ስለ አውሮፓዊው/እስያዊው አገር ለመረዳት፣ ጂዮርጂያን ይዩ።

ጆርጂያ (ወይም ጂዮርጂያ) ከአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች ውስጥ አንዱ ነው። እንዲሁም ጂዮርጂያ በታላቋ ብርታኒያ ይተዳደሩ ከነበሩት 13 ግዛቶች አንዱ ነበር። «ጂዮርጂያ» የሚለውን ስሙንም ያገኘው የብርታኒያ ንጉስ ከነበረው ጆርጅ ሁለተኛ ነው።

የጂዮርጂያ ዋና ከተማ አትላንታ ሲሆን፤ ጂዮርጂያን በደቡብ ፍሎሪዳ፥ በምስራቅ አትላንቲክ ውቅያኖስ እና ደቡብ ካሮላይና፥ በምዕራብ አላባማ እንዲሁም በሰሜን ቴነሲ እና ሰሜን ካሮላይና ያዋስኑታል።