የፀሐይ ግርዶሽ የሚከሰተው የተወሰነው የመሬት ክፍል በጨረቃ ጥላ ስር ሲዎድቅ ነው። መሬት፣ ጨረቃ እና ፀሐይ በአንድ መስመር ላይ ሆነው ሲቀመጡ፣ የፀሐይ ብርሃን በከፊል ወይም በሙሉ በጨረቃ ይጋረዳል። ይህ ሁኔታ መሬት ላይ የቀን ጨለማ ይፈጥራል። የፀሐይ ግርዶሽ አራት ዓይነቶች ሲኖሩት እነርሱም፦

  1. ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ
  2. ማዕከላዊ የፀሐይ ግርዶሽ
  3. ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ
  4. ድቅል የፀሐይ ግርዶሽ


የተጋረደችውን ፀሐይ በዓይን ማየት ቀላል ቢሆንም በዓይን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ለማየት በሚፈልጉ ሰአት የእይታ መነፀር ይጠቀሙ።