የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ
የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ (Deutsche Wiedervereinigung ዶይቸ ቪድርፈራይንገንግ) በ መስከረም 23 ቀን 1983 ዓ.ም. (Oct. 3, 1990 እ.ጎ.አ.) የሆነው የጀርመን ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ (ወይም ምስራቅ ጀርመን) ወደ የጀርመን ፌዴራል ሬፑብሊክ (ወይም ምዕራብ ጀርመን) ሲጨመር ነበር። GDR መጀመርያ ጊዜ እውነተኛ ምርጫ (ማለት ከአንድ ወገን በላይ መምረጥ) ከተደረገው ከመጋቢት 9 ቀን 1982 (Mar. 18) በኋላ ሁለቱ መንግሥታት የመወሐድ ውል ተፈራርመው ከ2ኛ አለማዊ ጦርነት ቀጥሎ ባለሥልጣን በሆኑት ሀያላት ተፈቅደው አንድ መንግሥት ፈጠሩ። ይህ የተወሐደ ጀርመን አገር የተባባሪ መንግሥታትና የናቶ አባል ሆኖ ቆየ። ዳግመኛ መወሐድ የሚባለው በ1863 ዓ.ም. መጀመርያ መወሐድ ስለተደረገ ነው።