ፋሲካ
ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው።
ስሙ ፋሲካ የመጣው ከአረማይክ /ፓስኻ/፣ ግሪክኛ /ፓስቃ/፣ ዕብራይስጥ /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ "እግዚአብሔር ያልፋል" ሲል፥ "ያልፋል" የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ፋሲካ ከዚያው ቃል ደረሰ።
በአዲስ ኪዳን ዘንድ ደግሞ ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል አዲስ ትርጉም ሰጠው። በመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበዓሉን ዝግጅት ሲጠብቅ ሥጋ ወደሙ እንደ መስዋዕቱ ሆኖ ባካፈለው ኅብስትና ወይን በኩል እንደሚገኝ አመለከተ። ኢየሱስም ተሰቅሎ ከ፫ ቀን በኋላ ተነስቶ ዳግመኛ ለደቀመዛሙርቱ ታይቶ፣ በነዚህ ዘመኖች ፍፃሜ ለፍርድ ቀን በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመለስ ነገራቸው። ይህ ሁሉ አሁን በክርስትና ወይም በአብያተ ክርስቲያናት በፋሲካ በዓል የሚከበር ነው። በፋሲካ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን፤ ማለትም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋዬን ቆርሼ ደሜን አፍስሼ አድንሀለሁ ባለው ቃል መሰረት፤ ወደዚህ አለም ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኖ አዳምን ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ሊያወጣው፤ የአዳምን በደል እርሱ ሊክስ የተሰቀለበት ጊዜ ይታሰብበታል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
በፋሲካ ከሚደረጉ ነገሮች አሉ።