ፈረንሳይኛ (français, la langue française) ከሚናገርባቸው አገራት መኃል: ፈረንሳይስዊዘርላንድቤኒንካሜሩንኮንጎ ሪፑብሊክኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክጅቡቲጋቦንማዳጋስካርማሊሞሪታኒያኒጄርሴኔጋልቻድቶጎ፣ ...

ፈረንሳይኛ ይፋዊ (ሰማያዊ) እና መደበኛ (ክፍት ሰማያዊ) የሆነባቸው አገሮች። አረንጓዴ በጥቂትነት የሚገኝበት ቦታ ያመለክታል።

እንደ ሌሎቹ ሮማንስ ቋንቋዎች፣ የፈረንሳይኛ አመጣጥ ከሮማይስጥ ነበር።

ሷዴሽ ዝርዝር 207 ዘመናዊ ፈረንሳይኛ ቃላት፣ 161 ወይም 78% በቀጥታ ከሮማይስጥ ቃላት ተደረጁ።

ከተረፉትም 46 ቃላት መኃል፤

  • 10 ቃላት ወይም 5% ከፍራንክኛ (ጀርማኒክ) መጡ፦ bois /ቧ/ (ደን)፤ cracher /ክራሼ/ (መትፋት)፤ gratter /ግራቴ/ (መጫር)፤ marcher /ማርሼ/ (መራመድ)፤ tomber /ቶምቤ/ (መውደቅ)፤ flotter /ፍሎቴ/ (መስፈፍ)፤ bruler /ብሩሌ/ (መቃጠል)፤ blanc /ብላንክ/ (ነጭ)፤ sale /ሳል/ (እድፋም)፤ gauche /ጎሽ/ (ግራ)
  • 1 ቃል ወይም 1% ከጋውልኛ (ኬልቲክ) መጣ፦ petit /ፕቲ/ (ትንሽ)።

የተረፉት 35 ቃላት ወይም 17% የመጡ ከሮማይስጥ ሲሆን፣ ከሮማይስጥ አዲስ ትርጉም ተሰጡ።

ደግሞ ይዩ፦ wikt:Wiktionary:የፈረንሳይኛ_ቅድመ-ታሪካዊ_አመጣጥ_-_ሷዴሽ_ዝርዝር

 
Wikipedia