ኅዳር ፲፪
ኅዳር ፲፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፪ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፯ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፫ ቀናት ይቀራሉ።
ይህን ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች፣ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ምድር ጀምሮ ከነዓን እስኪገቡ ድረስ እየመራ እየጠበቀ አብሯቸው በመጓዝ ምድረ ዕርስት እንዲገቡ ያደረገበት መታሰቢያ በማድረግ በየዓመቱ ያከብሩታል። [1]
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፬፻፸ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ በእደ ማርያም፤ የዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ልጅ በተወለዱ በ ሠላሳ ዓመታቸው፤ በነገሡ በአሥር ዓመታቸው ባልታወቀ ህመም ሞቱ። ልጃቸው ዓፄ እስክንድር ወይም ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ ተተክተው ነገሡ።
- ፲፰፻፸ ዓ/ም - አሜሪካዊው የሰገላዊ-ፈጠራ ሰው ቶማስ አልቫ ኤዲሰን ድምጽን መቅረጽና መልሶ ማሰማት የሚያስችለውን “ፎኖግራፍ” የተባለውን ፈጠራውን አሳየ።
- ፲፰፻፸፪ ዓ/ም - የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ሥርዓተ ቀብር በእንግሊዝ 'ዊንድሰር ካስል' ቅዱስ ጊዮርጊስ ፀሎት ቤት ተመፈጸ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የኢራን ሃይማኖታዊ-መሪ አያቶላ ኾሜኒ በአሜሪካ ላይ ያላቸውን የጥላቻ መልዕክት የራዲዮ ስርጭት ተከትሎ፤ በፓኪስታን ርዕሰ ከተማ እስላማባድ አክራሪ አመጸኞች የአሜሪካን ኤምባሲ በእሳት ሲያወድሙት አምሥት ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የግብጽ ተወላጅ የሆኑትን ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊን ለድርጅቱ ስድስተኛ ዋና ጸሐፊነት መረጣቸው።
ልደት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |