ሐምሌ ፩ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፩ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፬ ቀናት ይቀራሉ።

አቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ለማስተካከል

፲፱፻፵፪ ዓ/ም የአሜሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት ሃሪ ኤስ ትሩማንኮርያ ጦርነት ላይ ለተሠማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሕበር ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ብለው ጄነራል ዳግላስ ማካርተርን ሰየሙ። በጦርነቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላትም በ ማሕበሩ ስር ተሳትፈዋል።

፲፱፻፶፰ ዓ/ም የቡሩንዲንጉሥ ምዋምቡትሳ ፬ኛ ባንጊሪሴንግ በልጃቸው በልዑል ቻርልስ ንዲዚ ተገለበጡ።

፲፱፻፸፰ ዓ/ም የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የጦር መኮንን ነበሩ የተባሉት ኩርት ቫልዳይምአውስትሪያ ፕሬዚደንት ሆነው የቃለ መሃላ ሥርዐት ፈጸሙ።

፲፱፻፺፭ አንድ መቶ አሥራ ስድስት መንገደኞችን የጫነው የሱዳን አየር መንገድ (Boeing 737-200) አውሮፕላን ፖርት ሱዳን በአደጋ ሲከሰከስ አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም። ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሠላሳ አንድ ኢትዮጵያውያን እና የሃምሳ ዘጠኝ ሌላ ዜጎች ሕይወት የጠፋበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409 እንደዚሁ የ(Boeing 737-8AS) አውሮፕላን ነበር።

፲፱፻፺፯ ዓ/ም በስኮትላንድ ግሌን ኢግልስ የተካሄደው የቡድን ስምንት (G8) ስብሰባ ለታዳጊ አገሮች እርዳታ በሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ወይም ሃያ ስምንት ነጥብ ስምንት ቢልዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ይጨምራል አለ። እንዲሁም ኢትዮጵያን አካቶ፣ ለአሥራ ስምንት የአፍሪቃ ድሀ አገራት ብድራቸውን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።

ልደት ለማስተካከል

ዕለተ ሞት ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል