ግንቦት ፳፮
ግንቦት ፳፮ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፷፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፺፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የ’ኤየር ፍራንስ’ ‘ቦይንግ’ ፯፻፯ አየር ዠበብ ከፓሪስ ኦርሊ ማረፊያ ተነስቶ ወደ አትላንታ ለመብረር ሲነሳ በደረሰበት አደጋ ፻፴ መንገደኞችና የዓየር መንገዱ ባልደረቦች ሞተዋል።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የአሜሪካው ‘ኖርዝ ዌስት ኤየርላይንስ’ (Northwest Airlines) ዲ-ሲ-፯ አየር ዠበብ በረራ በሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ ውድቆ ሲሰምጥ ፻፩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኮንኮርድ አየር ዠበብ አምሳል የተሠራው የሶቪዬት ቱፖሌቭ ቲ-ዩ-፻፵፬ (Tupolev Tu-144) ፈረንሳይ ላይ በደረሰበት የበረራ አደጋ ሲከሰከስ ፲፬ ሰዎች ሞተዋል።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፯፻፷፭ ዓ/ም - የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ በዚህ ዕለት አርፈው በቁስቋም ደብረ ጸሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/June_3
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |