መስከረም ፲፯
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰዎ!
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፯ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፫፻፵፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፫፻፵፰ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የተሰቀለበትን መስቀል ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት ቁፋሮ የተጀመረበትን ዕለት በማስታወስ በሰፊው እና በደመቀ ስርዓት ታከብራለች።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - በትልቁ የመስቀል በዓል ቀን መኳንንቱ ከነሠራዊቱ፤ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስና እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ ከነካህናቱ በተሰበሰቡበት በ ፲ ነጥብ የተዘረዘረው የልጅ እያሱ ወንጀል ተነቦ እሳቸውን ሽረው ወይዘሮ ዘውዲቱን ንግሥት፣ ደጃዝማች ተፈሪን ራስ ብለው አልጋ ወራሽና የመንግሥቱ እንደራሴ ተደረጉ። [1]
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ የዓለም መንግሥታት ማኅበር/ ሸንጎ (ሊግ ኦፍ ኔሽን) አባል ኾነች።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - ሴየራ ሌዎን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በፋሺስት ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን በመደገፍ በእንግሊዝ አገር እርዳታ በመሰብሰብ፣ የኢጣልያን ግፍ እና የምዕራባውያንን ድክመት በማጋለጥ የታገሉት ዕመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተገኙበት በመንግሥታዊ ሥርዓት በኢጣሊያ ጦርነት ሰማዕት ለሆኑ ጀግኖች በተዘጋጀው መካነ መቃብር፣ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” (፲፱፻፳፱ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |