ጊኔ-ቢሳው
ጊኔ-ቢሣው የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ነው። የጊኔ-ቢሣው ብሄራዊ ቋንቋ ፖርቱጊዝኛ ሲሆን ፉላኒኛ፣ ባላንታኛ እና ማንዲንግኛ በብሔሮቻቸው ይነገራሉ። የጊኔ ቢሣው ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል መደበኛ ነው።
República da Guiné-Bissau |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Esta é a Nossa Pátria Bem Amada |
||||||
ዋና ከተማ | ቢሳው | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፖርቱጊዝኛ | |||||
መንግሥት {{{ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ሖሴ ማሪዮ ቫዝ ኡማሮ ሲሦኮ ኤምባሎ |
|||||
ዋና ቀናት መስከረም ፲፬ ቀን 1966 ዓ.ም (Sep. 24, 1973 እ.ኤ.አ.) |
ነፃነት ከፖርቱጋል ታወጀ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
36,125 (134ኛ) 22.4 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት |
1,547,777 (150ኛ) |
|||||
ገንዘብ | CFA ፍራንክ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | +245 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .gw |
ከሀገሩ ኗሪዎች 45% ያህል የእስልምና ተከታዮች (በተለይ ሱኒ)፣ 22% ያህል የክርስትና አማኞች (በተለይ ካቶሊክ)፣ 31 % አካባቢ ኗሪ አረመኔ እምነቶችን ይከተላሉ። በጊኔ-ቢሳው ባሕል በርካታ የሙዚቃ ስልቶች በተለይም ጉምቤ የሚባለው ስልት አሉ። የሀገሩ ባሕላዊ አበሳሰል ሩዝ፣ ጥቁር-ዓይን አተር፣ ኮቴሃሬ፣ ስኳር ድንች፣ ካሳቫ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ሙዝ ጥብስ፣ ኮረሪማ ይመርጣል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው።
ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ ዓሣ፣ ኦቾሎኒና ሌላ ለውዝ አይነቶች፣ እንጨት ናቸው።