የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር

1989
(ከዘመነ ማርቆስ የተዛወረ)

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ።

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።

የበዓላት አከባበር በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚከበሩ በዓላት ብዙውን ጊዜ ከግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር በ7 ዓመታት ይዘገያሉ። ለምሳሌ፣ የገና በዓል በጥር 7 ቀን ይከበራል፣ ይህም ከግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር ጥር 1 ቀን ጋር ይመሳሰላል።

የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ. ሆነ።

የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም።

በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ። [1] Archived ኦክቶበር 6, 2008 at the Wayback Machine [2] [3] Archived ጃንዩዌሪ 25, 2016 at the Wayback Machine ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው። [1][4] Archived ኦክቶበር 6, 2008 at the Wayback Machine

የወራት አቆጣጠር የተወረሰ ከቅብጢ ዘመን አቆጣጠር፣ ይህም የወጣ ከጥንታዊ ግብጽ ዘመን አቆጣጠር ነው። ሆኖም የወሮች ስሞች በግዕዝ ተለውጠዋል።

ti ጎርጎርዮስ በሰግር ዓመት
መስከረም ሰፕቴምበር 11 ሰፕቴምበር 12
ጥቅምት ኦክቶበር 11 ኦክቶበር 12
ኅዳር ኖቨምበር 10 ኖቨምበር 11
ታኅሣሥ ዲሰምበር 10 ዲሰምበር 11
ጥር ጃንዋሪ 9 ጃንዋሪ 10
የካቲት ፈብርዋሪ 8 ፈብርዋሪ 9
መጋቢት ማርች 10 ማርች 10
ሚያዝያ ኤፕሪል 9 ኤፕሪል 9
ግንቦት ሜይ 9 ሜይ 9
ሰኔ ጁን 8 ጁን 8
ሐምሌ ጁላይ 8 ጁላይ 8
ነሐሴ ኦገስት 7 ኦገስት 7
ጳጉሜ ሰፕቴምበር 6 ሰፕቴምበር 6


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
  1. ዘመነ ማቴዎስ
  2. ዘመነ ማርቆስ
  3. ዘመነ ሉቃስ
  4. ዘመነ ዮሀንስ

የውጭ መያያዣዎች

ለማስተካከል
  1. ^ ኣበራ ሞላ