ዓፄ በእደ ማርያም
(ከዓፄ በዕደ ማርያም የተዛወረ)
==
ዓፄ በእደ ማርያም | |
---|---|
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ | |
ግዛት | ፲፬፻፷ - ፲፬፻፸ . |
ቀዳሚ | ዘርአ ያዕቆብ |
ተከታይ | ዓፄ እስክንድር |
ባለቤት | ካልዩፕ |
ሥርወ-መንግሥት | ሰሎሞን |
አባት | ዘርአ ያዕቆብ |
እናት | ንግሥት ጽዮን ሞገሴ |
የተወለዱት | 1440 ዓ.ም. ደብረ ብርሃን |
የተቀበሩት | አትሮንስ ማርያም |
ሀይማኖት | ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ |
==
አጼ በእደ ማርያም በ፲፬፻፵ ዓ.ም ደብረ ብርሃን ከአባታቸው አጼ ዘርአ ያዕቆብና እናታቸው ጺዮን ምገሴ ተወልደው ከነሐሴ ፳፮፣ ፲፬፻፷ ዓ/ም - ኅዳር ፲፣ ፲፬፻፸ ዓ/ም የነገሡ የስሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት አባል ናቸው። ዓፄ በእደ ማርያም፤ በተወለዱ በ ሠላሳ ዓመታቸው፤ በነገሡ በአሥር ዓመታቸው ባልታወቀ ህመም ሞቱ።
ንጉሠ ነገሥት በእደ ማርያም ከላንቶ ይባል የነበረውን አገር አትሮንስ ማርያም ብለው ሰይመው፣ ቤተ ክርስቲያንም አሠርተው የማርያምን ታቦት አስገቡ። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኒኮሎ ብራንካሌዮን በተባለ የቬኒስ ሰዓሊ የድንግል ማርያምና የሕጻኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል አስለው ነበር። [1]
ማገናዘቢያ
ለማስተካከል- ^ መሪራስ ኤ. ኤም በላይ፣ “የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ”፣ ገጽ 249 - 257
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |