የዓለም ዋንጫ

በከፍተኛ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን የተካሄደ የአለም አቀፍ ማህበር የእግር ኳስ ውድድር

የዓለም ዋንጫዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር አባል አገሮች የወንድ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚከናወን ውድድር ነው። ከ፲፱፻፳፪ ዓ/ም ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይካሄዳል። ነገር ግን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት የ፲፱፻፴፬ ዓ/ም እና የ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ውድድሮች ሲሰረዙ እስካሁን አሥራ ዘጠኝ ውድድሮች ተካሂደዋል። የዋንጫና ደረጃ ጨዋታዎቹ በዓለም በብዙ ተመልካቾች ከሚታዩ የስፖርት ዝግጅቶች አንደኛ ነው። በደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የ ፳፻፪ቱ ፲፱ ኛው የዋንጫ ውድድር በ ፩ ነጥብ ፩ ቢሊዮን ሰዎች እንደታየ ይገመታል።

የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ
የዛሬ
የዛሬ
ዓርማ ዓመተ ምሕረት አስተናጋጅ አገር ተወዳዳሪ ቡድኖች የዋንጫው ውድድር ቀን የዋንጫ ቡድኖች አሸናፊ ቡድን የጎል ብዛት
  ፲፱፻፳፪ ዓ/ም
(1930 እ.ኤ.አ.)
ኡራጓይ ፲፫ ሐምሌ ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ/ም ኡራጓይ እና አርጀንቲና ኡራጓይ ፬ ለ ፪
  ፲፱፻፳፮ ዓ/ም
(1934 እ.ኤ.አ.)
ኢጣልያ ፲፮ ሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፳፮ ዓ/ም ኢጣልያ እና ቼኮዝሎቫኪያ ኢጣልያ ፪ ለ ፩
  ፲፱፻፴ ዓ/ም
(1938 እ.ኤ.አ.)
ፈረንሳይ ፲፭ ሰኔ ፲ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ኢጣልያ እና ሁንጋሪያ ኢጣልያ ፬ ለ ፪
  ፲፱፻፵፪ ዓ/ም
(1950 እ.ኤ.አ.)
ብራዚል ፲፫ ሐምሌ ፯ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ/ም ኡራጓይ እና ብራዚል ኡሩጓይ ፪ ለ ፩
  ፲፱፻፵፮ ዓ/ም
(1954 እ.ኤ.አ.)
ስዊዘርላንድ ፲፮ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፵፮ ዓ/ም ጀርመን እና ሁንጋሪያ ጀርመን ፫ ለ ፪
  ፲፱፻፶ ዓ/ም
(1958 እ.ኤ.አ.)
ስዊድን ፲፮ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፶ ዓ/ም ብራዚል እና ስዊድን ብራዚል ፭ ለ ፪
  ፲፱፻፶፬ ዓ/ም
(1962 እ.ኤ.አ.)
ቺሌ ፲፮ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ብራዚል እና ቼኮዝሎቫኪያ ብራዚል ፫ ለ ፩
  ፲፱፻፶፰ ዓ/ም
(1966 እ.ኤ.አ.)
እንግሊዝ ፲፮ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፰ ዓ/ም እንግሊዝ እና ጀርመን እንግሊዝ ፬ ለ ፪
  ፲፱፻፷፪ ዓ/ም
(1970 እ.ኤ.አ.)
ሜክሲኮ ፲፮ ሰኔ ፲፪ ቀን ፲፱፻፷፪ ዓ/ም ብራዚል እና ኢጣልያ ብራዚል ፬ ለ ፩
  ፲፱፻፷፮ ዓ/ም
(1974 እ.ኤ.አ.)
ጀርመን ፲፮ ሰኔ ፳፰ ቀን ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ጀርመን እና ሆላንድ ጀርመን ፪ ለ ፩
  ፲፱፻፸ ዓ/ም
(1978 እ.ኤ.አ.)
አርጀንቲና ፲፮ ሰኔ ፲፮ ቀን ፲፱፻፸ ዓ/ም አርጀንቲና እና ሆላንድ አርጀንቲና ፫ ለ ፩
  ፲፱፻፸፬ ዓ/ም
(1982 እ.ኤ.አ.)
እስፓኝ ፳፬ ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፸፬ ዓ/ም ኢጣልያ እና ጀርመን ኢጣልያ ፫ ለ ፩
  ፲፱፻፸፰ ዓ/ም
(1986 እ.ኤ.አ.)
ሜክሲኮ ፳፬ ሰኔ ፳ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ/ም አርጀንቲና እና ጀርመን አርጀንቲና ፫ ለ ፪
  ፲፱፻፹፪ ዓ/ም
(1990 እ.ኤ.አ.)
ኢጣልያ ፳፬ ሰኔ ፳፱ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ/ም ጀርመን እና አርጀንቲና ጀርመን ፩ ለ ዜሮ
  ፲፱፻፹፮ ዓ/ም
(1994 እ.ኤ.አ.)
አሜሪካ ፳፬ ሐምሌ ፰ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ/ም ብራዚል እና ኢጣልያ ብራዚል ፫ ለ ፪
  ፲፱፻፺ ዓ/ም
(1998 እ.ኤ.አ.)
ፈረንሳይ ፴፪ ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፺ ዓ/ም ፈረንሳይ እና ብራዚል ፈረንሳይ ፫ ለ ዜሮ
  ፲፱፻፺፬ ዓ/ም
(2002 እ.ኤ.አ.)
ኮርያ እና ጃፓን ፴፪ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም ብራዚል እና ጀርመን ብራዚል ፪ ለ ዜሮ
  ፲፱፻፺፰ ዓ/ም
(2006 እ.ኤ.አ.)
ጀርመን ፴፪ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም ኢጣልያ እና ፈረንሳይ ኢጣልያ ፭ ለ ፫
  ፳፻፪ ዓ/ም
(2010 እ.ኤ.አ.)
ደቡብ አፍሪቃ ፴፪ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም እስፓኝ እና ሆላንድ እስፓኝ ፩ ለ ዜሮ
 

የሚቀጥለው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ዋንጫ ፤ ፳ኛው ውድድር በብራዚልሰኔ ወር ፳፻፮ ዓ/ም (2014 እ.ኤ.አ.) ይካሄዳል።

የ፳፻፲ ዓ/ም (2018 እ.ኤ.አ.) የዓለም ዋንጫ በሩሲያ ይካሄዳል።
የ፳፻፲፬ ዓ/ም (2022 እ.ኤ.አ.) የዓለም ዋንጫ በኳታር ይካሄዳል።

ዋቢ ምንጭ

ለማስተካከል