ጀርመን ወይንም በይፋ ስሙ የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በመካከለኛ አውሮፓ የሚገኝ ታሪካዊ አገር ነው። አገሩ 16 ክልሎች ሲኖሩት ዋናና ትልቁ ከተማውም በርሊን ነው።

የጀርመን ፌድራላዊ ሪፐብሊከ ባንዲራ_ሥዕል = Flag of Germany.svg

የጀርመን ሰንደቅ ዓላማ የጀርመን አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ዶይችላንድሊድ
Deutschlandlied

የጀርመንመገኛ
የጀርመንመገኛ
ዋና ከተማ በርሊን
ብሔራዊ ቋንቋዎች ጀርመንኛ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
ቻንስለር
ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ
ፍራንክ-ቫልተር ሽታይንማየር
ኦላፍ ሾልዝ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
357,021 km2 (63ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
 
82,521,653 (16ኛ)
ገንዘብ ዩሮ (€)
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +49
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .de


በ100 ዓም በፊት እነኚህ ጎሳዎች "ጀርመኒያ" የተባለች ትንሽዬ ግዛት እንዳቋቋሙ በታሪክ ይገለፃል። ጀርመን መካከለኛውን የአውሮፓ ክፍል ይዛ እንደ ሀገር መቋቋም የጀመረችው በቅዱስ ሮማን ግዛት በ10ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። ይህ ግዛት የጀረመን "የመጀመሪያው ራይክ" ተብሎ ይጠራል። ይህ ግዛት ከፍራንኮች (ፈረንሳይ) ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት ውስጥ በመግባት የቅዱስ ሮማን ግዛት በናፖሊያ ጦርነት በ1806 ዓም ሊፈርስ ችሏል። ከዛም በኋላ የጀርመን ኮንፌድሬሽን ጥቂት ግዛቶችን በመያዝ መቋቋም ጀመረ። በመካከለኛው ዘመን በሀይማኖት አስተምሮት ችግር ሳቢያ የፕሮቴስታንት እምነት ከካቶሊክ ተገንጥሎ መውጣት ጀመረ። በኢንላይትመንት ጊዜ፣ ጀርመኖች አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍለቅ ጀመሩ፣ የካቶሊክ መንግስትን ለመገርሰስ ሲባል የኢሉሚናቲ ማህበር በ1776 ዓም ተመሰረተ። ይህም ማህበር በዚሁ ስራ ቢሳካለትም አላማው ደግሞም የአለምን ሀኔታ ለመቆጣጠር፣ የሀይማኖትን ህልውና ለማጠልሸት እና የኒው ወርልድ ኦርደር አምባገነናዊ የአለም መንግስት ለመመስረት ነበረ።

በ1871 ዓም የጀርመን ግዛት ተቋቋመ። ይህም "ሁለተኛው ራይክ" ተብሎ ይጠራል። ይህ ግዛት ጀርመንን ቀኝ እንድትገዛ እና ጀርመናዊ/ኖርዲካዊ የወደቁት መልዐክት ለማስፋፋት ነበረ የታሰበው። ምስራቃዊ የአውሮፓ ግዛቷ ፕሩዥያ ኢምፓየር ይባላል። በአንደኛው የአለም ጦርነት በኋላ የጀርመን ግዛት ከኦስትሮ ሀንጋሪ፣ ከኦቶማን ኢምፓየርና ከቡልጋሪያ ጋር በመግጠም፣ በአላይድ ፓወር ተሸነፈች። ከ1918 እስከ 1919 ዓም በተደረገው አብዮት የጀረመን የዘውዳዊ ግዛት ወደ ፌድራላዊ ዌማር ሪፐብሊክ ከ1918 እስከ 1933 ዓም ስትመራ ነበር። ጀርመን ቀደም ሲል በአንደኛው የዓለም ጦርነት በገጠማት የድንበር መጥበብ ምክንያት ሰይጣናዊው አምባገነናዊው የናዚ መንግስት በአዶልፍ ሂትለር ተጀመረ። ይህም ጊዜ "ሶስተኛው ራይክ" ተብሎ ይጠራል።

ናዚ ጀርመን፣ ፋሺስት ኢጣሊያ እና የጃፓን ስርወ መንግስት የአንድዮሽ አምባገነናዊ የአለም መንግስት መመስረት ፍላጎት ቢኖራቸው ነገር ግን የነሱ ተቃራኒ የሆኑት አላይድ ፓወሮች አንድ ላይ ተቀናጅተው ይህንን ስርአት ለመመስረት ያቀረቡትን ጥያቄ ስለተቃወሙት ነበር ወደ ጦርነት የገቡት። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ሽንፈት፣ የጀርመን የጣሊያንና የጃፓን መንግስት ወደ ሊብራል ዴሞክራሲ ተለወጠ። ጀርመን ከ 1958 ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት አባል ነው ፣ እና ከተቀረው የምእራብ ጂኦግራፊያዊ ጎን ለጎን ፈጠራን ቀጥሏል። በሴፕቴምበር 1973 ምዕራብ ጀርመን የተባበሩት መንግስታት አባል ሆኑ። እ.ኤ.አ. በ 1991 የሶቪየት ኅብረት ውድቀትን ተከትሎ ፣ ጀርመን እንደገና ከተገናኘች በኋላ በአውሮፓ ህብረት እና በአውሮፓ አህጉር ውስጥ በጣም የበለፀገች ሀገር ሆናለች።

ባህልና ጠቅላላ መረጃ ለማስተካከል

ጀርመን አንድ ይፋዊ ቋንቋ ብቻ አለው እርሱም ጀርመንኛ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የጀርመንኛ ቀበሌኞች በአገሩ ይገኛሉ። ለአንዳንድ ሰዎች ጀርመን «የገጣሚዎችና የአሳቢዎች አገር» በመባል ታውቋል። በዓመታት ላይ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብ፣ በፍልስፍና፣ በሙዚቃ፣ በሲኒማ፣ እና በሳይንስ ዘርፎች በርካታ አስተዋጽኦች በማቅረባቸው ጀርመናውያን በዓለም ዝነኛነት አገኝተዋል፤ እንዲሁም መኪና የሚባለውን ፈጠራ በማስለማት ፈር ቀዳጅ ሆኑ። ጀርመን ደግም ስለ ቋሊማቢራዎች ልዩነት ብዛት የገነነ ሆኗል። እግር ኳስ በጀርመን ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው።

ራይን ወንዝ አቅራቢያ በጥንት ከሁሉ በፊት የተሰፈረው ሲሆን እዚያ አንዳንድ ጥንታዊ የሮሜ መንግሥት ድልድይ፣ አምባ፣ ወይም ፍርስራሽ ሊታይ ይችላል። የጀርመን ሕዝብ በብዛት ክርስቲያኖች ናቸው፤ በስደትም ወደ አገራቸው ለደረሱት ሰዎች በጠቅላላው ሰላምታ ሰጪዎች ናቸው። የበርሊን ግድግዳ በፈረሰበትና «የቅዝቃዛ ጦርነት» በጨረሰበት ወቅት የጀርመን ዳግመኛ መወሐድ ተከሠተ። በዚያ ሰዓት የቀድሞ አገራት ምሥራቅ ጀርመንምዕራብ ጀርመን አብረው የአሁኑን ጀርመን መንግሥት ፈጠሩ።

ብዙ የጀርመን ሰዎች በዓለም ዙሪያ ስመ ጥሩ ናቸው። ይህም ደራሲዎች ያኮብ ግሪምና ወንድሙ ቭልሄልም ግሪም፣ ባለቅኔው ዮሐን ቩልፍጋንግ ቮን ጌጠ፣ የፕሮቴስታንት ንቅናቄ መሪ ማርቲን ሉጠር፣ ፈላስፋዎች ካንትኒሺሄገል፣ ሳይንቲስቱ አልቤርት አይንስታይን፣ ፈጠራ አፍላቂዎች ዳይምለርዲዝልካርል ቤንዝ፣ የሙዚቃ ቃኚዎች ዮሐን ሴባስትያን ባክሉድቪግ ቫን ቤትሆቨንብራምዝስትራውስቫግነርና ብዙ ሌሎች ይከትታል።

እጅግ ቁም ነገር የሆነ ጠቃሚ ፈጠራ ማሳተሚያዮሐንስ ጉተንቤርግ በሚባል ሰው በ1431 ዓ.ም. ተጀመረ። ስለዚህ ተጓዦች ከውጭ አገር ሲመልሱ በአውሮፓ ያለው ሰው ሁሉ እርግጡን በቶሎ ያውቀው ነበር። አሁን ጀርመን «ዶይቸ ቨለ» በሚባል ራዲዮን ጣቢያ ላይ ዜና በእንግሊዝኛ ያሠራጫል። የጀርመን ሕዝብ ባማካኝ ከአውሮፓ ሁሉ ቴሌቪዥንን የሚወድዱ ሲሆኑ ፺ ከመቶ ሰዎች ወይም ሳተላይት ወይም ገመድ ቴሌቪዥን አላቸው።