እንግላንድእንግሊዝ ወይም አንግልጣርዩናይትድ ኪንግደም ዋና ክፍላገሮች አንዱ ነው። "ኢንግላንድ" የተባለበት ምክንያት ከዴንማርክ (አንገልን በአሁኑ ጀርመን ውስጥ) ወደ ታላቅ ብሪታንያ በ500 ዓም አካባቢ ከፈለሰው አንግሊ ብሔር ስሙን ስላገኘው ነው። ከ600 ዓም ጀምሮ በኢንግላንድ የሰፈሩት ሕዝቦች የድሮ አረመኔ ሃይማኖታቸውን ትተው ወንጌሉም ተቀበሉ፣ በዚያም ጊዜ ጽሕፈታቸውም ወደ ላቲን አልፋቤት ቀየሩ።

ኢንግላንድ

የአንግሊ እና ሳክሶንስ ጎሳዎች በ927 ዓም የኢንግሊዝን ግዛት አቋቋሙ። በሰሜን አውሮፓ ክፍል ያሉት የኖርዝ ህዝቦች በቪኪንግ ዘመን ለቅኝ ግዞት ወደ እንግሊዝ ሲመጡ አዲስ አረመኔ ማምለኪያ ስርአት አስተዋወቁ፣ ሆኖም ከጊዜ በኋላ እነዚህም ደግሞ ተጠመቁ።

ኢንግሊዝ ከ16ተኛው ክፍለ ጊዜ ጀምሮ ሀያላን ሀገር መሆን ጀመረች። ከ17ተኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዝ ቅኝ ግዛትን ማስፋፋት ጀመረች። የእንግሊዝ ግዛት በአለም ላይ ትልቁ ሲሆን ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ እንግሊዝ ሀያልነቷ ሊቀዘቅዝ ችሏል። በአሁኑ ሰአትም ከአሜሪካና ከጀርመን ቀጥላ ያለች ሀያላን ሀገር ናት። ኢንግሊዝ የተመድ፣ ኦከስ ስምምነት አባል ናት።