1916
1916 ዓመተ ምኅረት
- መስከረም 1 ቀን፦ ደቡባዊ ሮዴዢያ (አሁን ዚምባብዌ) እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት ሆነ።
- መስከረም 2 ቀን፦ መንፈቅለ መንግሥት በእስፓንያ አገር፤ ሚጌል ፕሪሞ ዴ ሪቤራ ፈላጭ ቁራጭ፣ በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።
- መስከረም 12 ቀን፦ ጉስታፍ ሪተር ቮን ካሕር የባየርን ክፍላገር ጀርመን ፈላጭ ቁራጭ አስተዳዳሪ ሆኑ።
- መስከረም 15 ቀን፦ የብሪታንያ ጥብቅና ግዛት በዮርዳኖስና ፓለስቲና፣ የፈረንሳይም ጥብቅና ግዛት በሶርያና ሊባኖስ ይፋዊ ሆኑ።
- መስከረም 17 ቀን፦ ኢትዮጵያ የዓለም መንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽን) አባል ኾነች።
- ጥቅምት 2 ቀን፦ ቱርክ አዲስ ርዕሰ ከተማዋን ከኢስታንቡል ወደ አንካራ አዛወረች።
- ጥቅምት 12 ቀን፦ ኰሙኒስቶች በሃምቡርግ ከተማ ጀርመን በሁከት አመጹ።
- ጥቅምት 18 ቀን፦ አዲስ የቱርክ ሪፐብሊክ በድሮ ኦቶማን ግዛት ምትክ በይፋ ተመሠረተ። ኬማል አታቱርክ ፕሬዚዳንት ናቸው።
- ጥቅምት 29 ቀን፦ በጀርመን ከተማ በሚዩኒክ የቢራ አዳራሽ ውስጥ የወደፊቱ መሪና የናዚ ቡድን ሊቀ መንበር አዶልፍ ሂትለር ውጤቱ ያልተሳካ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አንቀሳቀሰ።
- ጥቅምት 30 ቀን፦ የጀርመን ፖሊሶችና ወታደሮች በሙኒክ ከተማ የቢራ አዳራሽ በናዚዎች ቅስቀሳ የተጀመረውን ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት ደመሰሱ።
- ጥር 12 ቀን፦ ሌኒን አርፈው ጆሴፍ ስታሊን የሶቭየት ኅብረት አለቃ ሆኑ።
- ጥር 17 ቀን፦ የፔትሮግራድ ስም በሶቭየት ኅብረት ወደ ሌኒንግራድ ተቀየረ (አሁንም ሳንክት ፔቴርቡርግ ነው።)
- ጥር 18 ቀን፦ የሮሜ ውል በጣልያንና የሴርቦች፣ ክሮዋቶችና ስሎቬኖች መንግሥት መካከል ተፈረመ።
- የካቲት 7 ቀን፦ የዓለም አቀፍ የንግድ ሒሣብ መሣሪያዎች ድርጅት (IBM) ስም ተመሠረተ።
- መጋቢት 7 ቀን፦ በሮሜ ውል መሠረት የፍዩሜ ነፃ ግዛት ወደ ጣልያን፣ ሱሻክ የተባለው ሠፈር ግን ወደ ሴርቦች፣ ክሮዋቶችና ስሎቬኖች መንግሥት ተጨመሩ።
- መጋቢት 16 ቀን፦ የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ እና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ራስ ተፈሪ መኮንን «ስለ ባሮች አስተዳደርና ነፃነት የቆመ ደንብ» በሚል ርእስ የተጻፈ ባለ አሥር ገጽ መመሪያ አሳተሙ።
- መጋቢት 22 ቀን፦ በኢትዮጵያ ባርያ እንዳይሸጥ፣ እንዳይገዛ የሚከለክል አዋጅ ተዋጀ።
- መጋቢት 23 ቀን፦ ሂትለር በጥቅምት መንፈቅለ መንግሥት ሞክሮ በፍርድ እወህኒ ቤት ታሠረ።
- ሚያዝያ 30 ቀን፦ ሊትዌኒያ በ1915 የያዛት ክላይፔዳ ግዛት በይፋ ለሊትዌኒያ ተጨመረች።
- ግንቦት 3 ቀን፦ ሁለቱ ጀርመናውያን ተሽከርካሪ አምራቾች፣ ጎትሊብ ዴይምለር እና ካርል ቤንዝ ኩባንያዎቻቸውን አዋሕደው አዲሱን የመርሴዲስ-ቤንዝ (Mercedes-Benz) ኩባንያ መሠረቱ።
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1880ዎቹ 1890ዎቹ 1900ዎቹ - 1910ሮቹ - 1920ዎቹ 1930ዎቹ 1940ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1913 1914 1915 - 1916 - 1917 1918 1919 |
ልደቶች
ለማስተካከልዕረፍቶች
ለማስተካከልእንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር:
ለማስተካከል- እስከ ታኅሣሥ 22 ቀን 1915 ድረስ = 1923 እ.ኤ.አ.
- ከታኅሣሥ 23 ቀን 1915 ጀምሮ = 1924 እ.ኤ.አ.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |