ቼልሲ
ቼልሲ (Chelsea F.C.) በፉልሃም ለንደን የሚገኝ የእግር ኳስ ቡድን ነው። ይህ ቡድን እ.ኤ.አ በ1905 የተመሠረተ ሲሆን ፣ የሚጫወተው ደግሞ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ነው። ቼልሲ ፤ ከምሥረታቸው ጊዜ ጀምሮ የሚጫወቱት 41,837 ሰዎችን የማስተናገድ ብቃት ባለው ስታምፎርድ ብሪጅ ተብሎ በሚጠራው የእግር ኳስ ሜዳ ነው።
ሙሉ ስም | ቼልሲ የእግር ኳስ ክለብ | |||
ቅጽል ስም(ሞች) | ሠማያዊዎቹ | |||
አርማ | {{{አርማ}}} | |||
ምሥረታ | 1905 እ.ኤ.አ. | |||
ስታዲየም | ስታምፎርድ ብሪጅ | |||
ባለቤት ሊቀ መንበር አሰልጣኝ |
ቶድ ቦሂሊ | |||
ሊግ | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ | |||
ድረ ገጽ | [1] (እንግሊዝኛ) | |||
|
ቼልሲ፣ የመጀመሪያቸውን ድል የተጎናጸፉት እ.ኤ.አ በ1955 የሊግ ሻምፒዮናውን በማሸነፍ ነበር። ከዚያም እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ ፣ 1970ዎቹ ፣ 1990ዎቹ ፣ እና 2000ዎቹ የተለያዩ ዋንጫዎችን ለማንሳት በቅተዋል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ላቅ ያለ ድል ተጎናጽፏል። ከእ.ኤ.አ 1997 ጀምሮ ደግሞ 15 ያህል ዋና ዋና ዋንጫዎችን ለማንሳት በቅቷል። በአገር ውስጥ፣ ቼልሲ አራት ውድድሮችን አሸንፏል። እነዚህም ፤ ሰባት የኤፍ ኤ ካፕ ፣ አራት የሊግ ካፕ እና አራት የኤፍ ኤ ኮምዩኒቲ ሺልድ ዋንጫዎች ናቸው። በአህጉራዊ ውድድሮች ደግሞ ፤ ሁለት የዩኤፋ ካፕ ዊነርስ ዋንጫ ፣ አንድ የዩኤፋ ሱፐር ካፕ ዋንጫ ፣ አንድ የዩኤፋ ዩሮፓ ሊግ ዋንጫ እና አንድ የዩኤፋ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆኖአል። ቼልሲ የዩኤፋ ሻምፒዮንስ ሊግን ያሸነፈ ብቸኛው የለንደን ቡድን ሲሆን፣ ሦስቱንም የዩኤፋ ውድድሮች በማሸነፍ ከአራቱ አንዱ እና ከእንግሊዝ ደግሞ ብቸኛው ቡድን ለመሆን በቅቷል።