መስቀል
መስቀል
መስቀል ፍቺ:- በአብዛኞቹ የሕዝበ ክርስትና ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መሣሪያ መስቀል ተብሎ ይጠራል። “ክሮስ” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የተወሰደው ክሩክስ ከሚለው የላቲን ቃል ነው። ሆኖም የመስቀል አምልኮ ከክርስቶስ ዘመን በፊትም ጀምሮ የነበረ ለመሆኑ በርካታ የጽሑፍና የሥነቁፋሮ ማስረጃዎች አሉ። የተወሰኑትን ከዚህ ቀጥሎ ማየት ይቻላል።
“ከክርስትና ዘመን በፊት ጀምሮ በሁሉም የጥንቱ ዓለም ክፍሎች የተለያየ የመስቀል ቅርጽ ያለባቸው የተለያዩ ዕቃዎች ተገኝተዋል። በሕንድ፣ በሶሪያ፣ በፋርስና በግብፅ ቁጥር ስፍር የሌላቸው መስቀሎች ተገኝተዋል። . . . ከክርስትና በፊት በነበሩት ጊዜያትና ክርስቲያን ባልሆኑት ሕዝቦች መካከል መስቀልን እንደ አንድ ሃይማኖታዊ ምልክት አድርጎ መጠቀም በመላው ዓለም ላይ የተለመደ ልማድ ነበር ማለት ይቻላል። ብዙውን ጊዜም ከአንድ ዓይነት የተፈጥሮ አምልኮት ጋር የተያየዘ ነበር።”
“[ሁለት እንጨቶች የተጋጠሙበት] የመስቀል ቅርጽ የመጣው ከጥንትዋ ከላውዴዎን ሲሆን በዚያ አገርና እንደ ግብጽ በመሳሰሉት የአካባቢው አገሮች ተሙዝ ለተባለው የጣዖት አምላክ (ታው የተባለውን የምሥጢራዊ ስሙን የመጀመሪያ ፊደል ቅርጽ የያዘ ስለሆነ) እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግል ነበር። በ3ኛው መቶ ዘመን (ዓ.ም.) አጋማሽ ላይ አብያተ ክርስቲያናት ከአንዳንዶቹ የክርስትና እምነት መሠረተ ትምህርቶች ርቀው ሄደው ወይም የሌሎችን እምነት መቅዳት ጀምረው ነበር። የከሃዲውን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ክብር ለመጨመር አረማውያን ምንም የእምነት ለውጥ ሳያደርጉ የቀድሞ እምነቶቻቸውን ከነምልክቶቻቸው እንደያዙ የቤተ ክርስቲያን አባሎች እንዲሆኑ ተፈቀደላቸው። ስለሆነም ታው ወይም ብዙ ጊዜ T ቅርጽ ያለው ሃይማኖታዊ ምልክት የክርስቶስን መስቀል የሚወክል እንዲሆን አግዳሚው ቅርጽ ከላይ ከአናቱ ዝቅ እንዲል ተደረገ።”
“እንግዳ ሊመስል ቢችልም ክርስቶስ ከመወለዱ ከረጅም ጊዜ በፊትና ከዚያም ወዲህ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ባልተዳረሰባቸው አገሮች መስቀል ቅዱስ ምልክት ሆኖ ሲሠራበት መቆየቱ የማይታበል ሐቅ ነው።
“የግብጽ ካህናትና የሃይማኖት መሪዎች ነን ይሉ የነበሩት ነገሥታት የፀሐይ አምላክ ካህናት ስለነበሩ የሥልጣናቸው ምልክት አድርገው
“በብዙ ቦታዎች ልዩ ልዩ ቅርጽ ያላቸው የመስቀል ሥዕሎች በግብጽ ሐውልቶችና መቃብሮች ላይ ተገኝተዋል። በብዙ ምሁራን ዘንድ እነዚህ የመስቀል ቅርጽ ያላቸው ምስሎች [የወንድን ብልት] ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን የሚያመለክቱ ምስሎች እንደሆኑ ይገመታሉ። . . . በግብጽ አገር በሚገኙ መቃብሮች ክሩክስ አንሳታ [ክብ ቅርጽ ያለበት ወይም ከአናቱ ላይ መያዣ ያለው መስቀል] ከወንድ ብልት ቅርጽ ጋር ጐን ለጐን ተገኝቷል።” —ኤ ሾርት ሂስትሪ ኦቭ ሴክስ ወርሽፕ (የወሲብ አምልኮ አጭር ታሪክ) (ለንደን፣ 1940)፣ ኤች ከትነር፣ ገጽ 16, 17፤ በተጨማሪ ዘ ነን ክርስቲያን ክሮስ (ክርስቲያናዊ ያልሆነው መስቀል)
“እነዚህ መስቀሎች ለባቢሎን የፀሐይ አምላክ ምልክት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የታዩት ከ100–44 ከክርስቶስ ልደት በፊት በጁሊየስ ቄሣር ዘመነ መንግሥት በተሠሩ ሣንቲሞች ላይ ነው። ከዚያ ቀጥሎ በ20 ከክርስቶስ ልደት በፊት በቄሣሩ ወራሽ (በአውግስጦስ) ዘመን በተሠሩ ሣንቲሞች ላይ ተስሏል። በቆስጠንጢኖስ ዘመን በታተሙ ሣንቲሞች ላይ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የታየው ምልክት ነው። ይኸው ተመሳሳይ ምልክት በዙሪያው ያለው ክብ ሳይጨመርበት አራት እኩል ርዝመት ያላቸው ቀጥተኛና አግዳሚ መስመሮች እንዲኖሩት ተደርጐ አገልግሏል። ይህም ‘የፀሐይ መሽከርከሪያ’ ተብሎ በተለይ ይከበር የነበረው ይህ ምልክት ነበር። ቆስጠንጢኖስ የፀሐይ አምላክ የተባለውን ጣዖት ያመልክ እንደነበረና ከሩብ መቶ ዘመን በኋላ ይህን መስቀል በሰማይ አይቻለሁ ብሎ እስከተናገረበት ጊዜ ድረስ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ እንደማያውቅ መግለጽ አስፈላጊ ነው።
በዓለ መስቀል በክርስትና ኃይማኖት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የተሰቀለበት መስቀል በአይሁድ ከተቀበረበት ሥፍራ መገኘቱን ማስታወሻ በዓል ሲሆን በምዕራብም ምሥራቅም አብያተ ክርስቲያናት ይሄንን መታሰቢያ መስከረም ፫ ቀን ሲያከብሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በየዓመቱ መስከረም ፲፯ ቀን ታከብራለች።
"መስከረም ባበባው ሠርግ በጭብጨባው ይታወቃል” ይላሉ አበው። አንድም መስከረም ርዕሰ ዓውደ ዓመት፣ የዘመን መለወጫ በመሆኑ ወርኃ አደይ ወወርኃ ጽጌ ተብሏል። እናም ኢትዮጵያውያን በርዕሰ በዓልነት ታላቅ ማዕዘን ላይ ያስቀመጡት ወርኃ መስከረም፣ ኃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን አቅፏል። ከነዚህም ውስጥ ከዕንቁጣጣሽ በዓል ቀጥሎ በሠፊው የሚታወቀው በዓለ መስቀል የተባለው ነው።
መስቀል ምንም እንኳ በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ፣ የራሱ የሆነ ትርጉም ያለው ቢሆንም ከኃይማኖታዊ ክንዋኔው ባሻገር፣ ባህላዊ በሆነ ገፅታ የሚያከብሩት የኅብረተሰብ ክፍሎች ቀላል የሚባሉ አይደሉም። ለምሣሌ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚካኼዱት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችና እሬቻ ተብሎ የሚታወቀው የኦሮሞ ህዝብ በዓል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ይኼ ጽሑፍ የሚያጤነው ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በየዓመቱ መስከረም ፲፯ ቀን ተከብሮ የሚውለውን በዓለ መስቀል ታሪካዊ ዳራ ለማስታወስና በዚህ ታሪካዊ በዓል ላይ የአንዳንድ ሊቃውንት አስተያየቶችን መጠቋቆም ነው።
ስለመስቀል በዓል አከባበር መነሾ፣ በጽሑፍና በቃል የተላለፉ መረጃዎች እንደሚነግሩን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በተአምራዊነቱና በክርስቲያኖች ምልክት ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑ፣ አይሁድ በቅንአት ተነሣሥተው ለ፫፻ ዓመታት ያህል በቆሻሻ መጣያ ጥለውት ነበር። ይሁንና በ፫፻፳፮ ዓ/ም የቄሳር ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ፣ ኪራቆስ በተባለ አንድ የታሪክ አዋቂና ሽማግሌ ጠቋሚነት፣ መስቀሉ የተጣለበትን አካባቢ ተረዳች። ከዚያም በኋላ ደመራ ደምራ በእሳት አቀጣጥላ ዕጣን ባጨሰች ጊዜ፣ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ያረፈበትን ሥፍራ አስቆፍራ መስቀሉን አውጥታዋለች።
ንግሥተ ዕሌኒ በጭሱ ምልክትነት፣ መስቀሉን ለማውጣት ለሰባት ወራት ያህል ማስቆፈሯን ማለትም መስከረም ፲፯ ቀን አስጀምራ በመጋቢት ፲ ቀን እንዳስወጣቸው ይነገራል። ዛሬ በኦርቶዶክስ ምዕመናን ዘንድ ደመራ የሚደመረውም ይህንን ታሪክ ተከትሎ እንደሆነ የሊቃውንቱ ምስክርነት አለ።
በነገራችን ላይ ስለመስቀል በዓል ስናነሳ፣ ከላይ እንደተገለጸው ሌሎችም አብያተ ክርሲያናት ቢያከብሩትም በልዩ ክብር እና ደማቅ ሁኔታ ግን የታሰበው በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘንድ ብቻ መሆኑን ማውሳት ያስፈልጋል። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወይም ክርስቲያኖች በኢየሱስ ተሰቅሎ መሞትና በመስቀሉ የማይረሳ ውለታ የሰው ልጅ መዳኑን ቢያምኑም እንደ ኦርቶዶክስና ሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ትውፊትን ስለማይቀበሉ፣ የመስቀል በዓልን ኃይማኖታዊ በዓል አድርገው አይመለከቱትም።
ወደ ተነሳንበት ነጥብ ስንመለስ፣ ስለመስቀል በዓል በአንዳንድ ሊቃውንት የተለያየ አስተያየት ሲሰነዘር ቆይቷል። ከዚህ ውስጥ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው መስቀሉን ለማግኘት ሰባት ወራት ያህል እንደፈጀ ቢነገርም በአንዳንድ ሊቃውንት ህሳቤ ደግሞ መስቀሉ የተገኘው መስከረም ፲፯ ነው ሲሉ በአጽንዖት ይናገራሉ። ይሁንና አብዛኛው የቤተክርስቲያኗ ሊቃውንት ግን “መስቀሉ የተገኘው በመጋቢት ፲ ቀን ነው፣ ይህ ወር ግን የዐቢይ ጾም ወር በመሆኑ በዓሉ በመስከረም ፲፯ ቀን እንዲሆን ሊቃውንቱ ተስማምተው አቆይተውናል” ሲሉ የላይኛውን ሃሳብ ያፈርሳሉ።
በኢትዮጵያችን ሌላው የጌታችንን መስቀል ልዩ ሥፍራ እና ክብር የሚሰጠው ጉዳይ ደግሞ በ፲፭ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዓፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የተሰቀለበት ቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ መቀመጡ ነው። ስለዚህ መስቀል መምጣት የቤተክርስቲያኗ ጸሐፍት በተለያዩ ሠነዶቻቸው የተረኩ ሲሆን፣ ንጉሡ አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን አስመጥተው በኢትዮጵያ አድባራት ሁሉ በመዞር፣ ሊያሳርፉበት ያልሞከሩበት ቦታ አልነበረም፤ ነገር ግን መሬቱ እየተንቀጠቀጠ አስቸገረ። በመጨረሻ ግን “አንብር መስቀልዬ በዲበ መስቀል። (መስቀሌን በመስቀልያ ሥፍራ አስቀምጠው)” የሚል መለኮታዊ ምሪት ስለደረሳቸው፣ አሁን ግሼ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ መስከረም ፳፩ ቀን ፲፬፻፵፮ ዓ/ም አሳረፉት። የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ሥፍራ መስቀልያ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው ነው።
"እግዚአብሔር ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ያስብልን፤ ህዝቦቹንም ይጠብቀን፡፡"
ምንጮች
ለማስተካከል- http://www.ethiopiazare.com/history/63-history/503-meskel Archived ሴፕቴምበር 21, 2010 at the Wayback Machine