የመስቀል ጦርነቶች

የመስቀል ጦርነት
(ከመስቀል ጦርነት የተዛወረ)

የመስቀል ጦርነቶች


ዓለም ከአስተናገደቻቸው አስከፊና አሰቃቂ የፓለቲካ፣ የዳር ድንበር እንዲሁም የዘር ጦርነቶች ባልተናነሰ የአይማኖት ጦ ርነቶችንም አስተናግዳለች። ስስና አይነኬ በመባል በሚጠራው የአይማኖት ጉዳይ አማካኝ ነት ወንድም ከወንድሙ፣እህትም ከእህቶ ሳይቀር ጎራ በመክፈል እርስበርሳቸው ደም ተፋሰዋል። በዚህች የሰው ልጆች እንደመኖሪያ ቤታችን በምንጠቀምባ ት ዓለም ውስጥ ብዙ አስከፊና መራራ የአይማኖት ጦርነቶች የተካሄዱባት ሲሆን ከነሱም ውስጥ የመስቀል ጦርነት (Crusade) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በሆላ ከ1095 እስከ 1204 ባሉት 109 አመታት ውስጥ 4 የመስቀል ጦርነቶች የተደረጉ ሲሆን በነዚህም ጦርነቶች አማካኝነት ከ5 ሚሊየን ያላነሰ ህዝብ ህይወቱን አጥቶል። እነዚህ የመስቀል ጦርነቶች አብዛኞቹ በዘመኑ በነበሩ የአይ ማኖት አባቶች ወይም ጳጳሳት አማካኝነት የተመሩ ሲሆን ለጳጳሳቱ ወደn ጦርነት መግባት እንደምክንያት ሆኖ የሚ ጠቀሰውበታላቁ መፅሐፍ ወይም በመፅሐፍ-ቅዱስ ውስጥ ቅ ድስቲቶ ምድር (holly land) ተብላ የተጠቀሰችውን እየሩ ሳሌምንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞችን ከወራሪዎች እጅ ለመንጠቅ በሚል ነው። በነዚህ ተከታታይ 4 የመስቀል ጦርነትቶች ውስጥ የመስቀል

ጦረኞች በማን ተመሩ? አላማቸውስ ምነበር? እንዴትስ ተጠ

ናቀቀ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከዚህ በታች ባጭሩ እንያቸው።


አንደኛው የመስቀል ጦርነት

በPope Urban 2ኛ፣ Walter The Penniless እንዲሁ ም በPeter The Hermite በጋራ በተካሄደው የመ ጀመርያው የመስቀል ጦርነት 1095 እስከ 1099 ለ4 አመታት የፈጀ ሲሆን አላማቸውም አንቲያክንና እየሩሳሌምን ይዞ የመስቀል ጦር ግዛቶች ማድረግ ነበር ይህም አላማቸ ው ሰርቶ ጦርነቱን በአሸናፊነት አጠናቅቀዋል።


ሁለተኛው የመስቀል ጦርነት

በPope Eugenus 3ኛ፣ በEmperor Konrad 3ኛ፣በLo uis 5ኛ እንዲሁም በBerard of clarivaux ትብብር የተደረገው ሁለተኛው የመስቀል ጦርነት ከ1147 አስከ 1149 የፈጀ ሲሆን አላማውም በሙ ስሊም ጦረኞች ግዛት ስር የነበረችውን የኤዳሰን ከተማን ለመያዝ ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ በመሸነፋ ቸው አላማቸው ሳይሰምር ቀርቶል አልፎ ተርፎ ቀድሞ በቁጥ ጥራቸው ስር የነበሩትን ከተሞችንም አጥተዋል


ሶስተኛ የመስቀል ጦርነት

ይሄ ሶስተኛው የመስቀል ጦርነት በወቅቱ ስማቸው ገኖ በነበ ረው የጦር ሜዳ ጀግኖች በነ Richard The lion-He arted፣ በEmperor Fredic Barbar ossa፣ በphilip Augutus እና King of Frace ቅንጅት ከ1189 እስከ 1192 የተደረገ ጦርነት ሲሆን። በSaladin እ ጅስር የገባችውን እየሩሳሌም ዳግም ለማስመለስ የታቀደ ጦርነት ነበር። ምንም እኳን ክሩሴደሮቹ ሙስሊሞችን በሁሉም ውጊያዎች ቢያሸንፉም፤ ንጉሱ ሪቻርድ አውሮፓ ውስጥ የተፈጠረን አመፅ ለማስቆም ሲመለስ ውጊየው በመቆሙ ወደ ከተማይቱ ሳይገቡ ቀርተዋል።


አራተኛው የመስቀል ጦርነት

በ1198 በpope innocent II አማካኝነት የተጠረውና በፈ ረንሳይ የመስቀል ጦረኞች የተሳተፋበት ከ1202 እስከ 1 204 የፈጀው 4ኛው የመስቀል ጦርነት ክርስትያኖችን የኋይልና የሞራል ውድቀት ላይ ጥሎ ነው ያለ ፈው። የሙስሊሞችን ኋይል ከእስራሄልና ከአጎራባች አገሮች ማስወጣት ዓላማው አርጎ የተነሳው ይህ አራተኛው የመስቀል ጦርነት እንዳሰቡት ሳይሳካ ከመጠ ናቀቁ በላይ በቁጥጥራቸው ስር የነበሩትን የኮንስታንቲኖፕል( Constantinople) እና የዛራ(Zara) ግዛቶች አጥተውበታል።

ምንጭ => www.lemenemesekelasefelege.blogspot.com/2017/12/images-1jpg.html?m=1