ስሎቫኪያ (ወይም በይፋ የስሎቫክ ሪፐብሊክ) በመሀከላዊ አውሮፓ ክፍል ያለች ሀገር ናት። በተራራ የተከበበቿ ስሎቫኪያ፣ 49,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት አላት። ወደ 5.4 ሚሊየን የሚክል ህዝብ ያላት ሲሆን፣ ብራቲስላቫ ዋና ከተማዋ ነው። ትልቁ ከተማም የሚሆነው ኩሲክ ነው።

Slovenská republika
የስሎቫኪያ ሪፐብሊክ

የስሎቫኪያ ሰንደቅ ዓላማ የስሎቫኪያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር "Nad Tatrou sa blýska"

የስሎቫኪያመገኛ
የስሎቫኪያመገኛ
ዋና ከተማ ብራቲስላቫ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ስሎቫክኛ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ
ዙዛና ካፕቶቫ
ኢድዋርድ ሄገር
ዋና ቀናት
ታኅሣሥ 23 ቀን 1985
(January 1, 1993 እ.ኤ.አ.)
 
የነጻነት ቀን
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
49,036 (127ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
 
5,435,343 (116ኛ)
ገንዘብ የስሎቫኪያ ኮሩና
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +421
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .sk

ከስድስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የስላቭ ህዝቦች የአሁኗን የስሎቫኪያን ምድር ረገጠዋል። ይህም የሶሞ ግዛት እንዲመሰረት ትልቁን ሚና ተጫውተዋል። በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን፣ የኒትራ ክፍለ ሀገር ቢቋቋምም የሞራቪያ ግዛት ቅኝ ገዝቶታል። በ10ኛው ክፍለ ዘመን ታላቋ ሞራቪያ የሀንጋሪውን ክፍለ ሀገር በመቀላቀል የሀንጋሪ ግዛት በ1000 ዓም መቋቋም ጀመር። በ1241ና በ1242 ዓም የሀንጋሪ ግዛት በሞንጎል ወረራ ቢገነጣጠልም የሃንጋሪው ንጉስ ቤላ ቦታውን ሊታደገው ችሏል። ቤላ የሀንጋሪና የጀርመን ሰዎችን በቦታው በመሰብሰብ ትልቁን ስራ ሰርቷል።

የአንደኛው አለም ጦርነት ሲያበቃ፣ ቼክስሎቫኪያ እንደ ሀገር መመስረት ጀመረች። ይህችም ሀገር ከአውሮፓ ሀገራት በተለየ ዴሞክራሲ የሰፈነባት ስትሆን ጥቂት የፋሺስት አራማጆች የስሎቫክያ ሪፐብሊክን ሲመሯት ነበር። ቼክስሎቫኪያ የናዚ ጀርመን ተጓዳኝ ግዛት ስትሆን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ነፃ ወታለች። ከዛም በኋላም በሶቬት ተፅዕኖ መመራት ጀመረች። ብዙ ሙከራዎች በሀገሪቱ ውስጥ የኮሚኒስት አገዛዝ እንዲገታ ቢሰነዘሩም የፕራጉ ስፒሪንግ እንዲነሳና በስተመጨረሻም የቬልቬት አብዮት እንዲቀሰቀስ አድርጓል። ቼክስሎቫኪያም በ1993 ዓም ተከፈለች፣ ስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክና ስሎቫክያ እንደ ሉአላዊ መሆን ጀመሩ።

ስሎቫኪያ የበለፀገች ሀገር ናት። ስሎቫክያ ከጎረቤት ሀገሯ ቼክ በተለየ ክርስትናን የምትቀበል የሀይማኖት ሀገር ናት። የሶቬት አገዛዝ ስሎቫክያ ከቼክ ጋር በአርተሳሰብ እንድትነፃፀር አድርጓታል። የስሎቫክያ ህዝቦች ሰላምን፣ ብልፅግናና መቻቻልን የሚደግፉ ሲሆኑ የምዕራብውያን ጣልቃ ገብነትን የምትቃወም ነፃነታዊ ሀገር ናት። የሀይማኖት አስፈላጊነት በሀገሪቱ ውስጥ በመኖሩ አብዛኛውን የስሎቫኪያ ህዝብ የምዕራብያውያን የልቅ አስተሳሰብን የሚከተሉ አደሉም። ነገር ግን ስሎቫኪያ የምዕራብያውያን አካል ናት።