ጥቅምት ፳፫
ጥቅምት ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፫ኛው እና የመፀው ፳፯ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፫ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፯ ዓ.ም. - በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሩሲያ በኦቶማን ንጉዛት ላይ ጦርነት አወጀች።
- ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. - በኢትዮጵያ፣ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በድንገተኛ ሞት ከአለፉ በኋላ አልጋ ወራሹ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን ተተክተው በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ ጭነው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተባሉ።
- ፲፱፻፵፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አራዳ የተገነባውን የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ።
- ፲፱፻፶፯ዓ.ም. - የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ በአዲስ አበባ አካባቢ ማሰራጨት ጀመረ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የዓመቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ሽልማት ከ ፵ሺ የኢትዮጵያ ብር ጋር ለብሪታኒያዊው የታሪክ ምሁር፣ ባዝል ዴቪድሶን (Mr. Basil Davidson) ተሰጠ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) የታወጀውን “ብሔራዊ የሥራ ዘመቻ” እንደምትደግፍ አስታወቀች።
- ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን በየዓመቱ የማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ቀን እንዲከበር የሚያስችለውን ብሔራዊ ሕግ ፈረሙ።
- ፳፻ ዓ.ም. - በሰሜን ሸዋ አስተዳደር፣ በሀገረ-ማርያም ከሰም ወረዳ፣ ኮረማሽ አጥቢያ የሚገኘው የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ መልክ ከተገነባ በኋላ ተመርቆ አገልግሎት ላይ ዋለ።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ታዋቂው ደራሲ ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ላይ ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ)http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081102.html
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/183838 Annual Review of 1964
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/784 Annual Review of 1970
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
[* አ.አ. ሚሌኒየም ጽ/ቤት አዲስ አበባ ባለፈውና በአዲሱ ሚሌኒየም ገጽ 10-12]
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |