ሴኔጋል
ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 17 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል።
የሴኔጋል ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Pincez Tous vos Koras, Frappez les Balafons | ||||||
ሴኔጋል በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ዳካር | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፈረንሳይኛ | |||||
መንግሥት {{{ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ማኪ ሳል ሞሐመድ ዲየን |
|||||
ዋና ቀናት መጋቢት ፳፮ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. (April 4, 1960 እ.ኤ.አ.) |
ነፃነት ከፈረንሳይ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
196,712 (86ኛ) 2.1 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት የ2016 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
15,589,485 (72ኛ) 14,320,055 |
|||||
ገንዘብ | CFA ፍራንክ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | 221 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .sn |
የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ።
ታሪክ
ለማስተካከልበአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ።
ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ።
በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች።
አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል።
ምጣኔ ሀብት
ለማስተካከልወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው።
ፖለቲካ
ለማስተካከልሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።
ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው።
በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡
የአመራር ክፍሎች
ለማስተካከልሴኔጋል ወደ 14 ክልሎች ትከፈላለች። የክልሎችና የክልሎች ዋና ከተማዎች ስም ተመሳሳይ ነው።
|
ትላልቅ ከተማዎች
ለማስተካከልከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው።[1] ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው።[1][2]
ከተማ | የሕዝብ ብዛት (2005 እ.ኤ.አ.) |
---|---|
ዳካር (ዋና ዳካር, ጉዌዲያዋዬ እና ፒኪኔ[2]) | 2,145,193[1] |
ቱባ (ቱባ ሞስኪ[2]) | 475,755[1] |
ቲዬስ | 240,152[1] |
ካኦላክ | 181,035[1] |
ምቦር | 170,875[1] |
ሴንት ሉዊ | 165,038[1] |
ሩፊስክ | 154,975[1] |
ዚጉዊንቾር | 153,456[1] |
ሕዝብ
ለማስተካከልሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው።
የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ።[3]
የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ።
ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም።
በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።
ማመዛገቢያ
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ Agence Nationale de la Statistique et de la Démographie (2005 እ.ኤ.አ.). "Situation économique et sociale du Sénégal" (PDF) (በፈረንሳይኛ). Government of Senegal. Archived from the original on 2008-06-25. በ2008-11-18 የተወሰደ.
- ^ ሀ ለ ሐ Forsberg, Jan. "Cities in Senegal" (በእንግሊዝኛ). Archived from the original on 2012-02-27. በ2008-11-18 የተወሰደ.
- ^ "World Refugee Survey 2008" (in እንግሊዝኛ). U.S. Committee for Refugees and Immigrants. 2008-06-19. Archived from the original on 2010-05-28. https://web.archive.org/web/20100528032724/http://www.refugees.org/survey/ በ2011-01-23 የተቃኘ.