ሞንሮቪያ
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 550,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 06°18′ ሰሜን ኬክሮስ እና 10°47′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
የፖርቱጋል መርከበኞች በ1560 ዓ.ም. ገዳማ ቦታውን 'ካፕ ሜዙራዶ' በሰየሙት ጊዜ ብዙ ኗሪዎች ይገኙ ነበር።
በ1813 ዓ.ም. ነጻ ጥቁሮች ከአሜሪካ በሸርብሩክ ደሴት (ዛሬ ሲዬራ ሌዎን) ሠፈሩ። ነገር ግን ይህ አልተከናወነምና ብዙዎች ሞቱ። ስለዚህ በ1814 ዓ.ም. ሌላ መርከብ ይዞአቸው ወደ ካፕ ሜዙራዶ አዲስ ሠፈር ጀመሩ። ስሙ ክራይስቶፖሊስ (ከግሪክ 'የክርስቶስ ከተማ' ማለት ነው) ሆነ። በ1816 ዓ.ም. ግን አዲስ ስሙ ሞንሮቪያ ሆነ፤ ይህም በወቅቱ አሜሪካዊ ፕሬዚዳንት በጄምስ ሞንሮ ትዝታ ተደረገ። ከአለሙ ዋና ከተሞች (ከዋሺንግቶን ዲሲ በቀር) እሱ ብቻ ለአሜሪካዊ ፕሬዚዳንት ስም ተሰየመ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |