ራዲዮ ራዲዮ ሞገዶችንመከርከም መልዕክት ከቦታ ቦታ የሚተላለፍበት ቴክኖሎጂ ነው። [1] ራዲዮ ሞገድ የብርሃን አይነት ሞገድ ሲሆን ልዩነቱ የራዲዩ ሞገድ የብርሃንን ያኽል አይርገበገብም። የራዲዮ ሞገድ በአየርም ሆነ በወና ውስጥ የሚጓዘው የኤሌክትሪክ መስኩን በማርገብገብና ሞገድ በመፍጠር ነው። ይህን ሞገድ ባህርዩን በዘዴ በመቀየር (በመከርከም) መልዕክት እንዲያዝል ተደርጎ ይላካል። ለምሳሌ የራዲዮ ሞገዱን ቁመት በአንድ ድምፅ ሞገድ ትክክል ተከርክሞ ሲጫን ኤ.ኤም ራዲዮ ይፈጠራል። በራዲዮ ሞገዱ ድግግሞሽ ላይ ሲጫን ደግሞኤፍ.ኤም ራዲዮ ይሆናል። በሞገዱ ቅድመት ላይ ሊጫን ይችላል፣ ሆኖም ይሄ ብዙ ጊዜ የተለመደ አይደለም። በድምፅ ሞገድ ትክክል የተከረከመው የራዲዮ ሞገድ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁስ ሲያጋጥመው በቁሱ ውስጥ ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ጅረት ይፈጥራል። ይህን ተለዋዋጭ ጅረት የሚተረጉሙ መሳሪያወች የተጫነውን ድምፅ ከራዲዩ ሞገዱ አውርደው ወደ ስፒከሩ በመላክ የራዲዮ ዝግጅት እንዲደመጥ ይሆናል። ከድምፅ በተጨማሪ የምስል መልዕክትም ሊላክ ይችላል፣ በዚህ ወቅት የቴሌቪዥን ዝግጅት እንዲታይ ይሆናል።

2008 ዲጂታል ራዲዮ

የራዲዮ ቴክኖሎጂ ብዙ ተማሪወችንና ብዙ ጊዜ የወሰደ ጥረት ነው እንጂ ያንድ ሰው ድንገተኛ ፈጠራ አይደለም። ሆኖም አንድ አንድ ተማሪወች ከሌሎች በተለየ መልኩ ጉልህ አስተዋጾ ስላደረጉ በታሪክ ተጠቃሽ ናቸው፣ ከነዚህ ውስጥ ቶማስ ኤድሰንኒኮላ ቴስላ እና ጉልየልሞ ማርኮኒ ዋናዎቹ ናቸው። በ1885 ዓ.ም. ኒኮላ ቴስላ እንዴት መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ያለ ሽቦ ማስተላለፍ እንዲቻል አሳየ [2]። ከዚያ በኋላ ተመራማሪወች፣ አንዱ ያንዱን ስራ በማሻሻል በ1887 ዓ.ም. ማርኮኒ ያለ ሽቦ መልዕክትን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ሩቅ ቦታ የሚያስተላልፍ ስርዓት በተጨባጭ በመገንባት (2.4 ኪሎ ሜትር) በሚቀጥለው አመት ደግሞ ከእንግሊዝ አገር ለራዲዮ ፈጠራ ፓተንት በማግኘት አሁን ድረስ ስሙ ተጠቃሽ ነው። በ1889 ማርኮኒ የመጀመሪያውን የራዲዮ ማሰራጫ በአይል ኦፍ ራይትእንግሊዝ በመክፈት እንዲሁም የራዲዮን ማምረቻ ፋብሪካ በማቋቋም ስሙ ከራዲዮ ፈጠራ ጋር እንዲቆራኝ ሆነ።

ደግሞ ይዩ
የራዲዮ ቴክኖሎጂዎች
ኅልዮት
  1. ^ Dictionary of Electronics By Rudolf F. Graf (1974). Page 467.
  2. ^ IEEEVM: Nikola Tesla