ቤኒን

በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ሉዓላዊ መንግስት

ቤኒን ወይም በይፋ የቤኒን ሪፐብሊክምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብ ቶጎን፣ ከምሥራቅ ናይጄሪያን እና ከሰሜን ቡርኪና ፋሶኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ ፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግን ኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።

République du Bénin
የቤኒን ሪፐብሊክ

የቤኒን ሰንደቅ ዓላማ የቤኒን አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር L'Aube Nouvelle

የቤኒንመገኛ
የቤኒንመገኛ
ቤኒን በቀይ ቀለም
ዋና ከተማ ፖርቶ ኖቮኮቶኑ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
 
ፓትሪስ ታሎን
ዋና ቀናት
ሐምሌ ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.
(August 1, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነጻነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
114,763[1] (100ኛ)

0.4
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2013 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
10,653,654[2] (84ኛ)

10,008,749
ገንዘብ ምዕራብ አፍሪካዊ CFA ፍራንክ
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +229
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .bj

የቤኒን ይፋ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን እንደ ፎንዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው። የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒን የተባበሩት መንግሥታትየአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።

ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠር የፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።

ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋም የቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።

ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርት ጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይ ካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ ኮኮነትዓሳእንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ። ፔትሮሊየምወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊ ሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች።

በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎ ዳቦኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል። አሳ እና ዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣ በሬፍየልየጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ። በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ ኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል። ቤሬ ወይም አሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ ፎርማጆኩስኩስሩዝባቄላፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።

እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል።

 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ቤኒን የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።