ማሊ
የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች።
የማሊ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: ማሊ Le Mali |
||||||
ማሊ በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ባማኮ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፈረንሳይኛ | |||||
መንግሥት {{{ ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት |
ኢብራሂም ቡባካር ከይታ አብዱላዬ ኢድሪሣ ማይጋ |
|||||
ዋና ቀናት ግንቦት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. (ጁን 20, 1960 እ.ኤ.አ.) |
ነፃነት ከፈረንሳይ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
1,240,192 (24ኛ) 1.6 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2007 ግምት |
11,995,402 (73ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ፍራንክ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | 223 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .ml |
ታሪክ
ለማስተካከልማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር።
ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር።
ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች።
ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ።
መልከዓ-ምድር
ለማስተካከልማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ።
ፖለቲካ
ለማስተካከልየማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት።
አስተዳደራዊ ክልልሎች
ለማስተካከልማሊ በስምንት ክፍለ-ሀገሮችና አንድ ከተማ ተከፋፍላለች።
ኢኮኖሚ
ለማስተካከልማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።