ፍራንክሊን ሮዘቨልት

ፍራንክሊን ዴላኖ ሮዘቨልት (1874-1937 ዓ.ም.) የኒው ዮርክ አገረ ገዥና የአሜሪካ 32ኛ ፕሬዚዳንት ነበሩ።

ፍራንክሊን ሮዘቨልት በ1925 ዓ.ም.

ሮዘቨልት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዉድሮው ዊልሶን ዘመን የባሕር ኅይል ምክትል ሚኒስትር ነበሩ። በ1913 ምርጫ የምክትል ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆኑ። ጄምስ ኮክስም የፕሬዚዳንት ዕጩ ነበሩ። ነገር ግን ኮክስና ሮዘቨልት በዋረን ሃርዲንግና በካልቪን ኩሊጅ ተሸነፉ። ሮዘቨልት በ1920 ዓ.ም. የኒው ዮርክ አገረ ገዥ ሆኑ።

ታላቁ ጭፍግግ ሳቢያ ፕሬዚዳንት ሄርበርት ሁቨር በጣም ስላልተወደደ በ1925 ምርጫ ሮዘቨልት ሁቨርን አሸነፏቸው። ሮዘቨልት በጣም ስለተወደደ በ1929 ዓ.ም. ምርጫ ለሁለተኛ የ4 አመት ዘመን ተመለሱ። እንዲሁም በ1933 ምርጫ ለሦስተኛ ዘመንና በ1937 ምርጫ ለአራተኛ ዘመን ተመረጡ። በጠቅላላ 4 ዘመኖች ተቀበሉ። በ2ኛ አለማዊ ጦርነትም የአሜሪካ መሪ ነበሩ። ነገር ግን ፖሊዮ ከሚባል በሽታ የተነሣ አካለ ስንኩል ሆነው ባለ መንኮራኩር ወምበር ነበራቸውና በአራተኛው ዘመን መሃል ሞቱ። ምክትላቸው ሃሪ ትሩማን ወዲያው ፕሬዚዳንት ሆኑ።

ፍራንክሊን ሮዘቨልት አራት ጊዜ በመመረጣቸው ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን ገዙ። ከሳቸው በኋላ የመንግሥት አንደኛ ዘርፍ የሆነ የሕግ አማካሪ ቤት ወደፊት ሌላ ፕሬዚዳንት እንደሱ 3 ወይም 4 ዘመናት እንዳይቀብል አንፈልግም የሚል ድምጽ አሰሙ። ስለዚህ በ1943 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት 2ኛ ዘርፍ የሆኑት ፕሬዚዳንቶች ከ2 ጊዜ (እነሱም 8 አመታት) በላይ ሊያገለግሉ አይችሉም የሚለው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 22ኛ ማሻሻያ አንቀጽ ሕጋዊ ደንብ ሆነ።