ሐምሌ ፭
ሐምሌ ፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፭ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፲ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፩ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፴፫ ዓ/ም - ኢትዮጵያን ለመርዳት የተላከው የብርቱጋል ሠራዊት በዕለተ ቅዳሜ ምጽዋ ላይ አረፈ። ክረምቱንም ካሳለፈ በኋላ የዓፄ ልብነ ድንግል ሚስት ከነበሩት እቴጌ ሰብለ ወንጌል ወዳሉበት ተጓዙ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ደሴቶች ከብርቱጋል ነፃነታቸውን አወጁ።
- ፳፻፭ ዓ/ም - በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ- ኤ ኦ ፒ (ET-AOP) የተመዘገበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አየር ዠበብ በዛሬው ዕለት በሎንዶን 'ሂዝሮው' ጥያራ ጣቢያ እንደቆመ የእሳት አደጋ ደረሰበት። ይኽ አደጋ የተከሰተው ጥያራው መንገደኞችን አሣፍሮ ከአዲስ አበባ ከገባ ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/July_12
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |