻይና ርዕሰ ከተማ ቤይጂንግ በሚገኘው የቲያናንመን አደባባይ ለብዙ ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው ሕዝባዊ የዴሞክራሲ ዓመጽ፣ በዚህ ዕለት በጦር ሠራዊት የታንክ እና መሣሪያ ኃይል ተሰብሮ ሲያከትም በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎችም በወታደሮቹ ተረሽነው ሞተዋል።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የእስራኤል አየር ኃይል የግብጽን፤ የዮርዳኖስን እና የሶርያን አየር ኃይል በቦምብ ሲደበድብ “የመካከለኛው ምሥራቅ የስድስት ቀን ጦርነት” ተቀጣጠለ። በዚህ ጥቃት ግብጽ አራት መቶ ያህል የጦር አየር ዠበቦች ሲወድሙባት፤ የዮርዳኖስ እና የሶርያ አየር ኃይሎች ከሞላ ጎደል ተደምስሰዋል።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የፕሬዚደንት ምርጫ የዴሞክራት ቡድን እጩ የነበሩት ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ በነፍሰ ገዳይ ጥይት ሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ ተመተው ነፍሳቸውን ለማዳን የሕክምና እርዳታ ሲቀበሉ አደሩ። ዳሩ ግን በማግሥቱ ግንቦት ፳፱ ቀን ሕይወታቸው አልፋለች።
- ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በአይስላንድ የሚገኘው ላኪ የተባለው ተራራ በእሳተ ገሞራ ፈንድቶ ከ ፱ ሺ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በአገሪቱ ላይ የሰባት ዓመት ረሀብ አስከተለ።
- ፲፰፻፭ ዓ/ም - የሸዋው መርዕድ አዝማች ወሰን ሰገድ አርፈው በቁንዲ ጊዮርጊስ ተቀበሩ። ልጃቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አልጋውን ወረሱ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - በኢጣልያ አስተናጋጅነት የተካሄደው ሁለተኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውድድር የመጨረሻው ጨዋታ በኢጣልያ እና ቼኮዝሎቫኪያ ቡድኖች ግጥሚያ ሲሆን ኢጣልያ ፪ ለ ፩ አሸንፋ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፴፪ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት ከደብረ ወርቅ ብዙ ጉዋዝና መሣሪያ ጭኖ ወደ ቢቸና ሲጓዝ የነበላይ ዘለቀ አርበኞች ገጥመውት ከፍተኛ ውጊያ ተደርጎ አርበኞቹ ድል አድርገውት ብዙ መሣሪያ ማረኩ።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - ለአሜሪካ ጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ የነበሩትን ማርቲን ሉተር ኪንግን የገደለው ጄምስ ኧርል ሬይ በሂዝሮው የሎንዶን አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ ተያዘ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የዘጠና ሰባትን ምርጫ አስከትሎ በተፋፋመው ዓመጽ የኢሕአዴግ ሠራዊት በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ የጅምላ ፍጅት ያደረገበት ዕለት ነው።
ሰኔ ፪ ቀን
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የወባን በሽታ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት፣ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥትና የአሜሪካ መንግሥት ስምምነት ተፈራረሙ።.
- ፲፰፻፷፪ ዓ/ም - እንግሊዛዊው ደራሲ ቻርልስ ዲክንስ (Charles Dickens) በዚህ ዕለት ሞተ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ከውጭ የተገኘ ገንዘብ በመጠቀም የመንግሥትን ሥርዓት ለማናጋት ሽብርተኝነት አካሂዳችኋል ብሎ የወነጀላቸውን፤ ታምራት ከበደን፤ሄኖክ ክፍሌን እና ሌሎችንም የሰባት ዓመት እስራት ፍርድ ፈረደባቸው።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የደቡብ አፍሪቃው ብሔራዊ ሸንጎ (African National Congress) የፖለቲካ ቡድን፣ በእስራት ላይ የነበሩትን የመሪውን፣ የኔልሰን ማንዴላን የትጥቅ ትግል ጥሪ ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፴ ዓ/ም - በሁለተኛው የቻይና እና የጃፓን ጦርነት፤ የቻይና መንግሥት የጃፓኖቹን ግፊት ለመግታት በሚል ዓላማ የ’ቢጫ ወንዝ’ን ግድቦች ሲያፈርስ የተከሰተው ትልቅ ጎርፍ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦቹን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - አሥራ ስድስተኛው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአለም አቀፍ የልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ለግብርና ልማት የሚውል ሃያ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር (US $21 million) አጸደቀ
- ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በቻይና የሲቹዋን ግዛት ውስጥ ከአሥር ቀናት በፊት የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ምክንያት በድንጋይና አፈር ናዳ ተገድቦ የነበረው ‘ዳዱ’ የተባለው ወንዝ ይሄንኑ ግድብ ጥሶ ሲሄድ መቶ ሺ ያህል ሰዎች በጎርፉ ተጥለቅልቀው ሞተዋል።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፑብሊክ የቀድሞው አምባ-ገነን ‘ቄሳር’፣ ዣን ቤደል ቦካሳ በአሥራ ሦስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ጊዜያት ለፈጸሟቸው ወንጀሎች የሞት ቅጣት ተፈረደባቸው።
- ፲፰፻፳፪ ዓ/ም - ፴፬ ሺ የፈረንሳይ የወረራ ሠራዊት ከዛሬይቱ አልጄርስ በስተምዕራብ በምትገኘው ‘ሲዲ ፈሩሽ’ በተባለ ወደብ ላይ አርፈው አልጄሪያን በቅኝ ግዞት ያዙ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - የናዚያዊ ጀርመን መሪ አዶልፍ ሂትለር እና የፋሺስታዊ ኢጣልያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ በኢጣልያን ከተማ ቬኒስ ላይ ተገናኙ። ከግንኝነታቸው በኋላ ሙሶሊኒ በሂትለር ላይ በማሾፍ “ኮስማና ሞኝ ጦጣ” ብሎታል። (“ጀበናዋ ድስትን ሻንቅላ ብላ ሰደበች” እንደሚሉ!)
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የደቡብ ኮሪያ ተወላጅ የሆኑት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከሰኔ ፮ - ፲፯ የተካሄደው ሁለተኛው የነፃ አፍሪቃ አገሮች ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ሲከፈት ከሁለት መቶ ሃምሣ በላይ ልዑካን እና ተመልካቾች ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የንግድ ሚኒስትር አቶከተማ ይፍሩ የተመራ የሰባት ኢትዮጵያውያን ልዑክ ለአሥራ ሁለት ቀን የንግድ ውይይት ወደቻይና መዲና ቤይጂንግ አመራ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - የኢጣልያ መንግሥት ግንቦት ፭ ቀን ፲፱፻፸፫ ዓ/ም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስን በጥይት ያቆሰለውን ቱርክ፣ ሜህመት አሊ አጅካን (Mehmet Ali Agca) በምኅረት ከእስር ለቀቀው።
- ፲፱፻፳ ዓ/ም - የአርጀንቲና ተወላጁ የአብዮት መሪ ኤርኔስቶ ‘ቼ’ ጌቫራ በዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፳ ዓ/ም - የዕመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት እናት ኤመሊን በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የስዊድን መንግሥት በአዲስ አበባ የመሥፍነ ሐረር መታሰቢያ ሆስፒታል (አሁን ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል) እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ማዕከል ማስከፈቻ የሚሆን የአምሥት ነጥብ አራት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ብድር ለመስጠት ስምምነት ፈረመ።
ሰኔ ፰ ቀን
- ፲፯፻፷፮ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ሰሜን አሜሪካዊ ቅኝ ግዛቶች መኻል የ ሮድ ደሴት (Rhode Island) የባርነትን ንግድ በማቆም የመጀመሪያዋ ሆነች።
- ፲፰፻፳፰ ዓ/ም - አርካንሳስ የአሜሪካ ኅብረት ሃያ አምሥተኛ አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለ አፍሪቃ አንድነት ድርጅት ጉባዔ ለመወያየት ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ )አሁን ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ) እና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ አመሩ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የሃያ ስድስት ዓመቷ መቶ ዓለቃ ቫለንቲና ተሬሽኮቫ (Valentina Tereshkova) በሶቪዬት ኅብረት የጠፈር መንኮራኩር ‘ቮስቶክ ስድስተኛ’ ወደጠፈር ስትተኮስ በዓለም የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ሶዌቶ ከተማ ውስጥ በተካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ፣ በፖሊሶችና ወጣት ጥቁሮች መኻል የተከተለው ግጭት ምክንያት አሥራ ሁለት ሰዎች ሞተዋል።
ሰኔ ፲፩ ቀን
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኡጋንዳው አምባ-ገነን ፕሬዚደንት ኢዲ አሚን እግረ መንገዳቸውን አዲስ አበባ ላይ አርፈው ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ተወያዩ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ረብሻ፣ ደብረ ዘይት ላይ ያመጹት የአየር ኃይል አባላት ለማረጋጋት ከተላከው የአየር ወለድ ሠራዊት ጋር ሲጋጩ ከሁለቱም ወገን ሰዎች ሞተዋል።
- 1780- በየፈረንሳይ አብዮት መፈንዳት ምክንያት የተወሰኑ የፈረንሳይ ዜጎጅ በቴኒስ መጫዎቻ ሜዳዎች ተሰብስበው አዲስ ሕገ መንግስት ሳይጸድቅ እንደማይነቃነቁ አስታዎቁ።
- 1854- የመጀመሪያ የሮማኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ባርቡ ካታርጉ፣ የህዝቡን የመሰብሰብ መብት በማገዱ ተገደለ።
- 2001- በኢራን የተቃውሞ ሰልፍ ነዳ አጋ-ሶልጣን የተሰኘች ሴት ስትገደል እሚያሳየው ቪዲዮ በአለም ተሰራጨ። የአንድ ግለሰብ አሟሟት በብዙ ህዝብ ሲታይ ይህ ቀደምቱ ነው ተባለ።
- 225ዓ.ዓ. – ሁለተኛው የፑኒክ ጦርነት ተካሂዶ በሃኒባል የተመራው የካርቴጂያን ጦር ሮማውያንን አሸነፈ።
- 1940 – ማንቸስተር ስሞል ስኬል ኤክስፐሪመንታል ማሽን የተሰኘው፣ ትዕዛዛትን በማጠራቀሚ እሚሰራ ኮምፒዩተር ስራ ላይ ዋለ።
- 1956 – ሶስት የሲቪል መብት ታጋዮች በኩ ክለክስ ክላን የነጭ የዘር የበላይነት አራማጆች አሜሪካ ውስጥ ፊላደልፊያ፣ ሚሲሲፒ ታንቀው ተገደሉ።
- 1625 – ጋሊልዮ ጋሊሊ መሬት በጸሐይ ዙሪያ እንደምትሽከረከር የሚለውን የምርምር ውጤቱን እንዲክድ በሮማን ካቶሊክ ቤ/ክ ተገደደ።
- 1799 – የብሪታኒያ ጦር መርከብ የአሜሪካን መርከብ ተከታትሎ አጠቃ። ለዚህ ምክንያቱ በአሜሪካው መርከብ ላይ የብሪታኒያ ጦርን ከድተው የኮብለሉ ወታደሮች አሉ በማለት ነበር።
- 1994 – 6.5 Mw የሚለካ የመሬት እንቅጥቀጥ ሰሜን ምዕራብ ኢራንን በመምታቱ 261 ሰዎች ሲሞቱ 1300 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የየኢራን መንግስት ለዚህ አደጋ ፈጣን ምላሽ ባለማድረጉ የህዝብ ቁጣን አስነስቶ ነበር።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የሱዳን ፕሬዚደንት ጃፋር አል ኒሜሪ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን ሊቀ መንበር የናይጄሪያውን ፕሬዚደንት ጄኔራል ያኩቡ ጋዋንን በመወከል በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መኻል ስለተነሳው ግጭት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የሁለት ቀን ውይይት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም ሕንዳዊ የሲክ አመጸኛ ቡድን ከሞንትሪያል ተነስቶ በሎንዶን በኩል ወደ ዴልሂ በረራ ላይ የነበረውን የሕንድ አየር መንገድ አውሮፕላን በድብቅ በጫኑት ቦምብ ፍንዳታ አየርላንድ አጠገብ ባህር ውስጥ ሲሰምጥ ሦስት መቶ ሃያ ዘጠኙም ተሣፋሪዎች ሞተዋል።
- ፲፮፻፲፮ ዓ/ም - ዠሮም ሎቦ እና ሌሎችም የብርቱጋል ሚሲዮናዊያን ከደንቀዝ በተነሱ በስድስተኛው ቀን በቀድሞ ስሟ “ማይ ጓጓ” (የውሐ ጩኸት) ከምትባለው በኋላ ብርቱጋሎች ለአቡነፍሬምናጦስ ማስታወሻ ከአድዋ አጠገብ ‘ፍሪሞና’ ብለው ከሰየሟት ሥፍራ ደረሱ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋጋው በ፳፮ ሚሊዮን ፮፻፴፭ ሺ ፫፻፸፰ የእንግሊዝ ፓውንድ (£26,635,378.25) የተገመተ እና በጠቅላላው ሚዛኑ ፲፬ ሺ ፻፴፬ ኪሎ ከ ፭፻፸፮ ግራም ያልተጣራ ወርቅ በድብቅ ጭኖ በአቴና በኩል ሎንዶን ገብቷል።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -የኤርትራ ነፃነት ግንባር መጋቢት ፲፯ ቀን ኤርትራ ውስጥ ከጠለፋቸው አምስት የ’ቴናኮ’ (Tennaco) ነዳጅ ምርመራ ባልደረቦች መኻል አንድ ካናዳዊ የሄሊኮፕተር አብራሪ በዚህ ዕለት ለቀቁ።
- 1932 – ሁለተኛው የአለም ጦርነት፣ 200፣000 የአላይድ ቡድን ወታደሮች የፈረንሳይን ባሕር ጠረፍ ለቀው ወጡ።
- 2001 – ታዋቂው ዘፋኝ ማይክል ጃክሰን አረፈ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአሜሪካ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት መላክተኛ ብላታ ኤፍሬም ተወልደ መድኅን በሳን ፍራንሲስኮ ከተማ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምሥረታ ሥነ ሥርዓት ላይ አገራቸውን በመወከል የቃል ኪዳኑን ሰነድ ፈረሙ።
ሰኔ ፳'
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም- ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመሠረቱት የጥቁር አንበሳ ቡድን በነቀምት አካባቢ ቆሞ የነበረ የኢጣልያ የጦር አየር ዠበብ አጥቅተው በእሳት አወደሙት።
- ፲፱፻፮ ዓ/ም - የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽ፣ አውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድ በዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው።የአውስትሪያው ልዑል ‘ፍራንዝ ፈርዲናንድ’ እና ባለቤታቸው የሳራዬቮን ከተማ በመጎብኘት ላይ ሳሉ በነፍሰ ገዳይ እጅ ሕይወታቸውን አጡ። ይኼ ድርጊት የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት መንስዔ እንደነበር በታሪክ ተዘግቧል።
- ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተቀናቃኞች፤ በአንድ በኩል አለማኝያ እና በሌላው ወገን የቃል ኪዳን አገራት የጦርነቱን ፍጻሜ ስምምነት የቨርሳይ ውል በዚህ ዕለት ተፈራረሙ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ካይሮ ላይ በተካሄደ ሥርዓተ-ሢመት በቅብጡ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ ተቅብተው የፓትርያርክነቱን ዘውድ ደፉ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታኒያ ዋና መላክተኛ (‘አምባሳዶር’) አላን ካምቤል (ALAN CAMPBELL ) በአገራቸው ስም፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለምግብ ዋስትና ዓላማ የተዘጋጀውን የ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ብር (£400,000) የለገሣ ውል ፈረሙ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም የሴይሼልስ ሪፑብሊክ ነፃነቷን ከብሪታንያ ተቀዳጀች። * *
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ገላውዴዎስ በዘመኑ የካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን <<ኦሪታዊ’ ናት>> እያሉ ስም የማጥፋት ዘመቻቸውን በመከላከል፣ ዳሞት ላይ የተጻፈ የሃይማኖቱን እውነትነት የሚገልጽ ውሳኔ ፈረመ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የፋሺስታዊ ኢጣልያ ሠራዊት ኢትዮጵያን በግፍ ወሮ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ እና ንጉሠ ነገሥቷ ከተሰደዱ በኋላ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዠኔቭ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ማኅበር ላይ ተገኝተው የኢጣልያን ግፈኝነትና የኢትዮጵያን አቤቱታ አሰሙ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኮንጎ ሪፑብሊክ (ኮንጎ ሊዮፖልድቪል/የቤልጂግ ኮንጎ) ከቤልጂግ ቅኝ ግዛትነት ነፃነቷን አወጀች። ዮሴፍ ካዛቩቡ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።
- ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - አባ ፍራንሲስኮ ፓላው የተባለ የካቶሊክ ሚሲዮናዊ እና መቶ-ዓለቃ ሆሴ ዮአኪን ሞራጋ የተባሉ የእስፓኝ አቅኚዎች የዛሬዋ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ በተቆረቆረችበት ሥፍራ ላይ የሚሲዮናዊ ቤት አቆሙ።
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተወለዱ በ፸፪ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አርፈው ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ጋና በዚህ ዕለት ሪፑብሊክ ስትሆን ክዋሜ ንክሩማ ፕሬዚደንት ተብለው ንግሥት ኤልሣቤጥ (ዳግማዊት)ን በመተካት የአገሪቱ ርዕሰ-ብሔር ሆኑ።
- 1644 – በየእንግሊዝ እርስ በርስ ጦርነት፣ የስኮትላንድ እና እንግሊዝ ፓርላመንታሪያኖች በማበር ሮያሊስቶችን ተዋግተው አሸነፉ።
- 1949 – የበረራ ጀማሪዎች አሜሊያ ኸርሃርት እና ፍሬድ ኑናን አለምን ለመዞር ሲሞክሩ ሰላማዊ ውቅያኖስ ሲደርሱ ጠፉ።
- 1989 – የታይላንድ ገንዘብ የሆነው ባህት በግማሽ ሲገሽብ የእስያ ንዋያዊ ቀውስ ተጀመረ።
ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 26 ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 27 ሰኔ ፳፰ ቀን
- ፲፰፻፸፰ ዓ/ም - የፈረንሳይ ሕዝብ በዚህ በመቶ አሥረኛው የነፃነት በዓላቸው ዕለት ለአሜሪካ ሕዝብ ዛሬ በኒው ዮርክ ወደብ የምትገኘውን 'የሀርነት ሐውልት' (statue of liberty) ስጦታ አበረከቱ።
ሰኔ ፳፱ ቀን
- ፲፯፻፸፯ ዓ/ም - በየአሜሪካ ሕብረት መንግሥት ዶላር የሕብረቱ ብሔራዊ ገንዘብ እንዲሆን በስምምነት ተመረጠ።
- ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ሉዊ ፓስተር የተባለው የፈረንሳይ ዜጋ በእብድ ውሻ በተለከፈው ጆሴፍ ማይስተር በተባለ ልጅ ላይ የውሻ ልክፍት መከላከያ ክትባቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተነ።
- ፲፱፻፲፭ ዓ/ም - የሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ (socialist) ሪፐብሊክ በዛሬው ዕለት ተመሠረተ።
- ፲፱፻፴፰ ዓ.ም - አርባ ሦስተኛው የየአሜሪካ ሕብረት መንግሥት ፕሬዚደንት ጆርጅ ዎከር ቡሽ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - የሩሲያው ተወላጅ ሚካኤል ካላሽኒኮቭ በሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ (socialist) ሪፐብሊክ ፣ የፈጠረው ክላሽ (ካላሽኒኮቭ) ጠብመንጃ፣ ኤ.ኬ. 47 (AK 47) ሞዴል መሠራት ጀመረ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከሌሎች የአፍሪቃ አገሮች በመነጨ ተጽዕኖ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያን እና የብርቱጋልን ጥንታዊ ግንኙነት ለማቋረጥ ተገደዱ።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - ማላዊ ከዩናይትድ ኪንግደም ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - ማላዊ ሪፑብሊክ ሆነች። ሄስቲንግስ ካሙዙ ባንዳ የመጀመሪያው ፕረዚደንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ.ም - በሕንድ ውቅያኖስ የሚገኙት የቆሞሮስ ደሴቶች ሕብረት ነጻነቷን ከፈረንሳይ ተቀዳጀች።
- ፲፰፻፶፯ ዓ/ም - ፕሬዚደንት አብራሃም ሊንከንን ከገደላቸው ጆን ዊልክስ ቡዝ ጋር በግድያው ለመተባበራቸው በሕግ የተፈረደባቸው አራት ሰዎች ዋሺንግተን ዲ.ሲ ላይ በስቅላት ተቀጡ።
ሐምሌ
ለማስተካከል፲፱፻፵፪ ዓ/ም የአሜሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት ሃሪ ኤስ ትሩማን በኮርያ ጦርነት ላይ ለተሠማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ብለው ጄነራል ዳግላስ ማካርተርን ሰየሙ። በጦርነቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላትም በማሕበሩ ስር ተሳትፈዋል።
፲፱፻፶፰ ዓ/ም የቡሩንዲው ንጉሥ ምዋምቡትሳ ፬ኛ ባንጊሪሴንግ በልጃቸው በልዑል ቻርልስ ንዲዚ ተገለበጡ።
፲፱፻፸፰ ዓ/ም የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሕበር ዋና ፀሐፊ እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የጦር መኮንን ነበሩ የተባሉት ኩርት ቫልዳይም የአውስትሪያ ፕሬዚደንት ሆነው የቃለ መሃላ ሥርዐት ፈጸሙ።
፲፱፻፺፭ አንድ መቶ አሥራ ስድስት መንገደኞችን የጫነው የሱዳን አየር መንገድ (Boeing 737-200) አውሮፕላን ፖርት ሱዳን በአደጋ ሲከሰከስ አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም። ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሠላሳ አንድ ኢትዮጵያውያን እና የሃምሳ ዘጠኝ ሌላ ዜጎች ሕይወት የጠፋበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409 እንደዚሁ የ(Boeing 737-8AS) አውሮፕላን ነበር።
፲፱፻፺፯ ዓ/ም በስኮትላንድ ግሌን ኢግልስ የተካሄደው የቡድን-ስምንት (G8) ስብሰባ ለታዳጊ አገሮች እርዳታ በሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ወይም ሃያ ስምንት ነጥብ ስምንት ቢልዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ይጨምራል አለ። እንዲሁም ኢትዮጵያን አካቶ፣ ለአሥራ ስምንት የአፍሪቃ ድሐ አገራት ብድራቸውን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።
- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም - ኢትዮጵያን የወረረውን ግራኝ መሐመድን ለመከላከል የዘመተውን የ|ብርቱጋል ሠራዊት የመራው ኤስቴቫዎ ዳጋማ ወንድሙን ክሪስቶቫዎ ዳጋማ ን ከአራት መቶ ወታደሮችና መቶ ሃምሳ ባሪያዎች ጋር ትቶ ከምጽዋ ወደብ ወደአገሩ ተጓዘ።
- ፲፱፻፯ ዓ.ም - ስመ-ጥሩው ኢትዮጵያዊ አርበኛ እና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀ መንበር የነበሩት ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን (ዕ.ሞ. ጥቅምት ፱ ቀን [[1972|፲፱፻፸፪ ዓ/ም) በዛሬው ዕለት ቡልጋ ውስጥ፣ ልዩ ስሙ የለጥ ቡሄ ዓምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ።
- ፲፱፻፰ ዓ/ም - ከ፲፱፻፷፫ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፷፯ ዓ/ም የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሰር ኤድዋርድ ሂዝ (ዕ.ሞ. ሐምሌ ፲ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ/ም) በዚህ ዕለት ተወለዱ
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የቀድሞው የሞሮኮ ንጉሥዳግማዊ ሀሳን (በአረብኛ: الحسن الثاني)፤ (ዕ.ሞ ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ/ም) በዚህ ዕለት ተወለዱ። ንጉሡ የዛሬው የንጉሥ ሞሀመድ ራብአዊ (በአረብኛ: محمد السادس) አባት ናቸው።
- ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - ሪቻርድ ራውንድትሪ (Richard Roundtree). ሪቻርድ በዋና ተዋናይነት <<ጆን ሻፍት>> (John Shaft) ሆኖ <<ሻፍት ኢን አፍሪካ>> (Shaft in Africa) በተባለው ፊልም ላይ ከ'ጭራ ቀረሽ'ዘነበች ታደሰ እና ደበበ እሸቱ (ዋሳ Wassa) ጋር ሠርቷል፤ በዛሬው ዕለት ተወለደ።
- ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - የእንግሊዝ ልዕልት፣ (አሁን ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ) እና የሌፍተናንት (አሁን የኤዲንበራ መስፍን ልዑል) ፊሊፕ የጋብቻ እጭት ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺፬ ዓ/ም - የቀድሞውን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የተካው የአፍሪቃ ኅብረት አዲስ አበባ ላይ ተመሠረተ። የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚደንት ጻቦ እምቤኪ የኅብረቱ የመጀመሪያው ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከአደን የብሪታኒያ አየር ኃይል ሠፈር የተላከ ‘አየር ወለድ የባሕር አደጋ ተከላካይ’ ቡድን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ባለሥልጣናት ጋር የሁለት ቀን ውይይት ለማድረግ አዲስ አበባ ገባ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለኢራን ‘ሻህ’ የተላከ መልዕክት ለማድረስና ለሁለት ቀን ውይይት ቴህራን ገቡ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - በደቡባዊ ናይጄሪያ ውስጥ ከሚያንጠባጥብ የነዳጅ ቧንቧ ነዳጅ ሲቀዱ በፍንዳታ ሁለት መቶ ሃምሣ የመንደር ነዋሪዎች ሕይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - በንግሥት ዘውዲቱ እና በአልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ ትዕዛዝ መሠረት በራስ ደምሴ የተመራ ሠራዊት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢተወደድ ኃይለ ጊዮርጊስን በእግር ሰንሰለት አሠረ። ንብረታቸው ሁሉ ተወረሰ።
- ፲፱፻፲፯ ዓ.ም - በመቅደላ ጦርነት በእንግሊዞች ከተወሰዱት ሁለት የዓፄ ቴዎድሮስ ዘውዶች አንደኛው የብር ዘውድ በዛሬው ዕለት ለግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱ ተመለሰ። ከወርቅ የተሠራው ዘውድ አሁንም እንግሊዝ አገር ይገኛል።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ሞይስ ሾምቤ ካታንጋ የተሰኘውን የኮንጎ ግዛት በቤልጅግ መንግሥት ድጋፍ ነፃ መሆኑን ይፋ አደረገ።
- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም - ኢትዮጵያን ለመርዳት የተላከው የብርቱጋል ሠራዊት በዕለተ ቅዳሜ ምጽዋ ላይ አረፈ። ክረምቱንም ካሳለፈ በኋላ የዓፄ ልብነ ድንግል ሚስት ከነበሩት እቴጌ ሰብለ ወንጌል ወዳሉበት ተጓዙ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ደሴቶች ከብርቱጋል ነፃነታቸውን አወጁ።
ሐምሌ ፮
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -የቀድሞው የኤርትራ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የነበሩት ደጃዝማች ሀሚድ ፈረጅ ሃሚድ በጀብሐ ሽብርተኞች እጅ ከመስጊድ ጸሎት ሲወጡ አቆርደት ላይ ተገደሉ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - የአፍሪቃ ረሀብተኞችን ለመርዳት የተዘጋጀው የሙዚቃ ትርዒት (Live Aid) እስከ ሠላሳ ሚሊዮን ፓውንድ (£30m) ዕርዳታ ሰበሰበ።
- ፲፪፻፷ ዓ/ም - አጼ ይኩኖ አምላክ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ተቀብተው ዘውድ ጭነው ነገሡ።
- ፲፯፻፹፩ ዓ/ም የፓሪስ ኗሪዎች በከተማቸው የሚገኘውን የባስቲይ (Bastille ) ጥንታዊ ምሽግና ወህኒ ቤት በማጥቃት ሰባት እስረኞችን ነጻ አወጡ። ይኼም የፈረንሳይ አብዮት የፈነዳበት ዕለት በየዓመቱ ይከበራል።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም የዩናይተድ ስቴትስ መንግሥት የ $500, $1,000, $5,000 እና $10,000 ሰርዞ ከአገልግሎት ውጭ አደረጋቸው።
- ፲፻፺፩ ዓ/ም - በመጀመሪያው የክርስትና ዘመቻ (The Crusades) ምዕራባዊ ወጥቶ አደሮች በኢየሩሳሌም የትንሳዔ ቤተ ክርስቲያንን (Church of the Resurrection – Holy Sepulchre) ማረኩ። ቤተ ክርስቲያኑ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትና ያረገበት ሥፍራ ላይ የተሠራ ነው የሚል ዕምነት አለ።
- ፲፬፻፷፫ ዓ/ም - በንግሥ ስማቸው ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የሚባሉት ዓፄ እስክንድር ከአባታቸው ከ ዓፄ በዕደ ማርያም እና ከእናታቸው ሮምና ተወለዱ። እኚህ ንጉሠ ነገሥት በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ ከተቀመጡበት ዘመን (፲፬፻፸ ዓ/ም) እስከ ሞቱበት ዘመን (፲፬፻፹፮ ዓ/ም) ድረስ ነግሠዋል።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - አሁን በመቀሌ ከተማ ሰማዕታት ሐውልት አጠገብ የሚገኘው ድምጺ ወያነ ትግራይ በትግል ሜዳ ላይ ተመሠረተ።
- ፲፯፻፹፪ ዓ/ም - የዲስትሪክት ኦፍ ኮሉምቢያ (District of Columbia) የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መቀመጫ ዋና ከተማ ሆነ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ/ም -ዓፄ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው ዘውድ በጫኑ በስምንተኛው ወር የሀገሪቱን የመጀመሪያውን ሕገ መንግሥት በንጉሠ ነገሥቱ፣ አልጋ ወራሹ፣ ጳጳሳቱ፣ መሳፍንቱ፣ ሚኒስትሮቹ እና ባላባቶቹ መኳንንቱም ፈርመውበት በዐዋጅ ተግባር ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም -የአሜሪካ ኅብረት የመጀመሪያውን የሙከራ አቶሚክ ቦምብ አፈነዳ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የሟቹ የፕሬዚደንት ኬኔዲ ልጅ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጁንየር ከሚስቱ እና ከሚስቱ እህት ጋር በበረራ ላይ እንዳሉ በአየር ዠበብ አደጋ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ በመስመጥ ሕይወታቸውን አጡ።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት እና የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀባይ ኔልሰን ማንዴላ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የሟቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ታናሽ ወንድም ሴኔተር ኤድዋርድ ኬኔዲ ቻፓክዊዲክ ከሚባል ሥፍራ ሲመለሱ የሚነዱት መኪና ከመንገደኛቸው ከ ሜሪ ጆ ኮፔክኒ ጋር ድልድይ ጥሶ ወንዝ ውስጥ ሲከሰከስ ሴቷ ሕይወቷን አጥታለች።
- 1890 ዓ.ም. - አሜሪካውያን በስፓኒሾች ላይ በሳንቲያጎ ፍልሚያ ኩባ አሸነፉ።
- 1945 ዓ.ም. - በሆንዶ ደሴት ጃፓን 1700 ሰዎች በጎርፍ ሞቱ።
- ፲፯፻፸፩ ዓ/ም- የጎጃም መስፍን ደጅ አዝማች ክንፉ አዳም ንጉሥ ሰሎሞንን በነገሡ በዓመት ከአሥር ወር በኋላ ከዙፋናቸው አውርደው አሥረው አቤቶ ተክለ ጊዮርጊስን በቦታቸው አነገሡ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ፕሮፌሶር መስፍን ወልደ ማርያም በኢትዮጵያ አብዮት የባለ ሥልጣናትን ሙስና እና የሥልጣን ወንጀል እንዲመረምር ለተመሠረተው ሸንጎ ሊቀ መንበር እና ምክትላቸው ደግሞ ሻለቃ መሸሻ አድማሱ እንደሆኑ ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም -የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም ባንክን (The World Bank) እና ዓለም አቀፍ ገንዘባዊ ዕድርን (International Monetary Fund - IMF) የመሠረተውን የብሬቶን ዉድስ (Bretton Woods Agreement) ስምምነት አፀደቀ
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም - የዮርዳኖስ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ አብዱላ ኢየሩሳሌም ላይ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ የዓርብ ጸሎት ላይ እንዳሉ በአንድ የፍልስጥኤም ተወላጅ እጅ ተገደሉ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም -አፖሎ 11 የተባለው የጠፈር መንኮራኲር ጨረቃ ላይ ሲያርፍ የሰላሳ ስምንት ዓመቱ ኒል አርምስትሮንግ የጨረቃን ነጠፍ በመርገጥ የመጀመሪያው የሰው ልጅ ሆነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በቆጵሮስ ደሴት ላይ በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ሊቀ ጳጳስ ማካሪዮስ ከስልጣን በወረዱ በአምስተኛው ቀን፣ የቱርክ ሠራዊቶች ደሴቷን ወረሩ። እስካሁንም ይቺ ደሴት ለሁለት ተከፍላ የግሪክ ቆጵሮስ እና የቱርክ ቆፕሮስ በመባል የሁለቱ ዘሮች የልዩነት መተዳደሪያ ደሴት ናት።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት አካል የሆነው የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ድርጅቱ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማነቷን እንዳይቀበሉ በሙሉ ድምጽ ወሰነ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የምርጫ ፺፯ ውጤት ተጭበርብሯል በማለታቸው የአገሪቱን ሕገ መንግሥት ተቃራኒዎች ናችሁ በመባል ታሥረው የነበሩት የቅንጅት መሪዎችና ሌሎችም በተደረገላቸው “ምሕረት” ተለቀቁ።
- ፫፻፷፭ ዓ/ም - የግብጽ ከተማ እስክንድርያ ላይ በሱናሚ መነሻነት የተከሰተው በ ሪክተር ስኬል ሚዛን 8.0 ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ በከተማዋ ፭ ሺህ ሰዎችን ሲገድል ባካባቢዋ ደግሞ ከ ፵፭ ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎች ሞተዋል።
- ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - ከአሥራ አንድ ዓመት ግንባታ በኋላ በግብጽ የአስዋን ግድብ ሥራ ተጠናቀቀ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ፍንዳታ የልጅ እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት ከወደቀ በኋላ ምትካቸው ልጅ ሚካኤል ዕምሩ በዚህ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተሾሙ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እና የካታር መንግሥት በመካከላቸው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ለመመሥረት ተስማሙ።
- ፲፰፻፹፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ በሐረርጌ ውስጥ ኤጀርሳ ጎሮ ላይ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሽስት መንግሥት የሌላ ቋንቋ ወይም ባዕድ ቃላትን መጠቀምን ሕገ-ወጥ አድርጎ ደነገገ። (ኢትዮጵያም እንዲህ አይነት ህግ ባወጣች!!!!)
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - በጋማል አብደል ናስር የተመሠረተው የግብጽ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በ ጄነራል ሙሐመድ ናጊብ መሪነት ንጉሥ ፋሩቅን ገለበጠ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የግሪክ ወታደራዊ መንግሥት ውድቅ ሆኖ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኮንስታንቲን ካራማንሊስ መንግሥት እንዲመሠርቱ ተጋበዙ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የሞሮኮው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን አል ሓሳን አባታቸው ንጉሥ ዳግማዊ ሀሰን በተወለዱ በ ሰባ ዓመታቸው ሲሞቱ ንጉሥ ሞሐመድ አራተኛ ተብለው የንጉሥነት ዘውድ ጭነው ነገሡ።
- ፲፰፻፲፭ ዓ/ም -ቺሌ የሰውን ልጅ መሸጥ መለወጥ (ባርነት) ሕገ ወጥ አደረገች።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ ያረፈባት አፖሎ 11 መንኲራኩር ጠረፈኞቹን ኒል አርምስትሮንግን፣ ኤድዊን (በድ) ኦልድሪንን እና ማይክል ኮሊንስን ይዛ ሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ አረፈች።
- ፳፻ ዓ/ም - የአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ባራክ ኦባማ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎች በተሰበሰቡበት የበርሊን መናፈሻ ላይ ንግግር አደረጉ። በዚህ ንግግር ላይ ለ አውሮፓውያን እና አሜሪካኖች በበፊተኛው ትውልድ በአንድነት ኮሙኒዝምን እንዳሸነፉ፤ አሁን ደግሞ ሽብርተኝነትን በአንድነት እንዲዋጉ ጥሪያቸውን አቀረቡ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በልዑል ራስ አስራተ ካሳ የሚመራ የኢትዮጵያ የፓርላማ ቡድን ከዩናይተድ ስቴትስ ፕረዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጋር በ ዋይት ሃውስ ተገናኝቶ ስለ ኢትዮጵያ ልማት፤ የኢትዮጵያና የሶማልያ ግጭት እንዲሁም በአፍሪቃ የፖርቱጋል ቅኝ ግዛቶችና ስለ ደቡብ አፍሪቃ ሁኔታ ተወያየ።
- ፲፱፻፸ ዓ/ም - የመጀመሪያዋ የቤተ-ሙከራ-ጠርሙስ ጽንስ፣ ሉዊዝ ብራውን በዚህ ዕለት ተወለደች።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - ከፓሪስ ሻርል ደጎል ጥያራ ጣቢያ ለበረራ የተነሳው የፈረንሳይ 'ኮንኮርድ' ጥያራ (በረራ ቁጥር ፵፭፻፺) ከጥቂት የበረራ ጊዜ በኋላ ሲከሰከስ ተሣፋሪዎቹን በሙሉ እና አራት መሬት ላይ የነበሩ ሰዎችን፤ በጠቅላላው የ፻፲፫ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።
ይህ ቀን ልዩ ቀን ነው!!! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት ቀን ሲሆን፤ በዚህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅዱስ ኢየሉጣን ያዳነበት ቀን ነው። ይህ በዓል በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተከብሮ ይውላል። በተለይ ደግሞ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በልዩ ሁኔታ ይከበራል።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም በኩባዊው ፊደል ካስትሮ መሪነት ሞንካዳ በሚባል የሠራዊት ሠፈር ላይ የተሞከረው ያልተሳካ ጥቃት በአገሪቱ ፕረዚደንት ፉልጀንሲዮ ባቲስታ ላይ የተከሰተውን የኩባ አብዮት የመጀመሪያ ድርጊት ሆነ።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም የግብጽ መሪ ጋማል አብደል ናሰር የዓለም ባንክ ለአስዋን ግድብ ሥራ ብድር/ዕርዳታ ሲከለክላቸው በምላሽ የሱዌዝ ን ቦይ የኣገር ንብረት ኣደረጉት።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የከተማ ቦታን በግል መያዝ ክልክል መሆኑንና የከተማ መሬት ሲወረስም ምንም ካሣ እንደማይከፈል የሚያበሥረውን «የከተማ ቦታና ቤት አዋጅ» አወጣ።
- ፲፰፻፷፱ ዓ/ም. ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ምንጃር ላይ ቀርሾ፡ዐጥር፡በተባለው፡ሥፍራ ላይ ተወለዱ።
- ፲፱፻፰ ዓ/ም ልዑል አልጋ ወራሽ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ከአባታቸው ከደጃዝማች ተፈሪ መኮንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) እና ከናታቸው ከወይዘሮ መነን አስፋው (በኋላ እቴጌ መነን) ሐረር ከተማ ተወለዱ።
- ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ቤላሩስ ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አወጀ።
- ፲፱፻፰ ዓ/ም - ልጅ ኢያሱ ዓርብ በሌሊት ከአዲስ አበባ ተነሥተው በምድር ባቡር ድሬ ዳዋ ገቡ። በወቅቱ አላወቁትም እንጂ፣ ርዕሰ ከተማዋን ለመጨረሻ ጊዜ ያዩዋትም በዚህ ዕለት ሲሆን እዚያው ሐረርጌ ውስጥ እያሉ በመጪው መስከረም የመስቀል ዕለት ከሥልጣናቸው ተሻሩ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዊሊያም ተብማን የቀብር ሥነ ሥርዓት ሞንሮቪያ ከተማ ገቡ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በቻይና፤ ከቤዪጂንግ ሰሜናዊ ምሥራቅ በምትገኘው ታንግሻን የተባለች ከተማ አካባቢ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፯፻፶ ሺ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተገምቷል።
- ፲፰፻፳፰ ዓ/ም በፓሪስ ከተማ በፈረንሳይ አብዮት እና በ’ናፖሌዎናዊ ጦርነቶች’ ሕይወታቸውን ላጡ ፈረንሳውያን ወታደሮች መታሰቢያ የቆመው ‘የድል ቅስት’ (Arc de Triomphe) ተመረቀ።
- ፲፱፻፲፫ ዓ/ም አዶልፍ ሂትለር የጀርመን ሰብአዊ የሠራተኞች ማኅበር (Nationalsozialistische Deutsche Arbeiterpartei ) መሪ ሆኖ ተመረጠ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በወሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስ በፋሺስት ኢጣልያኖች እጅ ተረሽነው ለኢትዮጵያ አገራቸው ነጻነት ሰማዕትነት ተቀበሉ።
- ፲፱፻፵ ዓ/ም በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ምክንያት ለ አሥራ ሁለት ዓመታት ተቋርጦ የነብረው የኦሊምፒክ ፲፬ኛው ውድድር በሎንዶን ተጀመረ።
፯፻፶፬ ዓ/ም የዛሬዋ የኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ተመሠረተች።
፲፮፻፳፩ ዓ/ም ናፖሊ በተባለች የምዕራብ ኢጣልያ ከተማ በመሬት ነውጥ ፲ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
፲፱፻፳፪ ዓ/ም በኡራጓይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር ዋንጫ ውድድር አስተናጋጇ ኡራጓይ ዋንጫውን ዋና ከተማዋ ሞንቴቪዲዮ ላይ አሸነፈች።
፲፱፻፵፰ ዓ/ም ፕሬዚደንት አይዘንሃወር የአሜሪካ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት" (House of Representatives) እና "የእንደራሴዎች ሸንጎ" (Senate) በአንድነት ያጸደቁትን “በእግዚአብሔር እናምናለን” ("In God We Trust”) የሚለውን የአገሪቱን ብሔራዊ መፈክር ሕግ ፈረሙ። ሐምሌ ፳፬
- ፲፮፻፲፩ ዓ/ም - የመጀመሪያዎቹ አፍሪቃውያን ”ተገዳጅ ሎሌዎች” ወይም ባሪያዎች በዩናይትድ ስቴትስ ጄምስ ታውን፣ ቨርጂኒያ የሚባል ሥፍራ ላይ ከመርከብ ወረዱ።
- ፲፯፻፺፫ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታንያን እና የአየርላንድን ንጉዛቶች በማዋሐድ የአሁኗን የታላቋ ብሪታንያና የሰሜን አየርላንድ ንጉዛት ያስፈጠረው ሕግ ጸደቀ።
- ፲፰፻፳፮ ዓ/ም - በጠቅላላው የብሪታንያ ንጉዛቶች “ተገሎሌ" ወይም ባርነትን የሚደመስሰው ሕግ ተደንግጎ ጸደቀ። ሆኖም ሠራተኛ ያልሆኑ ተገሎሌዎች ሕጉ በጸደቀ በአራት ዓመቱ በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴ ዓ/ም ነጻነታቸውን ሲያገኙ ሠራተኛ ተገሎሌዎች ደግሞ ስድስት ዓመት ቆይተው በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴፪ ዓ/ም ነጻ ወጡ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በኮንጎ ሽብር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ አስከባሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሆነው ያገለገሉት ሌተና ጄኔራል ከበደ ገብሬ የሥልጣን ጊዜያቸውን በዚህ ዕለት አጠናቀቁ።
ሐምሌ 25 ቀን:
ከሰባት አመታት በፊት ሳሲት* ከተማ አቅራቢያ ታሪክ ራሱን ደገመ፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ ሲያስቡት ይደንቃል፡፡ ድርጊቴንና ወኔዬን ከዳኛቸው ወርቁ ልቦለድ ገጸባህሪ ከአደፍርስ እንግዳ ተግባራት ጋር እንዳወዳድር ይዳዳኛል - ከቋንቋ ተማሪነት ወደ አማተር ጂኦሎጂስት ወይም አርኪኦሎጂስትነት ተለውጬ ነበርና፡፡ ሳሲትና አካባቢዋም ከ70 አመታት በኋላ ባለውለታዋን አስታወሰች፡፡ በሳሲትና አካባቢዋ ነዋሪዎችና በዋሻዎች መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርኝት ሊያሳይ የሚችለው ቀላሉ ነገር የተለያዩ ስፍራዎች የተሰየሙበት ከዋሻ ጋር የተያያዘ ስማቸው ይመስላል - ቀለም ዋሻ፣ ጠጠር ዋሻ፣ ጅብ ዋሻ፣ እንግድዋሻ፣ ልሳንዋሻ፣ ምግልዋሻ፣ አምባዋሻ፣ እምብስ ዋሻ፣ ጽድ ዋሻ፣ ንብ ዋሻ፣ ድል ዋሻ፣ ወርቅ ዋሻ፣ ላም ዋሻ፣ ጨለማ ዋሻ፣ ዋርካ ዋሻ፣ ሾላ ዋሻ …
በታሪካዊ ልቦለዱ በአዳባይ ላይ እንደተገለጸው ‹‹በ1931 ዓ.ም. በአንቀላፊኝ የራስ አበበ የጦር አዝማቾች ከምሁራን ባልደረቦቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ‹የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖቸ አርበኞች ማህበርን› አቋቁመው ፈረሙ፡፡›› (ገጽ 166-7)፡፡ አንቀላፊኝ ሜዳ እና ሌሎችም ታሪካዊ ስፍራዎች በትውልድ አካባቢዬ ቢገኙም በቅድሚያ የመጎብኘት ትኩረቴን የሳበው ከሳሲት እስከ ሰላድንጋይ በምድር ውስጥ ያስኬዳል ተብሎ የሚታመንበት ዋሻ ነበር፡፡ 20 ኪሎሜትር ገደማ ‹‹ይረዝማል›› ይባላል፡፡ ዋሻ መሸሸጊያ መሆኑ በታሪክ የታየበት ጊዜ አለ በሞጃ እና ወደራ ወረዳ፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት ልጅ ሆነው ተሸሽገውበት እደነበረ ያጫወቱኝ አቶ ማሞ ገብሬ፣ ካሳዬ ወንዳፈረው የተባለ የአካባቢው ተወላጅ አርበኛ ከጣሊያን ወራሪ ወታደሮች ጋር እየተታኮሰ የአካባቢውን ህዝብና ከብት ይዞ ወደ ዋሻው እንደገባ፣ ከብቱን የፋሽስት ወታደሮች ከዋሻው አውጥተው ሲያርዱና ሲጥሉት ህዝቡ ግን ራሱን ተከላክሎ ወደ ውስጥ ገብቶ እንደዳነና በማግስቱም የአምስት አመት የስደት ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ይፋት እንደወረደ ዋሻውም መጨረሻው እንደማይታወቅና ሰላድንጋይ ይደርሳል ሲባል እንደሰሙም ነግረውኛል፡፡ አቶ አስፋውና አቶ ተክለወልድ ደግሞ ከደጋው ህዝቡ ሲያባርረው የመጣን ጅብ ዋሻው ውስጥ ሊገባ ሲል እንደገደሉት አጫውተውኛል፡፡ ከአብዛኛዎቹ ተጠያቂዎቼ እንደሰማሁት ግን በአንድ ወቅት አንዲት ውሻ በዋናው በር ስትገባ ታይታ ሰላድንጋይ ለጉዳያቸው የወጡ ስትገባ ያዩዋት ሰዎች እዚያም ባለው በር ስትወጣ አይተዋታል እየተባለ እንደሚተረት ነው፡፡ እንዲያውም የዋሻው የሰላድንጋዩ መውጫ በሩ ቁሮ ገደል በተባለ ስፍራ እንደሚገኝ ነግረውኛል፡፡ ለተጠያቂዎቼ ግን ‹‹ይህን ያህል ርዝመት እንዳለው አይታችኋል›› ስላቸው ‹‹እሱ ተብሎ ያለቀ ነው›› ይሉ ነበር፡፡ በህዝቡ ዘንድ የሚወራውን ለማረጋገጥ ዘመቻ ግድ ይል ነበር፡፡
ለ15 ቀናት ያህል ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ስለዚሁ ጉዳይ እንመክራን፤ ስለ ዋሻው የሰሙ ሰዎች መጥተው የሚነግሩኝንና ለዝግጅት የሚያስፈልጉትን ቁሳቁስም እጽፋለሁ፡፡ እንደነፍሰጡር ቀናችንን መቁጠሩ የባሰ ጉጉት አሳደረብን፡፡ ከመካከላችን አንዳንዶቹ የሚያነሷቸው ሃሳቦች የሚከተሉትን ይመሳስሉ ነበር - ‹‹ወደ ዋሻው ገብተን ብንጠፋፋና የዋሻው በር ቢጠፋብን የት እናገኘዋለን?›› እና ሌሎች ደግሞ ‹‹ስንሄድ ባህር ወይም ጎድጓዳ ስፍራ ቢገጥመን ተቀርቅረን መቅረታችን አይደለምወይ?›› ይላሉ፡፡ አስጊ ሁኔታ ነበር፡፡ ከአዛውንቶች በሰበሰብኩት መረጃ መሰረት ዋሻው ወደተለያየ አቅጣጫ የሚወስዱ መንገዶች ስላሉት አንዱን ተከትለን ሰው ወደ ጎን እንዳይሄድ እየተቆጣጠርን መሄድ ፣ ሰላድንጋይ ከተማ የሚያደርስ ከሆነ መንገዱ እንደ መሬት ላይ መንገድ ስለማይቀና ስንቅ ቋጥረን የፈጀውን ያህል ጊዜ ይፍጅ እንጂ የዋሻውን መጨረሻ ማየት አለብን አልን፡፡ በጉዟችን ወቅት ድቅድቅ ጨለማውን ለማብራት ችቦ፣ ጧፍ፣ ማሾ፣ ባትሪ እና ሻማ እንያዝ የሚሉ ሃሳቦች መጡ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ችቦ ጭሱ ያፍነናል ባትሪም ዋሻው ውስጥ አይበራም በማለታቸው ማሾ እና ጧፍ ለመያዝ ተስማማን፡፡ መሽቶ ሲነጋ ሁለት ሳምንት ቀኑን ሙሉ ስለዚሁ ዋሻ ስናወራ እንውላለን፡፡ገብተን ሰይጣን ልናገኝ፣ ለደህንነታችን የሚያሰጋ ተአምራዊ ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል የሚሉ ሰዎችን ስጋት ወደኋላ እየተውን ለመግባት የሚያስፈልገውን የቁሳቁስም ሆነ የስነልቦና ዝግጅት ቀጠልን፡፡ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከመሬት በታች መላዕክት እንደሚኖሩ፣ ሰዎች የሚኖሩበት ሌላ ሃገር እንዳለ፣ በዶሮ የሚታረስበት ግዛትም እንደማይጠፋ ስንሰማ አድገናል፡፡ ምናልባት ይህን የምናይበት ሌላ አለም ሊገኝ ይችላል ብዬ እኔም አስብ ሌሎችም በአዕምሯቸው ያወጡና ያወርዱ ነበር፡፡ሰው ባገኘኝ ቁጥር አስረዳለሁ፤ ጥያቄዎቻቸውንም እመልሳለሁ፤ በሰዎቹ ፍላጎት ደስታና እርካታ ይሰማኛል፤ እጓጓለሁ፤ እገረማለሁ፡፡ በአካባቢያችን ሌሎች መሰል ዋሻዎች አሉ ቢባልና እኛም ብናውቅ መጀመሪያ ያደረግንውን ይህን ዋሻ ለመጎብኘት አንድ ቀን ቀረን - ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 1999 ዓ.ም. ፡፡ በትውስት ማሾዎች ጋዝ ሞላን፤ ጧፎቻችንን ገዛን፤ ሻማና ሌሎችንም እንዲሁ አሟላን፡፡ ሰዉ በማቴሪያል፣ በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት ከጎናችን ስለነበረ ነው ዓላማችንን በመጠኑ ለማሳካትና ይህን ለእናንተ ለመንገር የበቃንው፡፡ በማግስቱ በዋሻው አቅራቢያ ያሉና ሊገቡ የተስማሙ ገበሬዎች በጠዋት እንድትመጡ ስላሉን ሕዝቡንም ለመቀስቀስ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ ጓደኞቼን ቀስቅሼ ሌሎችንም እንዲቀሰቅሱ አሳሰብኩ፡፡ ከነጋ በኋላ ወደ 12፡30 ሰአት ላይ ተጠቃለን ጉዟችንን ለማድረግ ከከተማዋ እምብርት ተነሳን፡፡ ያሰብንውን ያህል ባይሆንም ወደ ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ተሰባስበናል፡፡ በየቤቱ እየሄድን ስንቀሰቅሳቸው በሰበብ ባስባቡ እንደማይሄዱ አስተዛዝነው ይነግሩናል፡፡ እኛም ‹‹አላስገደድናቸው ከመጀመሪያው ለምን እሺ አሉ? ሰው ሂድ ብሎ ሳያስገድዱት እሄዳለሁ ይላል እንዴ?›› ብለን ታዘብናቸው፡፡ ለማንኛውም እኛው እንበቃለን ብለን ዝግ ባለ አረማመድ ከተማዋን ለቀን ወደ ምዕራብ ስንጓዝ ሰው ሁሉ ያየናል፡፡ ‹‹አረ የነብር ቁርስ እንዳትሆኑ!›› ሳይል አይቀርም ተመልካቹ - ካይኑ ያስታውቅበታል፡፡ ከተማዋን ለቀን ወደገጠሩ ስንገባ ሰዎች ከዚህም ከዚያም እየሮጡ ከከተማዋም ጭምር ተከተሉን፡፡ በርከትከት እያልን መጣን፡፡ በየቤቱ እንዲሰማ አድርገን የምናውቃቸውን ሰዎች ተጣርተን ብዙ ሰዎች ለመሰብሰብም ቻልን::
ወደ ሰሜን ታጥፈን ቁልቁል ከወረድን በኋላ አፋፉ ላይ ስንደርስ መንዝን ካድማስ ወዲያ ማዶ እያየንና የቆላማውንም ስፍራ ልምላሜ እያደነቅን ለደቂቃዎች እንኳን ሳንቆይ፣ አያቴ ‹ያ ማዶው ሰላሌ ነው› የሚለኝን ጨለማ አገር ቃኝተን ሳንጠግብ አትኩሮታችንን ወደ ተጉለቱ ድንቅ ዋሻ መለስን፡፡ የአካባቢው ገበሬም ቀድሞን ዋሻውንና አካባቢውን ወሮታል፡፡ በዙሪያው ከሩቁ የሚታዩትና ነጫጭ የለበሱት እነዚህ ሰዎች የጥንት አርበኞችን ያስታውሷችኋል፡፡ ደምቃ ፍም መስላ ከወጣችው የጠዋት ፀሀይ ግርጌ ከግራና ከቀኝ ትልልቅ ተራሮችን የተሸከመውና በመሃልም ሸለቆ የሚንፈላሰስበት ባለረጅም አፉ ዋሻ በአረንጓዴ ቅጠላ ቅጠል ተከቦ፣ በሸለቆው ውስጥ የሚመጣው ወንዝና በዋሻው መግቢያ ፊት ለፊት የሚወርደው ፏፏቴ አንድ ላይ ሆነው ሌላ ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት እነሆ አሉን፡፡ አንዲት አጎንብሳ ጸጉሯን በሳሙና የምታሽና ጸጉሯም በመታጠቢያው ሳፋ ላይ ለሽ ያለን ኮረዳ ያስመስለዋል፡፡ ጸጉሯን በፏፏቴው፣ ከንፈሯን በዋሻው አፍ ፣ ሁለቱን ትከሻዎቿን በተራሮቹ እንዲሁም ሳፋውን እታች ፏፏቴው በሚያርፍበት ባህር መመሰል ይቻላል፡፡ ይህን ሁሉ በማየቴ ተደነቅሁ፡፡ ከባልንጀሮቼ ጋር ወደዋሻው ተጠጋሁ፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች በዋሻው በር ላይ ተቀምጠው ታሪክ ያወራሉ፣ ይመክራሉ፡፡ ዋሻው በጎንና በጎኑ መግቢያ መንገድ ስላለው ሸረር ብለን ገባን፡፡ አቤት የነበረ ጥድፊያ! አቤት ያን ዋሻ ተጠግቶ ሲያዩት ያለው ግርማ ሞገስ፡፡ ውስጥ ስንገባ አናቱ ደማቅ ጥቁር ፣ መሬቱ ደግሞ ቀይ ደረቅ ለስላሳ አፈር ሲሆን ጣራው የጠቆረው አባቶቻችን በጣሊያን የግፍ ወረራ ጊዜ በችቦ ለብልበውት ነው ተባልን፡፡ ምክንያቱም ማዕድን ሊሆን ስለሚችል በጣሊያኖች አይን እንዳይገባ ተብሎ ነበር፡፡ ሲፈረፍሩት የሚያብረቀርቅ ልዩ አለት እየተፈረፈረ ይወርዳል፡፡ የወንዙ/የፏፏቴው ውሃ በፊታችን ወርዶ መሬት ላይ ሲያርፍ የሚያሰማው ልዩ ድምጽ ልብን ያሸብራል፣ አዕምሮን በአንዳች ፍርሃታዊ ምትሃት ያርዳል፤ ሁለመናን ይቀሰቅስማል፡፡ ሽሽሽ… ቻቻቻ… ይላል፡፡ ይህም በአቅራቢያው ካለው አያልፉሽ ከተባለው የጸበል ቦታ፣ ከአጃና ሚካኤልም በላይ ምጡቅ ነበር፡፡ ባሕታዊነትን ያስመኝማል፡፡ በዋሻው አቅራቢያ ያለው ስነ-ሕይወታዊ መስተጋብር ለዘርፉ ምሁራን ለም የምርምር ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡ አይደርሱ የለ ደረስን፣ አየንው የንን የጓጓን የቋመጥንለትን ዋሻ! ታዲያ አፉን እንጂ ሆድ እቃውን ለማየት ገና በዝግጅት ላይ ነበርን፡፡ ማሾዎች ተለኮሱ፤ ጧፉንም ያዝንና ታጥቀን ተመራርጠን ተነሳን፡፡ የዋሻውን አፍ ርዝመት ለክተን 105 ሜትር መሆኑን አረጋገጥን፡፡ ከፍታውም በመግቢያው በር አካባቢ ከ3 ሜትር ቢበልጥ እንጅ አያንስም፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በጉንብስ አለያም በጣም ዝቅ ሲል በደረት መሄድ ግድ ይላል፡፡ በውስጠኛው የዋሻው ክፍል አለትና ቋጥኝ፣ የጅብ ጽዳጅ፣ የእንስሳት ብሎም የሰው አጽም አግኝተናል፡፡ ዙሪያውን አሰስንው፤ ጎበኘንው፡፡ ሆኖም ግን በዚያ በሰፊው የዋሻው ክፍል ውስጥ ወደ ውስጥ መፈናፈኛ ጠፋ፡፡ ‹‹በምን ተገብቶ ነው ሰላድንጋይ የሚደረሰው?›› ብዬ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ አብዛኛዎቹ ተጠያቂዎቼ ‹‹በግለሰቦች ተደፍኖ ነው እንጅ በር ነበረው ፤ የቱጋ እንደሆነ ለማግኘት ከቋጥኙ መብዛት የተነሳ አልቻልንም›› አሉኝ፡፡ ቋጥኞቹን አልፎ ሄድ ሲሉ በዋሻው የቀኝ ክፍል ወደ መሬት የሚያሰገባ መንገድ አግኝተው የተወሰኑት ጓደኞቻችን ገቡ፡፡ አንዲት ሽንቁር ማሰሮና ሁለት የሰው የራስ ቅል ይዘውም ተመለሱ፡፡ ደረጀ አስራተ የተባለው ሌላኛው ዘማች ደግሞ በዋሻው መግቢያ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ‹‹ጎራዴ ና ባትሪ ብቻ ስጡኝ›› ብሎ በአንዲት ሰው ሁሉ በፈራት ጠባብ ጎሬ አልፎ ሄዶ ቀረብን፡፡ ግማሹ ሰው ፈራ ተባ እያለ ‹‹ወደ ኋላ ልመለስ ወይንስ ልጠብቀው፣ ጅብ በልቶት ይሆን ነብር?›› ሲል፣ ደምሰው ታችበሌ በልበሙሉነት ሲጋራውን ሲያጨስ በመጨረሻ የደረጀ ድምጽ ሲሰማ ህዝቡ እፎይ አለ፡፡ እኔም ደስ አለኝ፡፡ ‹‹ምን አለ›› ስንለው ‹‹የሆነ ወደላይ የሚያስወጣ መንገድ አለ ወጥቼ ልምጣ›› ሲለን እንደገና ደንገጥ አልንና ጠበቅንው፡፡ ‹‹አይይይ ምንም የለ›› ሲል አንድ ሆነ፡፡ ወደ አስር የሚሆኑ በዋሻው የግራ አቅጣጫ የሄዱ ሰዎች ደግሞ ትንሽ ሄደው ሰማይ ሲያዩ ‹‹ሌላ አገር የደረስን መሰለን›› ብለው ጮሁ፤ ግን ሌላ የዋሻው መግቢያ በር ነበር፡፡ ስለዚህኛው መግቢያ በር፣ ከዋናው በር ሌላ መሆኑ ነው፣ በዚያኛው ቡድን በኩል ባለመሆኔ ማየት ባልችልም ከሰማሁት ለመናገር ግን እችላለሁ፡፡ እኔ የነበርኩት በበሩ ትይዩ በነበረው አቅጣጫ ነበር፡፡ አቶ ታደሰ ዘነበ እንደነገሩኝ ደግሞ በዚሁ በቀኙ አቅጣጫ ወደታች አይቼ ልምጣ ብለው ገብተው ጓደኞቻቸው ጥለዋቸው/ረስተዋቸው ሄደው መውጫው ጠፍቷቸው ለደቂቃዎች ተቸግረውና ቢጣሩ የሚሰማቸው አጥተው በስንት ፍለጋ የገቡባትን ከሰው ትከሻ የማትሰፋ በር አግኝተው ወጥተዋል፡፡ ‹‹እኔ ተቻኩዬ ተመለስኩ እንጂ ያችማ ያች የተባለችው ከጎተራ አፍ ትጠባለች ያሏት ወደሰላድንጋይ የምታወጣው የጠፋችብን ዋናዋ በር ሳትሆን አትቀርም፤ ስንትና ስንት መንገድ እኮ ሄጃለሁ፤ በደንብማ ቢፈለግ ይህ ዋሻ አንድ ነገር አይጠፋውም ›› ብለዋል በእለቱ ከሰዓት በኋላ ጉዟችንን ስንገመግም፡፡
በሁሉም አቅጣጫዎች የአለቱን ብዛት አንድ መሃንዲስ ቢኖር በቢያጆ ይገምትልን ነበር፡፡ አንድ ትምህርት ቤት ይሰራል፡፡ ወደፊት በዚያ ዋሻ ሄደን ምናልባት ሰዎች ካገኘን ለልጆቻቸው ትምህርት ቤት መስሪያ ስሚንቶ ብቻ ከገዙ ይበቃቸዋል፡፡ ዋሻችን ከላይ የሚያዥ ነገር እና መሬትም ላይ የዚያው ክምችት (stalactites and stalagmites) ብዙ ቦታዎቹ ላይ አለው፡፡ ወለሉ ጫር ጫር ሲያደርጉት አፈሩ ልስልስና በእጅም ቢዝቁት የሚዛቅ ነው - ልክ አሸዋ በሉት፡፡ አንዳንዴ በቡድን በቡድን ሆነን ስንድህ ልጅነታችንን ያስታውሰናል፡፡ ከዚያ ደግሞ ሄደን የሚያስቆምና የሚያስፎክር ቦታም እናገኛለን፡፡ በእንደዚህ አይነት ጉዞ ታዲያ መደራጀትን የመሸሽ ችግር አይቀረፍምና ‹‹በቃ እንሂድ፤ በቃ አገራችን እንውጣ!›› እያሉ ካስቸገሩትና ባጭሩ ተስፋ ከቆረጡት በላይ አንዳንዶቹ ከዋሻው እየወጡ ወደ ሳሲት ይመለሱ ጀምረው ነበር፡፡ አንድ ሽማግሌ ደግሞ ከዋሻው በር ላይ ካለው ካብ ላይ ትልልቅ ድንጋይ እያነሱ ታች ቆላ ወዳለው ባህር ሲወረውሩ ረበሹኝ፡፡ ‹‹አረ ተው አብዬ ምነው?›› ሲሏቸው መች ይሰማሉ፡፡ ብቻ ይስቃሉ ደስ ብሏቸዋል መሰለኝ ቦታው፡፡ ይህ በዋሻው በር ላይ የተካበው ካብ አርበኞች ምሽግ አድርገው ይጠቀሙበት የነበረ ይመስለኛል፡፡ በጎብኝዎቹ መጣደፍ ምክንየት ብቻ ከሰአታት መጠነኛ አሰሳ በኋላ ወደ ሳሲት ከተማ በዋሻው በር በሌላኛው አቅጣጫ ወጥተን ትንሽ ዳገትም (ልዩ ስሙ ትልቅ አረህ) ፈትኖን የመልስ ጉዟችንን ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይዘን ጀመርንው፡፡ የወረድንው በጭጨት ነበር፡፡ ብዙም ተጉዘን እረፍት ተደረገና ወደ ከተማችን ደርሰን አንድ ቤት ገብተን ውይይትና ጨዋታው ቀለጠ፡፡ ከጉዟችን በኋላ ገበሬው ማዕድን አለበት እያለ የዋሻውን አናት ያገልሰው እንደያዘ ሰማን፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት ከተደረገው ቀጥሎ (ከሰባ አመታት በኋላ) ህዝብ ተነሳስቶ የገባበት ትልቁ ዘመቻ በዚህ መልኩ ተጠናቋል፡፡ ሌላ ጉብኝትና ጥናት ለማድረግ ሰባ አመታት እንጠብቅ ይሆን? ስለተነሳሽነቱ ህዝቡን ባያሌው አመሰግናለሁ፡፡ ህዝቡ ያለው ‹‹ዱሮስ እሱን አምነን›› ሳይሆን ‹‹ይህ ዋሻ ቀን ይወጣለታል›› ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዶ/ር ሲቪል መሃንዲስ ሀይለጊዮርጊስ ወርቅነህ የህይወት ታሪክ ላይ እንደተመለከተው ከሶስት መቶ በላይ የአርበኛ ጦር ከነቤተሰቡ በሳሲት አቅራቢያ ባለ አንድ ዋሻ መሽጎ ነበር፡፡ በተጉለት ሌሎች አርበኞችን ፍለጋ የሚዘዋወረው ይህ ጦር ዋሻ ውስጥ እንደመሸገ በአካባቢው ነዋሪዎች ይጠቆምበትና በአንድ ሺህ የጣሊያን ጦር ይከበባል፡፡ አስራ አራት ቀን ሙሉ በረሃብ ተሰቃይተውና ከዋሻው የላይኛው ክፍል የሚያዠውን ውሃ እየመጠጡ፣ ኮርቻ ፈልጠው እያነደዱ የጤፍ ቆሎ እየቆሉ እየበሉ፣ የጣሊያን ጦር እየተኮሰባቸው ከቆዩ በኋላ በአስራ አራተኛው ሌሊት ወንዶቹ ጥሰው ሲወጡ ተጨፈጨፉ፤ አስራ ሁለት አመት ገደማ ያሉ ወንድ ልጆችም ተረሸኑ፤ ሴቶቹና ህጻናት መጀመሪያ ወደ መንዝ ከዚያም ወደ ደብረ ብርሃን እስርቤቶች ተወሰዱ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትም ዶ/ር በዚያን ወቅት አስር አመታቸው ሲሆን በኋላ አድገው ተምረው አለምአቀፍ ምርምሮችን አቅርበው ተሸልመዋል፡፡ በሳይንስ መዛግብት ላይ ስማቸውን ያሰፈረላቸው እስከ 150 ኪሎሜትር ርቀት ጠጣር ነገርን የሚያስተላልፈው ቧንቧቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ (አልፈዋል)! ከመጽሀፋቸው የሚከተለውን እንመልከት ፡- ‹‹በዋሻው ውስጥ አባቴ፣ አጎቴ፣ እናቴና ያጎቴ ባለቤት እና ከዘጠኝ የሚበልጡ የቅርብ ዘመዶቻችን፣ እና ሌሎች ቤተሰቦች እንዲሁም ከ300 የሚበልጥ መሳሪያ ያለው ሰው ነበር፡፡ በዚያም ላይ የቀንድና የጋማ ከብቶችና የቤት እንስሳዎችን የመሳሰሉ ሁሉ ከዋሻው ውስጥ ነበሩ፡፡ ለጥቂት ቀናት የሚበቃ ምግብ፣ ውሃና ማገዶም ተይዞ ተገብቶ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ለ14 ቀናት ያህል በመከበባችን፣ ያ ይዘን የገባንው ምግብና ማገዶ አለቀ፡፡ ዋሻው ፊት ለፊት ከሚፈሰው ውሃ ለመቅዳት እንዳንችል፣ ጠላት ፊት ለፊት መሽጎ ይጠባበቅ ስለነበረ፣ በጣም አስቸጋሪ ሆነ፡፡›› የህይወቴ ታሪክ (10) ይህን ታሪክ እኔና ሳሲቶች የገባንበት እንግድዋሻ አለያም በሱው አቅራቢያ የሚገኘው ልሳን ዋሻ ሊጋሩት ይችላሉ፡፡ ልሳን ዋሻ በአንድ ቀን ብቻ ከ600 በላይ ሰው እንደተረሸነ አዛውንቶቹ አጫውተውኛል፡፡ ይህ ከላይ የተጠቀሰው ግድያ ሊሆንም ይችላል፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም የታሪክ፣ የጂኦሎጂና የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎቹን አስተባብሮ ይህን ዋሻ፣ ሌሎችን ዋሻዎችና ታሪካዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ስፍራዎችን ቢያስጠና ለአካባቢው ህዝብ ባለውለታ ያደርገዋልና ቢያስብበት እላለሁ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የፌደራሉ መንግስት፣ የአርበኞች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶችም የተጉለት ቅርሶች ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ቢሰሩ በማለትም አሳስባለሁ፡፡ ጣሊያን ቤቱን ሲያቃጥልበት ህዝቡ ዋሻዎች ውስጥ ነበር የኖረው፡፡ አሁንም ዋሻ እንደሚፈለግ ያሳየኝ ክስተት ቢኖር አንድ አዛውንት በ1999 ዓ.ም. ‹‹አንተ ልጅ ጓዳችንን ለምን ለሰው ታሳያለህ?›› ያሉኝ ነው፡፡ የእርሳቸውን ሃሳብ እያከበርኩ አሁን የአለም ሁኔታ እየተቀየረ መሄዱንና ዋሻ ውስጥ እስክንገባ የሚያሳድደን ነገር እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዋሻውን ለአገር ጎብኝ እያሳየን የገቢ ምንጭ እንድናደርገው እና እኛም እንጎበኘው ዘንድ የሁላችሁንም ትብብር በሁሉም ዘማቾች ስም እጠይቃለሁ፡፡ በመጨረሻም ለጭቁን ህዝቦች አርዓያና መጽናኛ በሆኑት በኢትዮጵያ በአርበኞች መዝሙር ልሰናበት፡- ጥንታዊት ኢትዮጵያ እናታችን ሆይ አርበኛሽ ጽኑ ነው ቆራጥ ተጋዳይ የደሙ ምልክት ያው በልብሱ ላይ ጥንታዊት ኢትዮጵያ አትደፈሪቱ ጠላትሽ ግፈኛ አረመኔ ከንቱ፡፡ ጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ማህበር ጠላትሽ ተዋርዶ ስምሽ እንዲከበር እንሸከማለን የመከራ ቀንበር፡፡
አዳባይ (243)
- ሳሲት ከተማ ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን 92 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኝ ተጉለቴ ነች፡፡ ከሞጃና ወደራ ወረዳ መዲናዋ ከሰላድንጋይ ደግሞ 20 ኪ.ሜ ትርቃለች፡፡ ሰላድንጋይን ብዙ ሰው በጻድቃኔ ማርያም ገዳም ያውቃታል፡፡
፲፱፻፶፪ ዓ/ም ኒጄር ነጻነቷን ከፈረንሳይ ተቀዳጀች።
፲፱፻፺፯ ዓ/ም የሞሪታንያው ፕሬዚደንት ማውያ ኡልድ ሲድ አህመድ ታያ ለሳውዲ አሬቢያው ንጉሥ ፋህድ ቀብር ከአገራቸው ወጥተው ሳሉ በወታደራዊ መፈንቅል ከሥልጣናቸው ወረዱ።
- ፲፱፻፲፭ ዓ/ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የእስክንድርያ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ፲፱፻፰ ዓ/ም ላይቤሪያ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በተጀመረ በሁለተኛው ዓመት በጀርመን ላይ ጦርነት አወጀ።
- ፲፰፻፶፫ ዓ/ም - የብሪታንያ ንጉዛት የቀድሞዋን የናይጄሪያ ዋና ከተማ ሌጎስን ከግዛቷ ጋር አዋሃደች።
፲፱፻፫ ዓ/ም አንድ ሚሊዮንኛው የአዕምሯዊ ንብረት (patent) በዩናይትድ ስቴትስ የአዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተመዘገበ። ይኼም የፍራንሲስ ሆልተን ውስጣዊ ቱቦ አልባ ጎማ ነው።
፲፱፻፷፮ ዓ/ም የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን የ“ወተርጌት ቅሌት” (watergate scandal) ተብሎ በሚታወቀው ጉዳይ ምክንያት የፕሬዚደንት ስልጣናቸውን በማግሥቱ እንደሚለቁ ይፋ አደረጉ።
፲፱፻፹፪ ዓ/ም ኢራቅ ጎረቤቷን ኩዌትን በመውረር የኢራቅ አካል አደርገች። ይኼም ድርጊት የመጀመሪያውን የባህረ ሰላጤ ጦርነት የጫረው ድርጊት ነው ፲፩፻፷፭ ዓ/ም - ሁለት ምዕተ ዓመት የፈጀው የፒሳ ግንብ ሥራ ተጀመረ።
፲፱፻፳፰ ዓ/ም -ጄሲ ኦዌን የተባለው ጥቁር አሜሪካዊ በበርሊን የናዚ ጀርመን ከተማ በሚካሄደው አሥራ አንደኛው ኦሊምፒክ ውድድር ላይ አራተኛ የወርቅ ኒሻን አሸነፈ።
፲፱፻፴፯ ዓ/ም -ናጋሳኪ የተባለችው የጃፓን ከተማ ላይ የአሜሪካ የቦንብ አውሮፕላን የጫነውን አቶሚክ ቦንብ ሲጥል ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ ከተማዋ ወድማለች።
፱፻፷፮ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን የወተርጌት ቅሌት በተሰኘው ጉዳይ ምክንያት ስልጣናቸውን ሲለቁ፣ ምክትል ፕሬዚደንቱ ጄራልድ ፎርድሥልጣኑን ተረክበው ፴፰ኛው ፕሬዚደንት ሆኑ።