ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ስትሆን: በስሜን-ምዕራብ ከሱዳን፣ በሰሜን-ምስራቅ ከቀይ ባህር፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ-ምስራቅ ጅቡቲ ጋር ድንበር ትካለላለች። ኤርትራ የሚለው ስም ከላቲኑ «Mare Eritreum» የተወሰደ እና ስረ-መሰረቱ የግሪኩ Ἐρυθρὰ θάλαττα ሐረግ ሲሆን ትርጉሙም ቀይ ማለት ነው። ይህን ስም ለአካባቢው የሰጡት ጣሊያኖች በጥር ፲፰፻፺ ቅኝ ግዛታቸውን ሲያውጁ ነበር (ተመሳሳይ ስም በጀርመኖች 1870 እና ግብጾች ፲፰፻፷ወቹ በጥቅም ላይ ውለዋል፣ ነገር ግን የትኛውን ክፍል ስሙ እንደሚመለከት ግልጽ አልነበረም)። ኤርትራ፣ እንደ ሐገር፣ በጣሊያኖች ከተመሰረተች በኋላ በ5 ልዩ ሂደቶች ውስጥ በማለፍ ነው ያሁኑን ቁመናዋን የያዘችው። ከ1890 በፊት የነበረው የአካባቢው ታሪክ በ«ኤርትራ» ስር የሚጠና ባህይሆንም ስለአዲሱ ኤርትራ ግንዛቤ ስለሚያስጨብጥ ታሪክ ተመራማሪዎች ከ፲፰፻፺ በፊት ያለውንም ታሪክ ማጥናት ተገቢ እንደሆነ ይስማማሉ። ማንም የአፍሪካ ሃገር በቀኛ ገዥወች ስም አልተጠራም ከኤርትራ በስተቀር

ሃገረ ኤርትራ
State of Eritrea
ስቴት ኦፍ ኤሪትሪያ
دولة إرتريا
ዳውላት ኢሪትሪያ

የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ የኤርትራ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ኤርትራ ኤርትራ ኤርትራ
የኤርትራመገኛ
የኤርትራመገኛ
ኤርትራ በቀይ ቀለም
ዋና ከተማ አስመራ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ትግርኛአረብኛእንግሊዝኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
 
ኢሳይያስ አፈወርቂ
ዋና ቀናት
ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ.ም.
(May 24, 1991 እ.ኤ.አ.)
ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም.
(May 24, 1993 እ.ኤ.አ.)
 
የነፃነት ቀን ከኢትዮጵያ (በተግባር)


የነፃነት ቀን ከኢትዮጵያ (በሕግ)
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
፲፪፼፲፫፻፳ (፻፲ኛ)
0.14
የሕዝብ ብዛት
የ፳፻፲፪ እ.ኤ.አ. ግምት
የ2008 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
፮፻፰፼፷፬፻፺፭ (107ኛ)
5,291,370
ገንዘብ ናቕፋ
ሰዓት ክልል UTC +3
የስልክ መግቢያ +፪፻፺፩
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .er

አካባቢው( ከ1890 በፊት)

ለማስተካከል
 

ክዴቭ ፓሻ

ለማስተካከል

በ1860ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ፣ የግብጹ መሪ ኢስማኤል ከዴቭ ፓሻ በናይል ተፋሰስ ላይ ሰፊ የግብጽ ቅኝ ግዛት ለማበጀት ተነሳ። ለዚህ አዲሱ ግዛቱ ካርቱምን ዋና ከተማው በማድረግ የሱዳን ግዛቱን አጸና። ቀጥሎም የቀይ ባህርን ጠረፎች በ1865 ከተቆጣጠረ በኋላ በ1870ዎቹ መጀመሪያ ሐረርንና ተሻግሮ ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ግዛቶችን አበጀ። እንግዲህ በኒህ ግዛቶቹና በሱዳን መካከል የነበረው ብቸኛ መገናኛ መንገድ ካርቱም-ከሰላ- ከረን -ምፅዋ ብሎ የሚዘልቅ ነበር። ስለሆነም በ1872 ይህን ስልታዊ መንገድ የክዴቭ ፓሻ ሰራዊቶች ተቆጣጠሩ።

መቆጣጠር ብቻ አይደለም በየመንገዱ ምሽግ እየሰሩና የአውሮጳ ምስዮናውያንን እርሻ ቦታ እየሰጡ ቅኝ ግዛት አበጁ። በዚህ ሳይቆጠቡ፣ የመንገዱን ደህንነት ዋስትና ለማስጠበቅ ሲሉ የአካባቢውን ደጋማ ክፍል መያዝ ግድ አላቸው። ደጋማው ክፍል በዚህ ወቅት በአጼ ዮሐንስ ግዛት ስር ነበር።

ሦስቱ ማዕከላት

ለማስተካከል

ግብጾቹ አካባቢውን ለቅኝ ግዛታቸው ብለው አንድ ከማድረጋቸው በፊት በዚህ መልክዓ ምድር ሦስት እራሳቸውን የቻሉ ማዕከላት በታሪክ ይጠቀሳሉ። ታሪክ አጥኝው ካህሳይ ብርሐኔ እኒህን ሦስት ማዕከላት የጋራ ታሪክ የሌላቸው፣ ኢ-ጥገኛ ህዝቦች ይላቸዋል።

 
ራስ አሉላ እንግዳ(1827-1897)
 
የራስ አሉላ መኖሪያ፣ አስመራ

የመጀመሪያው ማዕከል በምዕራብ ቆላማ ክፍል የሚገኘው ሲሆን፣ ከመልክዓምድር አንጻር ከከሰላ እስከ ቦጎስ ያለውን ቦታ ያካልላል። በተለምዶ ባርካ የሚባለው ነው። ይህ ክፍል ትግረ ቋንቋ በሚናገሩ የቤኒ አሚር ጎሳዎች የሚመራ ቢሆንም በውስጡ ሌሎች ብሔሮችን አጠቃሎ ይዟል። አካባቢው ከደጋው የአሁኑ ኤርትራ ክፍል ይበልጥ ከሱዳኖች ጋር የበለጠ ጥብቅ ትሥሥር ነበርው። ለዚህ ምክንያቱ በ1820ዎቹ ሚርጋኒያን የእስልምና እምነትን ለቤኒ አሚሮች በመስበክ ስላስፋፉ ነበር። ሚርጋኒያ ወየም የሚርጋኒያ ቤተሰቦች ከሰላ ውስጥ ሃትሚያ በተባለ የሱፊ እስልምና ማዕከል ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ የአንድ ቤተሰብ ሰወች ነበሩ።

 
ራስ ወልደሚካኤል ሰሎሞን

ሁለተኛው ማዕከል ከምዕራቡ ክፍል በቋንቋም ሆነ በብሔር በጣም የተለየ ነው፣ የሚገኘውም በስተምስራቅ፣ በቀይ ባሕር ጠረፍ አካባቢ ነው። መጀመሪያ ደረጃ፣ ይህ የጠረፍ አካባቢ በስመ አዱሊስአክሱም ዋና ግዛት ነበር። ሆኖም ከ8ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አካባቢው በእስልምና ምህዋር ስር በመውደቁ (የዳህላክ ሡልጣኔት፣ ለምሳሌ)፣ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ግዛት አፈነገጠ። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ነገሥታት (ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለምሳሌ) አልፎ አልፎ አካባቢውን በማስመለስ በባሕር ምድር ስም የባሕረ ነጋሽ ግዛት አድርገው ቢያስተዳድሩትም ከ8ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የያዘውን መልክ ሊቀይር አልቻለም ። የዚህ አካባቢ ዋና ማዕከል ምፅዋ የነበረ ሲሆን በምጽዋ አረቦች ቤታቸውን ሰርተው የእስልምና ማዕከል አድርገውት ነበር። ይህን የእስልምና ማንነት በሚያፀና መልኩ ኦቶማን ቱርኮች ምጽዋን ከ1557 እስከ 1578 ባደረጉት ዘመቻ ተቆጣጥረው የቀይባሕር እስላማዊ ቅኝ ግዛታቸው አካል አደረጉት። በአካባቢው በረሃወች የሚኖሩት አፋሮች የእስልምናን ስርዓት መያዝ የጀመሩት በዚሁ ዘመን፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነበር።

ሦስተኛው ማዕከል በሁለቱ መሃል የሚገኘው ተራራማው የሐማሴንሰራየ እና አካለ ጉዛይ ግዛት ሲሆን በዚህ ቦታ ትግርኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖች ይገኙበታል። በተለምዶ መረብ ምላሽ የሚባለው ነው። ይህ ክፍል ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ዋና ክፍል የነበረ ነው። በአክሱም ዘመነ መንግስት የግዛቱ አይነተኛ ክፍል፣ እንዲሁም የሥርዓተ ገዳምና የክርስትና ዋና ማዕከል ነበር። ከአክሱም በኋላም ባሕር ምድር ተብሎ የሚታወቀው ግዛት ዋና እምብርት ነበር። ክፍሉ በኢትዮጵያ ከሚገኘው ሌላው የትግርኛ ተናጋሪ ጋር ካለው ቁርኝት አንጻር የሚለየው የነበር በሁለቱ ክፍሎች መካከል በሚጓዘው መረብ ወንዝ ነበር። ስለሆነም መረብ ምላሽ ተብሎ ይታወቅ ነበር። እንደማንኛው ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል፣ የዚህ አካባቢ ታሪክ የሚያጠነጥነው ከመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር በነበረው ግንኙነት ዙሪያ ነበር። የመረብ ምላሽ ዋና ክፍል ሐማሴን ሲሆን ይህ ክፍል ለዘመናት ይተዳደር የነበረው በሁለት ተፎካካሪ ቤተሰቦች ነበር፡ እነርሱም ሓዛጋ እና ሳዛጋ በመባል ይታወቃሉ። ይህ ክፍል አንድ አንድ ዘመቻወችን ወደ ቆላው ቢያደርግም፣ አልፎ አልፎም ከውጭ ሃይሎች እርዳታ ቢያገኝም፣ በአጠቃላይ ግን የአስተዳደሩ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ባህልንና ትውፊትን የተከተለ ነበር።

አጼ ዮሐንስ፣ ግብጾች፣ መሃዲስቶች እና ጣሊያኖች

ለማስተካከል

ይህ በዚህ እንዳለ ነበር ግብጾች (ክዴቭ ፓሻ) እኒህን ሶስት ክፍሎች አንድ በማድረግ ከኢትዮጵያ ለይተው ለመግዛት የሞከሩት። ከላይ እንደተጠቀሰው ግብጾች ከከሰላ ምጽዋ የሚዘልቀውን መንገድ ቅኝ አድርገው ነበር ሆኖም ግን ለጸጥታ ሲሉ የደጋውን ክርስቲያን ክፍል ለመቆጣጠር ሞክሩ። በዚህ ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ገቡ። በኖቬምበር 16፣ 1875 ላይ የአጼ ዮሐንስን ሰራዊት ጉንደት በተባለ ቦታ ገጥመው ተሸነፉ። ማርች 1-9፣ 1876 ላይ እንደገና ጉራ በተባለ ቦታ ገጥመው ከፍተኛ ሽንፈት ገጠማቸው። ይህን አይነት ክስረት ከገጠማቸው በኋላ ደጋውን ክፍል ትተው ድሮ በነበሩበት ምጽዋ-ከሰላ፣ በተለይ ቦጎስ ፣ መንገድ ላይ ተወሰነው በኢትዮጵያውያን ላይ የደፈጣ ውጊያ ማድረግ ቀጠሉ። ጠንክረው ለመከላከል ሲሉ፣ አጼ ዮሐንስ መረብ ምላሽን ለመያዝ አሰቡ፤ ስለሆነም በ1876 ዓ.ም. ራስ አሉላ እንግዳን የመረብ ምላሽ ገዥ አድርገው ሰየሟቸው። ራስ አሉላ በአገሬው ሰው እንደ ጸጉረ ልውጥ ተደርገው በመቆጠራቸው ነገሩ ቅሬታን ፈጠረ። ስለሆነም የመረብ ምላሽ የቀደመ ገዥ የነበሩት ራስ ወልደሚካኤል በግብጾች እርዳታ ሐማሴንን ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችለው ነበር። ራስ ወልደሚካኤል በ1879 ተማርከው ለእስር ተዳረጉ። ነገሮች እንዲህ ከተደላደሉ በኋላ ራስ አሉላ በግብጾች ምሽጎች ላይ አልፎ አልፎ ዘመቻ በማድረግ ጥቃት ማድረስ ጀመሩ። በመካለሉ ማሃዲ ሱዳኖች በግብጾች ላይ በመነሳታቸው ግብጾች ከሁለት ጎን አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ። ከአጣብቂኙ ለመገላገልና ከአካባቢው በሰላም ለመውጣት ሲሉ ግብጾቹ በ1884 ከአሉላ ጋር የሄዌት ስምምነት የተባለውን ውል ተፈራረሙ።

ብዙም ሳይቆይ፣ ከአመት በኋላ፣ ታኅሣሥ 1885 ላይ ጣሊያኖች ምፅዋ ላይ መልህቃቸውን ጥለው ወደ መሃል መስፋፋታቸውን ጀመሩ። መስከረም 1885 ላይ አሉላና የሱዳን መሃዲስቶች ኩፊት በተባለ ቦታ ተገናኝተው ራስ አሉላ ጦርነቱን በድል ቢደመድሙም ከሰላን ለመቆጣጠር የነበራቸው እቅድ በጣሊያኖች ወደ ምጽዋ ዘልቆ መግባት ተዘናጋ። ፊታቸውን ከምዕራቡ ግንባር በመመለስ፣ ራስ አሉላ፣ ጣሊያኖችን በዶገሊ (1887) ጦርነት እንዲሁም በኮዓቲት(1888) ጦርነት ድል አደርጓቸው። ይሁንና የጣሊያኖች መስፋፋት ሊገታ አልቻለም። ለዚህ ምክንያቱ በምዕራብ የመሃዲስቶች ጦርነትና እንዲሁም የጣሊያኖች በሃይል መጠናከር ነበር። በኒህ ድርብ ጫናዎች ምክንያት 1888 ላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት አፈግፍጎ መረብ ወንዝን ተሻገረ። 1889 ዓ.ም. ያለመንም ጦርነት የጣሊያን ሰራዊት አስመራ ገባ።

እንግዲህ በዚህ ዘመን የተፈጠረው የምዕራብ ኤርትራ(ባርካ)፣ የምጽዋዕ እስላሞች፣ የሱዳንና የግብጽ ግንኙነት ነበር በኋላ በ1950ወቹ ለተነሳው የኤርትራ ነጻነት ግንባር ጀብሃ የሚለውን አላማ መሰረት የሆነው። የኤርትራ ህዝቦች ነጻነት ግንባርም የአሉላን ጸጉረ ልውጥነትና በህዝቡ ዘንድ ያስነሳውን ማንጎራጎር እንደ-የመረብ ምላሽ ህዝብ ነጻነት ጥያቄ መነሻ አድርጎ ይወስደዋል። ይህ የታሪክ ክፍል የቱን ያክል ለ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያና የኤርትራ ታሪክ ሚና እንደነበረው ለመገንዘብ አዳጋች አይደለም።

 

ኮሎኒያ ኤርትራ (፲፰፻፺-፲፱፻፵፩)

ለማስተካከል

የጣሊያኖች መስፋፋት

ለማስተካከል

የጣሊያን መንግስት በደቡብ ምዕራብ ቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ከአንድ የመርክብ ኩባንያ ቦታዎችን በመግዛት በመሬቱ ላይ የሕጋዊ ይገባኛልን አጸና። እንዲሁም ከአካባቢው መሪዎች ጋር ውል በመፈራረም አሰብንና ቅርብ ደሴቶቿን ሐምሌ 1882 ቅኝ ግዛቶቹ እንደሆኑ አወጀ። ይህ እንግዴህ ኮሎኒያ አሰብ የሚባለው ነው። ከሶስት አመት በኋላ፣ የካቲት 1885 በእንግሊዞች መልካም ፈቃድ ምፅዋን ከግብጾች በመንጠቅ ተቆጣጠረ። ቀጥሎም ከጎሳ መሪዎች ጋር ውሎች በመፈራረም ሰምሐር እና ሳህል የሚባሉትን የሰሜን ምዕራብ ክፍሎች በሰላማዊ መንገድ ወደ ግዛታቸው ጠቀለሉ። ወደ ደቡብ ግን በጦርነትና ክፋፍሎ ማሸነፍ በሚለው የቅኝ ግዛት መንገድ መስፋፋት ጀመሩ። የመሃዲስቶችን፣ ኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያውን መካከል ያለውን ፉክክር በመጠቀም ሐማሴንን፣ ሰራየንና አካለ ጉዛይን ገንዘባቸው አደረጉ። ዳግማዊ አጼ ምንሊክ የአጼ ዮሐንስ ተተኪ ንጉስ እንዲሆኑ በመርዳት በቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ያላቸውን ግዛት ህጋዊነት እንዲቀበሉ አደረጉ (የውጫሌ ውል)። የውጫሌን ውል፣ አንቀጽ 3፣ የጣሊያኖችን ግዛት በምስራቃዊው ጠለል ላይ የወሰነ ቢሆንም እነርሱ ግን ውሉን በመጣስ ግዛታቸውን እስከ መረብ ወንዝ ድረስ አስፋፉ። 1890 ላይ ይህን ግዛታቸውን ኤሪትራ ብለው ሰየሙት።

በጊዜው፣ የኤርትሪያ ሕዝብ ስብጥር

ለማስተካከል
 
አስመራ ፲፰፻፺፭
 
የጣሊያናዊው አስመራ ገዢ ቢሮ - 1896 ዓ.ም.

ኤርትራን ካወጁ በኋላ ጣሊያኖች በ3ኛው አመት ህዝብ ቆጠራ አደረጉ። በዚህ ወቅት የህዝቡ ብዛት 191፣127 እንደሆነ ሊታወቅ ቻለ። በዘመኑ ከአርሶ አደሩ ክርስቲያን ደገኛ ትግርኛ ተናጋሪዎች በተጨማሪ በምዕራብ፣ ዘላን መስሊሞች ፡ ቤኒ አሚርብሌንሐባብመንሳ እና ማርያ እንዲሁም ዘላንና አርሶ አደር የሆኑት ኩናማናራ የተሰኙ ብሔሮች እንደሚኖሩ ታወቀ። በምስራቅና በደቡብ የባህር ጠረፎች ደግሞ አፋርሳሆ የተሰኙ አርብቶ አደሮች እንደሚኖሩበት ተመዘገበ።

ለማስተካከል

የጣሊያኖች አገዛዝ

ለማስተካከል

ጣሊያኖች የግዛታቸውን ማዕከል ምፅዋ ላይ በማድርገ የቢሮክራሲ ስርዓት ዘርግተው በራሱ ላይ ወታደራዊ ገዥወች ሾሙበት። ቆይተውም ከአገሬው ወሰደው 300+ሺህ ሄክታር የሚሆነውን መሬት ለአውሮጳውያን ገበሬዎች ለመስጠት ያሰቡት እቅድ ከህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበት ተቋረጠ። ሚያዚያ 1894 በደጃዝማች ባህታ ሐጎስ የተነሳው አመጽ ጣሊያኖች ወደ ኢትዮጵያ፣ ትግራይ የማጥቃት ጦርነት እንዲከፍቱ አደረገ። ነገር ግን በዳግማዊ ምኒልክ የተመራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ጣሊያኖችን በተደጋጋሚ ድል አደረጋቸው (አምባላጌ-ታህሳስ 1895፣ አድዋ - መጋቢት 1896)። በኒህ ጦርነቶች ጣሊያኖች ወደ 10፣000 ወታደሮችና 500 ሚሊዮን ሊሬ በመክሰራቸው ከዚህ በኋላ ለቅኝ ግዛታቸው የሚያወጡትን ወጭ ቀነሱ።በዚህ ጦርነት የማይረሳው ብዙ ወታደሮችም ተማርኳል የጣልያን ምርኮኛችን በካሳ እንዲለቀቁ ተስማምቷል ለኤርትራውያን የጣልያን ወታደሮች ግን ኣንድ እግራቸው እና ኣንድ እጃቸውን በመቁረጥ እንዲለቀቁ ተደርጓል የማይረሳው የኢትዮጵያ ጥቁር ታሪክ የነበረውን ጸብ ከዚህ ይጀምራል፣ከዚያ ወዲህ ጣልያኖች ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ጉርብትና ፈለጉ እንጂ በቀደመው አጥቂነታቸው ለመቀጠል አልፈለጉም።

ጣሊያኖች ግዛታቸውን አጸኑ

ለማስተካከል

ከአድዋ ሽንፈት በኋላ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራርመው አዲስ ገዢ፣ ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፣ 1897 ላይ በመሾም ግዛታቸውን ማጽናት ጀመሩ። በዚህ ወቅት የቀደመው ወታደራዊ ስርዓት እንዲቋረጥ ተደርጎ አገሪቱ የብሔር ልዩነትን "በሚያከበር" አስተዳደር ተከፍሎ እንዲቋቋም ተደረገ። ዳህላክ፣ አፋር እና ሰምሃር አንድ ላይ "ምስራቃዊ ክፍል" ተብለው ከምጽዋ እንዲተዳደሩ ተደረገ። "ምዕራባዊ ክፍል" ከአቆርዳት እንዲተዳደር ሲደረግ ቤኒ አሚርን፣ ናራንና ኩናማ ምድርን ያጠቃልል ነበር። ከከረን ሆኖ የሚተዳደረው ደግሞ ሰሜናዊ ሐማሴን (የእስልምና ተከታይ የሆነ)፣ ቤት አሰገደዓድ ሼኽ ነበሩ። ቀሪው ሐማሴን ከአስመራሰራየመንደፈራ(አዲ ወግሪ) እንዲተዳደር ሲደረግ አካለ ጉዛይሳሆ ጋር ተዋህዶ ከአዲ ቀይሕ ይገዛ ጀመር። ከላይ ወደታች በተዘርጋ መዋቅር የጣሊያን ባለስልጣኖች እያንዳንዱን ክፍል ያስተዳድሩ ጀመር። የአገሪቱ ዋና ከተማ ከምጽዋ ወደ አስመራ የተዛወረው በዚህ ወቅት፣ በ1898 ነበር።

ከ1898 እስከ 1908 በተደረጉ ውሎች (ከኢትዮጵያ፣ ከአንግሎ-ግብጻዊ ሱዳንና ከጅቡቲ ጋር) መሰረት የቅኝ ግዛቱ ድንበር ታወቀ። ኢትዮጵያን ስለ ድንበሩ ለማሳመን 3 አመትና 5ሚሊዮን ሊሬ ፈጅቶባቸው ግንቦት 1900 ላይ ያሰቡት ሊሳካላቸው ቻለ። ድንበሩ ከሞላ ጎደል የመረብበለሳሙና ወንዞችን የታከከ ነበር።

የቅኝ ግዛቱ አስተዳደር

ለማስተካከል

በ1898 ጣሊያኖች ለቅኝ ግዛታቸው አዲስ ደንብ አወጡ። ድሮ ይጠቀሙበትን የነበረውን የአገሬውን ባላባት በጭካኔ የመቅጣት መንገድ በመተው፣ ከነሱ ጋር የተሻረከውን የመሸለምና በነሱ ስር እንዲሰራ የማድረግ ዘዴን ጀመሩ። ከሕግም አንጻር የጣሊያን ሕግ ለጣሊያን ገዥወች የሚሰራ ቢሆንም የአካባቢው ሕግ ( ለምሳሌ የሙስሊሞች ሕግ) ለአካባቢው ሕዝብ እንዲሰራ አደረጉ። ከላይ ጣሊያኖች የሁሉ ገዢወች ሲሆኑ ከስር የአካባቢውን መሪወች ቀጥረው እንዲያስተዳድሩ አደረጉ። የአካባቢው ገዥወች ግብር በመሰብሰብ፣ ሕግ በማስከበርና ፍርድ በመስጠት ያገለግሉ ነበር። ይህ የአገሩን መሬት በአገሩ በሬ ዘዲያቸው የተሳካ ከመሆኑ የተነሳ በዚህ ወቅት አገሬው በአመጽ እንዳይነሳ እረድቷል፣ ቢነሳም በጣም በአናሳ ሁኔታ አልፎ አልፎ ነበር (ለምሳሌ ደጃዝማች አበራ ግዛውሙሃሙድ ኑሪገብረመድህን ሐጎስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸሹ የተገደዱ)። ጣሊያኖቹ በዚህ ዘመን ትግርኛ ከማይናገረው ክፍል ከፍተኛ ድጋፍን አገኙ፣ ለዚህም ምክንያቱ ሕግና ሥርዓት ባሉት መመሪያቸው መሰረተ ከደጋው ወደነዚህ ክፍሎች የሚመጣውን ዘመቻ በማስቆማቸው ነበር። በወቅቱ የጣሊያኖች ዋና አላማ ፖለቲካዊ መረጋጋት ስለነበር የትግርኛ ተናጋሪውን ክፍል በአመጽ እንዳይነሳ ብዙ ስራ ሰርተዋል። ስለሆነም የትግርኛውን ክፍሎች ማህበረሰባዊ ትሥሥር ለመቆራረጥ ብዙ ሙከራወችን አድርገዋል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ለተግባራቸው እንዲረዳቸው በእጅጉ ሞክረዋል። ነገር ግን ይህ ሙከራቸው ብዙ ፍሬ አላፈራም። ጣሊያኖቹ የእስላምና ተከታዩን ክፍል ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ የእስልምና ሃይማኖትን መስፋፋት በሰፊው ይደግፉ ስለነበር። በዚህ ምክንያት የኦርቶዶክስ ተከታዩ ክፍል የካቶሊክ ቤተከርስቲያንን በመጥፎ አይን በመመልከት የትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት የመግባት ፍላጎት እጅግ አነስተኛ ሆነ። እንዲያውም የኦርቶዶክሱ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በነበረው ጥብቅ ግንኙነት ምክንያት ከ1920ወቹ ጀምሮ ለቅኝ ገዥወቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ይመጣ የነንበረው ከኒሁ አብያተ ክርስቲያናት ሆነ።

 
የአገሬው ሰው አኗኗር፣ በጣሊያኖች ፖስትካርድ - 1930
የትምህርት ፖሊሲ
ለማስተካከል

አብላጫው የትምህርት ስራ በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ሚስዮናውያን የሚሰራ ነበር። በመጀመሪያ፣ የአገሬው ህዝብ ዕውቀት አድማሱ እንዳይሰፋ በማሰብ እንዳይማር በህግ ተከልክሎ ነበር ። ነገር ግን ለቅኝ ግዛቱ ተላላኪዎች ለመፍጠር በማስብ አገሬው አንስተኛ የኢለመንታሪ ትምህርት እንዲማር ተፈቀደ፣ ይሄውም የሆነው በ1911 ነበር።ከ 1ኛ ክፍል እስከ 4ኛ ክፍል ነበረ፣ ጣሊያኖቹ በተጨማሪ በአስቀመጧቸው የተለያዩ መሰናክሎች ምክንያት አቅማቸው ለትምህርት ከደረሱ የአገሬው ሰዎች መካከል ከላይ የተጠቀሰውን ትምህርት ያገኙት ከ2% አይበልጡም ነበር። ቅኝ ግዛቱ፣ ኤርትራዊ ምሁር እንዳይኖር ማድረጉ የማይካድ ሃቅ ነው።

ጣሊያኖችና አገሬው

ለማስተካከል

በኤርትራ ኗሪ የሆኑ ጣሊያኖች ቁጥር ቀስ በቀስ እያደገ ሄዶ 1934ዓ.ም. ላይ 4፣500 ደርሶ ነበር። በሚቀጥሉት 5 አመታት ከፍተኛ እድገትን በማሳየት፣ 1939ዓ.ም. ላይ ቁጥራቸው 75፣000 ደርሶ ነበር። ከሰፋሪ ጣሊያኖቹ ውስጥ የፋብሪካ ባለቤቶችና ገበሬዎች ቢገኙበትም አብዛኞቹ ግን መኖሪያቸውን ያደረጉት በአስመራምጽዋ ነበር። በ1930ወቹ መጨረሻ ላይ አንድ-አምስተኛ (20%) የሚሆኑት የአገሬው ሰዎች በከተማ ይኖሩ ነበር። በአንስተኛ ደመዎዝ እየሰሩ፣ ለአገሬው በተዘጋጁ የከተማ ክፍሎች ተወስነውና የፖለቲካ አቅም እንዳይኖራቸው የጣሊያን ዜግነት ተነፍጓቸው ይኖሩ ነበር።

የአፓርታይድ ስርዓት እና ፋሽዝም
ለማስተካከል

ምንም እንኳ በቅኝ ግዛት ስርዓት መሰረት አገሬውና ገዥዎቹ እኩል ባይታዩም እስከ ፋሽዝም መነሳት ድረስ የአገሬው ህዝብና ጣሊያኖቹ ከሞላ ጎደል የመደባለቅ ሁኔታ አሳይተዋል። ነገር ግን በ1930ዎቹ መጨረሻ ላይ አይን ያወጣ የአፓርታይድ ዘረኝነት ተጀመረ። በኤውሮጳውያንና በአገሬው ህዝብ መካከል ማንኛውም አይነት ጋብቻም ሆነ አብሮ መኖር በህግ ተከለከለ። 1940 ላይ የጣሊያንና አገሬው ክልሶች ሳይቀሩ የዜግነትና የትምህርት መብታቸውን በህግ አጡ።

የኢኮኖሚ እድገትና የልዩ ማንነት መፈጠር
ለማስተካከል

ከ1936 ጀምሮ ኤርትራ የኢኮኖሚ እድገት ማሳየት ችሏል። በ30ዎቹ መጨረሻ 2፣198 የኢንደስትሪ ተቋሞች በአገሪቱ ተመስርተዋል። ይሁንና ጣሊያኖች አገሪቱ እራሷን እንድትችል ሳይሆን የነርሱ ጥገኛ እንድትሆን ነበር ያደረጉት፣ ለዚህ ሲሉ አብዛኛው ምርት ከውጭ ያስመጡ ነበር። ከ10-15% የሚሆነው የአገሬው ወንድ ሃይል በኢንደስትሪ፣ በእርሻና በጥቃቅን የተላላኪ ስራወች ተቀጥርው ይሰሩ ነበር። ከ1936-41 ድረስ አብዛኛውን የአግሬውን ወንድ ቀጥሮ ያሰራ የነበረው የቅኝ ገዥው ውትድርና ተቋም ነበር (40% ወይም 60፣000 ለአቅመ አዳም የደርሱ ወንዶችን)።

እኒህ ወታደሮች ኢትዮጵያን ለመውረር ያገለገሉ ሲሆን ለዚህ ታማኝነታቸው ምክንያቱ ቅኝ ገዥወች በኤርትራ ላይ ያሰፈኑት ፖለቲካዊ መረጋጋት እንደምክንያት ይጠቀሳል። የጤና፣ የገበያ ኢኮኖሚ እንዲሁም ቁሳዊ ፍጆታ መስፋፋት በ1905ዓ.ም. 250 ሺህ ብቻ የነበረው የኤርትራ ህዝብ ወደ 614 ሺሕ በ1935 ዓ.ም. እንዲያድግ አድርጓል። ትግርኛ ተናጋሪው ክፍል በዚህ ጊዜ 54% የአገሪቱ ክፍል ነበር። እኒህ ለውጦች በአገሬው ላይ የስነ ልቦና ለውጥን አስከተሉ፣ ስለሆነም ከኢትዮጵያውያን ጐረቤቶቻቸው የተለዩ ህዝቦች የመሆን ማንነትን ፈጠረ።

 

የእንግሊዝ ወታደራዊ አገዛዝ (1941 -1952)

ለማስተካከል
 
የከረን ጦርነት የትካሄደበት ስፍራ

ሁለተኛው የአለም ጦርነትን ተከትሎ እንግሊዞችአንግሎ ግብጻዊ ሱዳን በመነሳት ጥር 1941 በኤርትራ ላይ ጥቃት አደረሱ። ከሶስት ወር በኋላ የከረን ጦርነትን በማሸነፍ ሚያዝያ 1941 ሙሉ ኤርትራን ተቆጣጠሩ። የእንግሊዝ ወታደራዊ አገዛዝ(BMA) በጣሊያኖች ምትክ አገሪቱን ማስተዳደር ጀመረ። 1947 ጣሊያን በፈረመችው የሰላም ውል መሰረት ኤርትራ ለአራቱ ሃይላት ተሰጠች። ከዚህ በኋላ ኤርትራ የጣሊያን ቅኝ መሆኗ አበቃላት።

ሕግና ስርዓት

ለማስተካከል

እንግሊዞች የመጀመሪያ አላማቸው ሕግና ስርዓትን ማጽናት እንዲሁም አገሪቱን ማረጋጋት ነበር። ለዚህ ሲሉ ጣሊያኖች ሲሰሩበት የነበረውን ስርዓት ብዙ ሳይቀይሩ ነበር መግዛት የጀመሩት። በ'44 እና '47 መካከል የኤርትራን ግዛቶች በብሔር ከ5 ከፍለው እንደገና አዋቀሩት። ይህ አዲሱ አወቃቀር ከጣሊያኖቹ እምብዛም አይለም ሆኖም ግን ከረንንና አቆርዳትን አንድ በማድረግ "ምዕራባዊ ግዛት" ስያሜ ሰጥተው አዲስ ክፍል አድርገዋል፣ ምፅዋንና አሰብን በማዋሃድ የቀይ ባሕር ክፍል ብለው ሰይመዋል፡

ሁለተኛው የአለም ጦርነት

ለማስተካከል

እንግሊዞች ከነበረባቸው የሰው ሃይል ማነስ የተነሳ የጣሊያን ተቀጣሪወችን ሳይቀር የቀደሙትን የአገሬውን ባለስልጣኖች ሳያባርሩ ነበር ግዛታቸውን የጀመሩት። የጣሊያኖችም ህጎች በነበሩበት እንዲጸኑ ተደርገዋል። ሆኖም ግን የአፓርታይድ ስርዓቱን አስቀርተው አገሬው የጤናና የትምህርት፣ የመናገር ነጻነትና የስራ እድል ተቋዳሽ እንዲሆን አድርገዋል። የትምህርት ቤቶች ቁጥር 100 ሲደርስ በዚህ ወቅት ትምህርት በትግርኛእና አረብኛ ይሰጥ ነበር። የሁለተኛው የአለም ጦርነት ካስነሳው የኢኮኖሚ ፍላጎት አንጻር ኤርትራ የእርሻና የኢንደስትሪ ምርቷ በክፍተኛ ደረጃ አደገ። እንግሊዞቹ ወደ 256 ሺህ ሄክታር መሬት በመቆጣጠር 59ሺህ ቶን የሰብል ምርት ለመሰብሰብ ቻሉ። ኢኮኖሚው በዚህ መንገድ ከማደጉ የተነሳ ኤርትራ እርሷን የቻለች ሆነች። የተማሩ ጣሊያኖችና ወዝ አደር የአገሬው ሰወች በእንግሊዞች እየተቀጠሩ ይሰሩ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የአገሬው ህዝብ የንግድ ማህበር እንዲያቋቁሙ የተፈቀደው በዚህ ጊዜ ነበር።

ከጦርነቱ በኋላ

ለማስተካከል

በጦርነቱ ወቅት ኢኮኖሚው ይደግ እንጂ፣ እንግሊዞቹ የበለጠ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ጣሊያኖች የዘረጉትን አብዛኛውን ኢንደስትሪና ኢንፍራስትራክቸር በመነቃቀል ሸጡ። ከአለም ጦርነት በኋላ የኢኮኖሚክ ፍላጎት ማንስ ባስነሳው ሁኔታ የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ እድገት ተጨናገፈ። የእግንሊዙ ወታደራዊ አስተዳደር ያስቀመጠው የብድር፣ የላይሰንስ፣ የውጭ ገንዝበና የምርት ገደብ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ መጨናገፍ ደጋፊ ነበር። የእርሻና የኢንደስትሪ ውጤቱም ከውጭ ካለው ፉክክር የማይከለከል ስለ ነበር ሌላው የኢኮኖሚው ቁስል ነበር። ይህ ሁሉ ተደማምሮ 1948ዓ.ም. ላይ የአገሪቱ ኢንደስትሪ እንዲዘጋና ወደ 10፣000 የሚጠጋ ኤርትራዊ ስራ አጥ እንዲሆን አደረገ። ኢኮኖሚያዊ ቀውሱና የዕቃወችን ውድነት ተከትሎ ብሔራዊነት ገኖ መውጣት ጀመረ። የአገሪቱ ኤኮኖሚና አስተዳደር በኤርትራውይን እንዲደረግ ጥያቄ መቅረብ ጀመረ።

 
አስመራ - በሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ (1945)
 
የመገንጠል አቋም ባላቸው ላይ የሃይል እርምጃ ይወስዱ የነበሩ፣ በተቃዋሚወቻቸው ሽፍታ የሚሰኙት ኤርትራውያን

ማህበር ፍቅሪ ሐገር

ለማስተካከል

ከ1941 ጀምሮ ሁሉንም ኤርትራውያን ያሳተፈ ፀረ-ቅኝ ግዛት ማህበር -ማህበር ፍቅሪ ሐገር ተቋቁሞ ነበር። የዚህ ማህበር አላማ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለእንግሊዞቹ ማስረዳት ነበር። ቀስ ብሎ ግን ከተማ ኗሪው ትግርኛ ተናጋሪ ክፍል ፅንፈኛ፣ ኢትዮጵያን የሚደግፍ አቋም መያዝና ማህበሩን መቆጣጠር ጀመረ። 1943 ላይ አብዛኞቹ እስልምና ተከታዮችና አንድ አንድ የደቡብና መሃከለኛ ደጋማ ክፍል ክርስቲያኖች ማህበሩን ለቀው የመለያየት እንቅስቃሴን ጀመሩ። 1946 ላይ የአንድነት ደጋፊወችና የሱዳን መከላከያ ሃይሎች (በእንግሊዞች ስር የነበሩ) አስመራ ውስጥ ደም ተፋሰሱ። ይህ ሁኔታ የፖለቲካ ውጥረትን ያስከተለና የጣሊያን ኗሪዎች በአንድነት ደጋፊዎች ከዚህ በኋላ ጥቃት እንዲደርስባቸው ያደረገ ነበር። ጥቅምት 1946 ላይ እንግሊዞች በፖለቲካ ፓርቲወች ላይ ያስቀመጡትን ዕቀባ አነሱ።

1947 ላይ ጣሊያኖች በፈረሙት የሰላም ውል መሰረት የኤርትራን የወደፊት ዕድል የተባበሩት ሃይሎች እንዲወስኑ ተደረገ። የተባበሩት ሃይላት የአገሬውን ፍላጎት ለማወቅ አጣሪ ኮሚሽን ላኩ። በዚህ ጊዜ ኤርትሪያ ውስጥ 4 ጉልህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይንቀሳቀሱ ነበር፣ እነርሱም

፩ - አንድነት ፓርቲ - ኅዳር 1947 ላይ እንደ ፓርቲ እውቅናን ያገኘ ነበር። ይደገፍ የነበረውም በትግርኛ ተናገሪዎቹ የሐማሴን ክፍሎች እና ባላባት እስልምና ተከታዮች ነበር።ይህ ፓርቲ ትልቅ የኢትዮጵያ መንግሥት እጅ ነበረው አቋሙም ያለምንም ድርድር ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ የሚል ስለነበረ። ይዞታው የአገሪቱን 48% ድጋፍ ያገኘ ከነበሩት ፓርቲዎች ሁሉ ታላቁ ነበር።
፪ - መስሊም ሊግ - ሁለተኛው ታላቁ ፓርቲ ሲሆን 30% የአገሪቱን ድጋፍ ያገኘ ነበር። ከባላባቶች ውጭ የሆኑትን መስሊሞች ድጋፍ ያገኝ ነበር። አቋሙ ኤርትራ ተገንጥላ እራሷን መቻል አለባት፣ ይህ ካልሆነ ተገንጥላ በተባበሩት መንግስታት ትመራ፣ የሚል ነበር።
፫ - ለዘብተኛ ተራማጅ ፓርቲ- ከማህበረ ፍቅሪ አፈንግጠው ተገንጣይነትን ከሚያራምዱት ቡድኖች የመጣ ሲሆን አብዛኛው ደጋፊ ደገኛ ክርስቲያኖች ነበሩ። ይህ ፓርቲ በወታደራዊው አገዛዝ(BMA) የሚደገፍ ነበር። አቋሙም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ትግርኛ ተናጋሪዎች ጨምሮ ከኢትዮጵያ መገንጠል ነበር።
፬ - ጣሊያንን ደጋፊ ፓርቲ - የዚህ ፓርቲ ደጋፊዎች ኗሪ ጣሊያኖች፣ ክልሶችና በቅኝ ግዛቱ ወቅት ጥቅም የነበራቸው ኤርትራውያን ነበሩ። አቋማቸው የጣሊያን ፓለቲካዊ ግዛት በኤርትራ ተመልሶ እንዲቋቋም ነበር።
 
የአገሬው ነዋሪ የተ.መ. የወደፊቱን የኤርትራ ጉዳይ በሚያጠናበት ወቅት
 
በወቅቱ የኢትዮጵያን መንግሥትን ወዳጆች አንድነትን ደጋፊዎች ኤርትራውያን እና ሰላማዊ ሰልፍ

ከዚህ በተረፈ የኢትዮጵያ፣ ታላቋ ብሪታኒያና ጣሊያን የራስ-ፍላጎቶች የኤርትራን የወደፊት እድል ያወሳሰበ ጉዳይ ነበር። ታላቋ ብሪታንያ አቋም ኤርትራ እራሷን መቻል የማትችል አገር ስለሆነች ከሁለት ተከፍላ እስላሞች የሚኖሩበት ምዕራባዊው ክፍል ለሱዳን እንዲሰጥ፣ ክርስቲያን ትግርኛ ተናጋሪው ደጋ ክፍል ለኢትዮጵያ እንዲሆን ነበር። ጣሊያን ፍላጎት በተባበሩት መንግስታት ቡራኬ የኤርትራ ሞግዚት ሆና እንድታስተዳድረው፣ ያ ካልሆነ አገሪቱ ለብቻዋ እንድትሆን ነበር። ኢትዮጵያ አቋም፣ ከታሪክ፣ ከመልክዓምድር፣ ከብሔርና ከኢኮኖሚ አንጻር፣ እንዲሁም ከስትራቴጂክ ፍላጎት አንጻር፣ ማለት የባሕር በር እንዲኖራት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ኤርትራ የርሷ እንደሆነች ነበር። አጼ ሃይለ ሥላሴ በቅኝ ግዛት ወቅት የተወሰደውን መሬት ለኤርትራውያን አስመልሳለው ብለው ቃል ሲገቡ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቄሶች ሙሉ በሙሉ ደጋፊያቸው ሆኑ፣ በግልጽም የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች ሆነው ይሰሩ ነበር።

ከ1947-48 የአራቱ ሃይሎች አጣሪ ኮሚሽን ወደ ኤርትራ ሄዶ የህዝቡን ልብ ትርታ ለማጥናት ያደረገው ሙከራ በኮሚሽነሮቹ መካከል ስምምነት ስላልፈጠረ እና የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነትም ለመለየቱ አስቸጋሪ ስለነበረ በ1948 ላይ ጉዳዩ ለአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት መድረክ ቀረበ። እንግሊዞችና ጣሊያኖች የቤቭን ፎርዛ አቅድ የተባለውን ሰነድ ያዘጋጁት በዚህ ወቅት ነበር። በአቅዱ መሰረት ኤርትራ ከሦስት ስትከፈል ምዕራቡ እስላም ክፍል ለሱዳን፣ ደጋው ለኢትዮጵያ፣ ዓሰብና ምጽዋዕ ልዩ ግዛት እንዲሆኑ ነበር። ሆኖም ግንቦት 1949 ላይ የተካሄደው የተ.መ. ጉባኤ ሃሳቡን ውድቅ አደረገው።


ይህን ተከተሎ ኤርትራ ውስጥ ፖለቲካዊ ቀውስ ተነሳ። መስሊም ሊግ የለዘብተኛ ተራማጅ ፓርቲንና የጣሊያን ደጋፊ ፓርቲን ሃይሎች በማስተባበር ታላቅ የተገንጣይ ቡድን መሰረተ። ሆኖም ግን በአባሎቹ የሶሽዮ-ፖለቲካ መሰባጠር ምክንያት ሃይሉ የዳከመ ነበር። በዛ ላይ የጣሊያንን እንደገና መምጣት በመፍራትና የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ለማክበር ቃል መግባት በመከተል ብዙዎች ከኢትዮጵያ ጋር ይህ-ከሆነ ውህደት እንዲፈልጉ አደረገ። የኢኮኖሚው መንኮታኮትም በእስላሞችና ክርስቲያኖች መካካከል እንዲሁም በቋንቋ-ብሔሮች መካከል ውጥረት አስነሳ። መስሊም ሊግ ጭሰኝነትን አስወግዳለሁ በማለቱ የሙስሊም ባላባቶች ውህደትን እንዲደግፉ አደረገ።

1950 ላይ የተ.መ. ሃቅ ፈላጊ ቡድን ኤርትራ በመሄድ ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ የህዝቡ ፍላጎት ላይ ጥናት አካሄደ። በዚህ ወቅት ሽፍቶች በመገንጠል ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት አደረሱ። የሃቅ ፈላጊው ቡድን አባል የሆኑት የኖርዌይ ተወካይ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር አንድ እንድትሆን፣ የበርማደቡብ አፍሪቃ በፌዴሬሽን እንድትዋሃድ፣ የፓኪስታንጓቴማላ ተወካዮች ለ10 አመት በተ.መ. ሞግዚትነት ተዳዳራ በኋላ እራሷን እንድትች ሃሳብ አቀረቡ። ሁሉም አባላት ኤርትራ ወዲያውኑ እራሷን እንደማትችል፣ ለዚህ ምክንያቱ የሶሺዮ-ኢኮኖምክ ብቃት አለመኖርን።

ከብዙ ክርክርና የዲፕሎማሲ ፍትጊያ በኋላ፣ ታህሳስ 1950 ላይ የተ.መ. አጠቃላይ ጉባኤ Resolution 390 A(V) ላይ የእጅ ምርጫ በማድረግ አጸደቀ። በጸደቀው ድንጋጌ መሰረት ኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቀጥል።ፌደረሽኑም የሁለቱም አገሮች እኩል መብት ኑሯቸው የፌደሬሽን ባንዴራ ኑሯቸው እንዲቀጥሉ ነበረ፤ the United States was instrumental in promoting Eritrea's linkage with Imperial Ethiopia, opposing the idea of an independent Eritrea, irrespective of the wishes of the Eritrean people. This was succinctly put by then US ambassador to the UN (later to become US Secretary of State) John Foster Dulles: "From the point of view of justice, the opinions of the Eritrean people must receive consideration. Nevertheless the strategic interest of the United States in the Red Sea basin and the considerations of security and world peace make it necessary that the country has to be linked with our ally Ethiopia."ወደ አማርኛ ሲገለበጥ ፤የተ.መ የኤርትራን ፍላጎት ሳይሰማ ከኢትዮጵያ ጋር አቆራኛት፤የዚያን ጊዜ አምባሳደር ጆን ፎስተር ዳላስ በኋላ ዋና ጸሓፊ የሆኑት እንዳሉት «ከህግ አንጻር የኤርትራን ህዝብ ፍላጎት መሰማት ነበረበት ሆኖ ግን የኛ የተ.መ ስትራቴጂ በቀይባህር ያለንን አንጻር እና የአለም ሴኩሪቲን ለማስጠበቅ ከጓደኛችን ኢትዮጵያ እንድትቀላቀል አድርገናል» አሉ፤ When Ethiopia deposed its Emperor and became a communist state 1974–1991, the United States did not support the Eritrean rebels' struggle for independence from communist Ethiopia, but remained committed to Eritrea's linkage with Ethiopia, albeit under a different, more pro-western Ethiopian administration.ከሁለት አመት የሽግግር መንግስት በኋላ ፌዴሬሽኑ መስከረም 1952 ላይ ተግባር ላይ ዋለ።

 
 

ኢትዮጵያ ኤርትራ ፌዴሬሽን (1952-1962)

ለማስተካከል

የፌዴሬሽን አስተዳደር ለአካባቢው እንግዳ ስለነበር የተለያዩ ክፍሎች በተለያየ መልኩ እንዲተረጉሙት ሆነ። የኢትዮጵያ መንግስት ፌዴሬሽን ማለቱ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ የሚያጠቃልል ነው ብሎ ተረጎመ። በኤርትራ በኩል፣ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ፌዴሬሽኑን ቢቀበሉም በአተረጓጎሙ ላይ ልዩነት አሳዩ። አንድነት አራማጆች ትርጉሙን ኢትዮጵያ በምታይበት አይን ሲመለከቱ በኢብራሂም ሱልጣን የሚመራው የኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የመገንጠል ደጋፊዎችን በማነሳሳት የኤርትራን ራስ ገዝነት አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ይተረጉሙ ነበር።

 
የኤርትራ ፌዴሬሽን ሲፀድቅ፣ መስከረም 1952

በተ.መ. የፌዴሬሽኑ ድንጋጌ መሠረት የሁለቱን ክፍሎች ግንኙነት የሚያስተዳድሩ ልዩ ተቋማት እንዲፈጠሩ አልተደረገም። ነገር ግን በምክር ለመርዳት ያክል Imperial Federal Council የተባለ ተቋም ተበጅቶ የነበር ሲሆን በቂ ኃይል ግን አልነበረውም ። ስለዚህ እውነተኛው የፌዴራሉ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ነበር። በሽግግሩ ወቅት የእንግሊዙ ወታደራዊ አስተዳደር የኤርትራን ህገ መንግስት እንዲህ ሲል ቀረጸ፣ ኤርትራ ራሱን የቻለ ግዛት ሲሆን ኤርትራዊ ዜግነትን ፣ ብሔራዊ ቋንቋን (ትግርኛና አረብኛ)፣ የተለየ ሠንደቅ አላማን፣ ማህተምንና ልዩ መንግስትን ለኤርትራ ይሰጣል። በራሱ ጉዳይ ዙሪያ ህግ ማጽደቅ ፣ ህግ ማስፈጸምና ፍርድ መፍረድ እንዲችል ለኤርትራው መንግስት ይፈቅዳል። የአካባቢውን ሥነ ንዋይ መቅረጽ፣ ግብር መሰብሰብ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ መስተዳድር እና የፖሊስ ስራ በዚሁ በኤርትራው መንግስት ስር ይከወናሉ። የፖለቲካ ፓርቲወች፣ የንግድ ማህበራት፣ የሰው ልጅ መብቶች፣ የህትመትና የመናገር ነጻነትንም ይፈቅዳል። የፌዴራሉ መንግስት በአንጻሩ የውጭ ጉዳይን፣ መከላከያን፣ ገንዘብን፣ ፋይናንስን፣ የውጭ ንግድና የኢትዮጵያና ኤርትራን ንግድን፣ መገናኛን በተመለከተ ስልጣን ይኖረዋል። በተጨማሪ የፌዴራል መንግስቱን ስራ ለማካሄድ አንድ አይነት ግብር እንዲያወጣ ይገደድ ነበር። በዚህ ወቅት አቶ አንዳርጋቸው መሳይ (የአጼ ኃይለ ስላሴ አማች) በኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ነበሩ።

የኤርትራ ምክር ቤት

ለማስተካከል

የኤርትራ ምክር ቤት (ባይቶ ኤርትራ) በእንግሊዞች አቀናባሪነትና አገር አቀፍ ምርጫ መጋቢት 1952ዓ.ም. ሲመሰረት በዚሁ ወቅት የኤርትራን ህገ መንግስትና የፌደሬሽኑን ደንብ አጸደቀ። እንዲሁም አቶ ተድላይ ባይሩን እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚ ና አቶ አሊ አህመድ ሙሳ ረዳይን እንደ ፕሬዜዳንት አድርጎ መረጠ። በዚያው አመት መስከረም ላይ የኢትዮጵያም መንግስት እንዲሁ ሁለቱን አጸደቀ። መስከረም 15 ላይ የአስተዳደሩ ሃይል ወደ ፌዴራል መንግስት ተዛወረ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያውም ሆነ የኤርትራው ውገኖች ለራሳቸው በሚስማማ መልኩ የፈዴሬሽኑን ደንቦች በመተርጎም ቀስ በቀስ የፖለቲካ ውጥረት ተነሳ። የአንድነት ደጋፊ የነበሩት አቶ ተድላ ባይሩ 1953 ላይ የፖለቲካ ተቃውሚዎቻቸው ወልደ አብ ወልደ ማርያምንና አብርሃ ተሰማን በመወንጀል ጥቃት ጀመሩ። የአንድነት ፓርቲ አቶ ተድላ ባይሩን በመደገፍ ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ጋር ማዋሃድ አላማው አድርጎ ተነሳ። እኒህ የአንድነት ደጋፊዎች በመንግስት ቢሮዎች ለየት ያለ ስራ የማግኘት እድል ስላገኙ የተገንጣይ ሃይሎች (የኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ግንባር) እጅግ ተበሳጩ። በተለይ በእስላማዊው ምዕራብ ኤርትራ ግንባሩ ከፍተኛ ድጋፍን ማግኘት ጀመረ። የኢኮኖሚው እየወደቀ መሄድ፣ የግብር መጨመርና የቁሳቁሶች ዋጋ መጨመር ለውጥረቱ መባባስ አስተዋጽኦ አደረጉ። በዚህ ወቅት ኤርትራ የምታስገባውና የምታስወጣው ዕቃ ላይ 25% የግብር ጭማሪ ተደርጎ ነበር። የጣሊያን ዜጎችም በጦርነቱ ያጡትን የኢንደስትሪ፣ ማዕድን ማውጣት፣ እርሻ ወዘት መብቶች ከእንደገና በማግኘታቸው አገሬው ህዝብ እንዲበሳጭ ካደረጉት ጉዳዮች አንዱ ነበር።

በዚያው አመት በ1953 ሙስሊም ሊግ መነሳሳትን አሳየ። እንዲያውም የእስላምናን ፍላጎትና የኤርትራን ህገ መንግስት እንደግፋለን በማለት ህዝባዊ አመጽ ማደራጀት ጀመረ። የኤርትራው ሥራ አስፈጻሚ ሊቀመንበር የህትመት ነጻነትን በመንፈግ አመጹን ለማፈን ሞከረ። 1954 ላይ ሙስሊም ሊግ በበኩሉ ለአጼ ሃይለ ስላሴ እና ለተባበሩት መንግስታት የመብቱን መታፈን በመቃወም ደብዳቤ ጻፈ። ነገር ግን ተቃውሞው አንድ ወጥ አልነበረም። በሙስሊም ሊግ ውስጥ በተነሳ ውስጣዊ ቅራኔ ኢብራሂም ሱልጣን ከሊጉ ተባረረ። የሆኖ ሆኖ ሙስሊም ሊግ በኤርትራ ምክር ቤት ባደረገው ዘመቻ አቶ ተድላ ባይሩ ምክር ቤቱ ክብር እንዲያጣና በራሱ ፓርቲ እንዲወቀስ አድርገው ነበር።

በኤርትራው ምክርቤትና በሥራ አስፈጻሚው ሊቀመንበር (ፕሬዘዳንት አሊ ረዳይ)ውጥረት የተጀመረው በዚህ ወቅት ነበር። ምክር ቤቱ ተድላ ባይሩን ከመጥላቱ የተነሳ እርሱን ከስልጣን ለማባረር አሊ ረዳን ማባረር ግድ እንዲላቸው ስለተረዱ ሴራ ማሴር ጀመሩ። ተድላ ባይሩ በበኩሉ ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደው ጊዜ በላይ፣ ምክር ቤቱ እንዲዘጋ (ሰስፔንድ እንዲደረግ) አደረገ። የተቃዋሚው ሃይል እሮሮውን ወደቀዳማዊ አጼ ሃይለ ስላሴ በማሰማት ጣልቃ እንዲገቡ አደረገ። ንጉሱም የነገሩን ኢ-ህገ መንግስታዊነት በመመልከት አቶ ተድላ ባይሩና ፕሬዜዳንት አሊ ረዳይ ከስልጣናቸው እንዲለቁ አደረጉ። በዚህ ወቅት ቢትወደድ አስፍሐ ወልደሚካኤል ተድላ ባይሩን ተክቶ ተሾመ። አስፍሐ ወልደሚካኤል የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ ነበሩ። ምክር ቤቱ በተራው ሼክ ሳይድ እድሪስ ሙሃመድ አዲምን (የኤርትራ ዲሞክራሲ ግንባር ተወካይ) ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ። ከዚህ በኋላ በአንድነት ፓርቲና በሙስሊም ሊግ መካከል ብዙ መቆራቆስና በኋላም የሙስሊም ሊግ ከሁለት መከፍል ተፈጸመ።

መስከረም 1956 ላይ በተደረገ የምክር ቤት ምርጫ ከ68 መቀመጫወች 32ቱን የአንድነት ፓርቲ አሸንፎ በጠንካራነት ወጣ። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ ጀመሮ በተነሳው የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ሽፍቶች በአገሪቱ መከሰት ጀመሩ። ህዳር 1956 ላይ አጼ ሃይለ ስላሴ ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር ኤርትራን ወደ እናት ሃገሯ ኢትዮጵያ የመመልስ ጉዳይ አንስተው ነበር። በጊዜው የአረብ አብዮት በአካባቢው እየተስፋፋ ስለነበር ለኤርትራም አስጊ ሁኔታ የፈጠረበት አጋጣሚ ነበር። ጥቅምት 1957፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያምና ኡመር ቃዲ ለተባበሩት መንግስታት በጻፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት በሚያሴሩት ሴራ የፌዴራል ደንቡ እየተሸረሸረ እንደሆነ አስገነዘቡ። የፌዴራል ባለስልጣኖች ኡመር ቃዲን በማሰር አንድ አንድ የተነሱ ሰላማዊ ሰልፎችንና አድማዎችን በማፈን ሁኔታውን አለዘቡት።

1958 ላይ የኤርትሪያ ሥራ አስፈጻሚ ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያን የቅጣት ህግ፣ ሰንደቅ አላማና ግብር ስርዓት በኤርትራ ላይ አጸና። ብርጋዴር ጄኔራል አብይ አበበ በዚህ ወቅት የንጉሱ ተወካይ በኤርትራ ሆነው ተሹመው ነበር። በዚህ ትይዩ ሶስት የፖለቲካ ሃይሎች በግብፅ ተደራጅተው ነበር፣ እነርሱም የኤርትራ ነጻነት እንቅስቃሴ - በወልደ አብ ወልደ ማርያም የሚመራ፣ የኤርትራ ነጻነት ግንባር (ጀብሃ) - በእድሪስ ሙሃመድ አዲም የሚመራ፣ የኤርትራ ዲሞክራቲክ ግንባር አንድነት ፓርቲ- በኢብራሂም ሱልጣን የሚመሩ ነበሩ። መጀመሪያ እኒህ ሃይሎች የተባበሩት መንግስታትን ትኩረት ለመሳብ ቢጥሩም ስላልተሳካላቸው በአረብ አገሮችና በሶማሊያ እርዳት ወደ ትጥቅ ትግል ገቡ።

ግንቦት 1960 ላይ ምክር ቤቱ የኤርትራ አስተዳደር፣ በኢትዮጵያ ንጉስ ሃይለ ስላሴ ስር የሚለውን ስያሜ ለኤርትራ መንግስት መረጠ። ነገር ግን የኢኮኖሚው አለመረጋጋት በሰራተኛው መደብ ውስጥ አድማና ተቃውሞ አስነሳ። ይህ የኢኮኖሚ ቀውስ ኢ-ኢትዮጵያዊ ቅርጽ ነበረው። 1961 ላይ እድሪስ አዋተና ጥቂት ተከታዮቹ በስሜን ምዕራብ ኤርትራ የትጥቅ ትግል አስነሳ። ግንቦት 1962 ተማሪዎች የኤርትራ ነጻነትን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ እንዲሁም በዚሁ ውቅት ኢ-ኢትዮጵያዊ ሴራ በአገሪቱ ውስጥ ተደርሶበት ከሸፈ። ሐምሌ 1962 ላይ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሁኔታውን ለማረጋጋት ወደ ኤርትራ ተጉዘው ነገሮች ሊረግቡ ቻሉ። ከአምስት ወር በኋላ ህዳር15፣ 1962 የኤርትራ ምክር ቤት ባደረገው ምርጫ ፌዴሬሽኑ እንዲፈርስና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቀላቀል ወሰነ። ምርጫውን ተከትሎ አጼ ሃይለስላሴ የፌዴራሉን ደንብ ውድቅ በማድረግ ኤርትራ የኢትዮጵያ 14ኛ ጠቅላይ ግዛት አደረጉ።

 
 

የኢትዮጵያ ክፍለ ሐገር (1962-1991)

ለማስተካከል

ኤርትራ የኢትዮጵያ ክፍለ ሐገር ከሆነች በኋላ ያለው ጊዜ በሁለት ጉልህ ዘመናት ይከፈላል፣ እነርሱም የዘውዱ ጊዜና የደርግ ዘመናት ናቸው።

የዘውድ ዘመናት (1962-1974)

ለማስተካከል

በዘውዱ አገዛዝ ወቅት ከኢትዮጵያ ወገን አንድ ወጥ ሳይሆን ያመነታ ሁለት አይነት አቋም ታይቷል፡ የመጀመሪያው አቋም በጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ይመራ የነበር ሲሆን አቋሙም ሙሉ በሙሉ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያው ስርዓት ማምጣትና ማዕከላዊነትን ማስፋፋት ነበር። ሁለተኛው አቋም ኤርትራን ከ1964-70 ያስተዳድሩ በነበሩት ራስ አስራተ ካሳ የሚመራ ሆኖ የኤርትራን ማንነት በማይነካ መልኩ፣ ግትር ያለ አቋም ሳይይዝ፣ መንግስት አስተዳደሩን እየለዋወጠ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲተዳደር ማድረግ ነበር። ለአስራተ ካሳ አቋም መነሻ በክርስቲያን ኤርትራውያን ላይ የነበረው እምነት ነበር። ስለሆነም ኤርትራ የበለጠ ነጻነት ቢሰጣት አገሪቱ ጸንታ ትቆማለች የሚል ነበር።

ከኤርትራኖችም አንጻር ሁለት መንታ አቋም ነበር። በተለይ ራስ አስራተ ካሳ የኤርትራ አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት የተማረው ክርስቲያኑ የኤርትራ ክፍል ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያ ደጋፊ ነበር። ብዙ የኤርትራ ክርስቲያኖች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በሃብት የበለጸጉ ኤርትራውያንን መቀላቀል ቀጠሉ። በቁጥር ጥቂት የማይባሉ ኤርትራውያን በዘውዱ ሥርዓት ውስጥ የመሪነት ቦታን አገኙ። በአንጻሩ ያልተማረው ወጣቱ ክፍልና፣ በእንግሊዙ ወታደራዊ አስተዳደር ስልጣን የነበረው ይህን አይነት ኢትዮጵያዊነት ሊቀበል አልቻለም። አብዛኛው የሙስሊም ክፍልም እንዲሁ አልተቀበለም።

መላው አረባዊነት እና ጀብሃ

ለማስተካከል

ብዙ የምዕራብ ኤርትራና የምጽዋ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች ጀብሃን (የኤርትራ ነጻነት ግንባር)ን መቀላቀል ጀመሩ። ጀብሃ በ1960ዓ.ም ካይሮ ውስጥ የተመሰረተ ግንባር ነበር። እኒህ ሙስሊሞች በጊዜው በካባቢው ተንሰራፍቶ የነበረውን መላው አረባዊነት በመዋስ የኤርትራ ህዝብ አረባዊነትን እንደ መፈክር አነገቡ። በዚያውም በአረብ አገሮች ይካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ስልት በጥቅም ላይ ማዋል ጀመሩ። የናስሪዝም እና የባቲዝም ንቅናቄዎችን ከመካከለኛው ምስራቅ በመዋስ ገንዘባቸው አደረጉ።

የጀብሃ መፈረካከስና የኤርትራ ህዝብ ነጻነት ግንባር

ለማስተካከል

በ60ዎቹ መጨረሻ፣ ምንም እንኳ ጀብሃ እድገት ቢያሳይም የመላው-አረባዊነት አቋሙን በመጥላት አንጎራጓሪ ክርስቲያን ወጣት ኤርትራውያን ሊደግፉት አልቻሉም። ጠረፍ ነዋሪ ሙስሊሞች ጀብሃ በምዕራብ ሙስሊሞች የተሞላና እኛን የረሳ ነው በማለት ለመደገፍ አልፈለጉም። የመላው-አረባዊነት መፈክርም በአረብ አገሮች በተነሳ የርስ በርስ ሽኩቻ ተነኳኮተ። ከዚህ በተጨማሪ ጀብሃ ከሁለት ተከፍሎ በክርስቲያኖች አውራነት የተመሰረት -- የኤርትራ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ሻዕቢያ) ሲቋቋም የኤርትራው ትግል ያበቃለት መሰለ ። ሆኖም ግን በጠቅላይ ግዛቱ የሚካሄደው ጦርነት የራስ አስራተ ካሳ አቋም የማይሰራ ስላስመሰለ ህዳር 1970 ላይ ራስ አስራተ ካሳ ከኤርትራ ስልጣናቸው እንዲነሱ ሆነ። ከዚህ በኋላ ወታደሮች በወታደራዊ ስልት ችግሩን እንዲፈቱ ነጻነት ተሰጣቸው።

የደርግ ዘመናት (1974-1991)

ለማስተካከል
 
የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቲ ስብሰባ፣ 1984፣ አዱሊስ

ኢትዮጵያ አብዮት መፈንዳት በኋላ የተነሳው ደርግም እንዲሁ ፖሊሲው ያመነታ ነበር። የደርግ የመጀመሪያው ሊቀመንበር የነበረው የኤርትራው ተወላጅ ጄኔራል አማን አንዶምአገሪቱ በኤርትራ ላይ ትከተል የነበረውን ፖሊሲ ለመገምገም ሞክሯል። በእርሱ ፖሊሲ መሰረት ኤርትራ በኢትዮጵያ ስር ሆና ነገር ግን የራሷ የፖለቲካ ማንነት እንዲኖራት የሚፈቅድ ነበር። አማን አንዶም ከተገደለ በኋላ የርሱ ፖሊሲ ተቀይሮ እስከ 1991 ድረስ የሚሰራበት ፖሊሲ በኮሌኔል መንግስቱ ሃይለማርያምአማካይነት ተፈጻሚነትን አገኘ። ይህ አዲሱ ፖሊሲ በኤርትራ እንቅስቃሴዎች ላይ ወታደራዊ ድልን በመቀዳጀት ላይ ያተኮረ ነበር።

በዚህ ሁኔታ፣ አብቅቶለታል ተብሎ የነበረው የኤርትራ አመጽ ማንሰራራት ጀመረ። በ1970ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ሻዕቢያ ሙሉ ጥቃትን ማድረስ ጀመረ። ምንም እንኳ ሁሉም ግንባሮች የኢትዮጵያን ሰራዊት የሚታገሉ የነበሩ ቢሆንም፣ ኤርትራውያን አንድ መሆን አልቻሉም ነበር። በተለይ ማርክሲስት የነበረው ሻዕቢያ ብዙ ክርስቲያን ኤርትራውያን ሲቀላቀሉት፣ ኃይሉ ከማደጉ የተነሳ፣ በመላው አረባዊነት አራማጁ ጅብሃ ላይ ጦርነት መክፈት ጀመረ። ከ1981-84 በተደረገ እርስ በርስ ጥሮነት ሻዕብያ የበላይነቱን ተጎንጻፎ ብቅ አለ። ከ80ዎቹ አጋማሽ ጀመሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄድ የነበረው ጥርነት እየተጠናከረ ሲሄድ ሻዕቢያ ወሳኝ ድሎችን ማስመዝገብ ጀመረ። 1987 ላይ ሶቭየት ህብረት ለደርግ የሚያደርገውን እርዳታ ሲያቋርጥ ሁኔታዎች ለሻዕቢያ ተመቻቹ። መጋቢት 1988 የአፋቤት ጦርነት ተብሎ በሚታውቀው የሻዕቢያ ሰራዊት በደርግ ሰራዊት ላይ ስልታዊ የሆነ ድል ተቀዳጀ። ከዚህ በኋላ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ስልጣን እየገነነ ግንባሩም ድል እየተጎናጸፈ ሄዶ ግንቦት 1991፣ በኢትዮጵያ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኤርትራ ኢ-ጥገኝነቷን ለማግኘት ቻለች። የኤርትራ ትግል በኢትዮጵያ ላይ ብዙ አሻራ የተወ ሲሆን በተለይ የነጻነት ግንባር ጽንሰ ሃሳብን ከአረብ አገሮች በማስመጣት በአካባቢው ማስፋፋቱ ተጠቃሽነት አለው።

 
 

ሃገረ ኤርትራ (ከ1991 በኋላ)

ለማስተካከል

አጠቃላይ የአገሪቱ ሁናቴ፣ በተለይ የውጭ ግንኙነት

ለማስተካከል

ኤርትራ እራሷን ከቻለች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የኢኮኖሚ እድገትን አሳይታለች። ሆኖም ግን ከጎረቤቶቿ ጋር የሰላም ግንኙነት አልነበራትም። ከሱዳንጋር እርስ በርስ በመወነጃጀል በ1990ወቹ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ገብተው ነበር። 1995 እና 96 ደግሞ ከየመን ጋር በሐኒሽ ደሴቶች ዙሪያ ጦርነት አድርጋ 1998 ላይ በተ.መ. ውሳኔ መሰረት ደሴቶቹ ለየመን ተሰጡ። ከዚህ በኋላ ቀዝቀዝ ያለ ሰላም በሁለቱ መካከል ሰፈነ።

ከኢትዮጵያ ጋር የነበራት ግንኙነት መጀመሪያ የወዳጅነት ቢሆንም በኋላ ላይ በንግድና በባህር ወደብ አቅርቦት ዙሪያ በተነሱ ጥያቄዎች ውጥረት ገጠመ። 1998ዓ.ም. ላይ ባድሜ በተባለች የጠረፍ መንደር ዙርያ በተነሳ የድንበር ግጭት ውጥረቱ ገንፍሎ ወጥቶ ወደ ጦርነት አመራ። ከሁለት አመት ጦርነት በኋላ ታህሳስ 2000 ላይ የተ.መ. ሰላም አስከባሪ ሃይል በኢትዮጵያ-ኤርትራ ድንበር ላይ ተሰማራ። የአለም አቀፉ የድንበር ኮሚሽን ድንበሩን ለማካለል የወሰደው ውሳኔ በኤርትራ ተቀባይነት ሲያገኝ በኢትዮጵያ ዘንድ በመሪህ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቶ ነገር ግን በተግባር ደረጃ የቤተሰቦችንን መለያየት ይፈጥራል በሚልና ሌሎች ምክንያቶች ተቀባይነት አላገኘም። ኤርትራ በበኩሏ የተ.መ. የሰላም አስከባሪው ክፍል በስለላ ስራ የተሰማራ ነው በማለትና ጫና በመፍጠር 2008 ዓ.ም. ኤርትራን ለቆ እንዲሄድ አደረገች። በዚያው አመት ኤርትራ ወታደሮቿን በራስ ዱሜራ አካባቢ በብዛት ስታሰማራ ከጅቡቲ ጋር የድንበር ጥል ገባች። ይህን ተከትሎ በተነሳ ጦርነት ወደ 30 ሰዎች ሞቱ።

ፖለቲካዊ አደረጃጀት፣ በተለይ የአገር ውስጥ አደረጃጀት

ለማስተካከል

ከግንቦት 1991 በኋላ ኤርትራ ትመራ የነበረው በጊዜያዊ መንግስት ሲሆን መሪዎቹም የቀደሙት የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ነበሩ። የኤርትራምርጫ(ሚያዚያ 23-25) ከተደረገ በኋላ ግንቦት19,1993 ይሄው ጊዜያዊ አካል የኤርትራ ሽግግር መንግስት መሆኑን አወጀ። አላማውም አዲስ ህገ መንግስት እስኪጸድቅና ምርጫ እስኪካሄድ አገሪቱን ለ4 አመት ማስተዳደር ነበር። ከ5 ቀን በኋላ ኢ-ጥገኛ ኤርትራ ግንቦት 24,1993 ላይ በኦፊሴል ታወጀ። የሽግግሩ መንግስት ህግ አርቃቂ አካል (ሀገራዊ ባይቶ) 30 የሻዕቢያ ማዕከላዊ አካላትን እና 60 አዳዲስ አባላትን የያዘ ነበር። 1993 ላይ ይሄው አካል የኤርትራን የመጀመሪያ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መረጠ። ፕሬዜደንቱ የአገሪቱና የመንግስቱ የበላይ አካል ሲሆን በህግ አርቃቂው ኮሚቴ እና በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ሙሉ ስልጣን አለው። በተጨማሪ አቶ ኢሳያስ የሰራዊቱ መሪ እና የሻዕቢያ ዋና ሃላፊ በመሆን ሃይላቸው የገነነ ነው። ከ1994 ጀምሮ ሻዕቢያ ስሙን ቀይሮ ህዝባዊ ግንባር ለፍትሕና ለዲሞክራሲ PFDJ ተባለ። ግንቦት 1997 የተጠበቀው ኤርትራዊ ህገ መንግስት በጉባኤ ቢጸድቅም ተፈጻሚነት አጣ። የፓርላማ እና የፕሬዜደንት ምርጫም እንዲሁ ሳይደረግ ቀረ። 150 አባላት ያሉት የአሁኑ ሀገራዊ ባይቶ ይቀደመውን ኮሚቴ 1997 ላይ የተካ ሲሆን 75 የPFDJ ሹሞችና እና ተጨማሪ 75 የተመረጡ አባላትን አጠቃሎ ይዟል።

የአስተዳደር ክፍሎች

ለማስተካከል
 
የኤርትራ አስተዳደር ክፍሎች

በአሁኑ ወቅት ኤርትራ በ6 ዞባዎች ይከፈላል። እኒህ በተራቸው በንዑስ ዞባዎች ይከፈላሉ። የዞባወቹ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ በአገሩ የውሃ አቅርቦት ጠባይ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የኤርትራ መንግስት ይህን ያደረገበት ምክንያቱን ሲገልጽ እያንዳንዱ አስተዳደር በራሱ የእርሻ አቅም ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው እና ታሪካዊ አውራጃዊ ርስበርስ ግጭቶችን በዚያው ለማስወገድ ነው።

ዞባዎቹ እና የዞባዎቹ ክፍሎች እኒህ ናቸው:

ቁጥር ዞባ ንኡስ ዞባ
1 ማዕከላዊ ዞባ
ዞባ ማእከል
በሪኽ, ጋላ-ነፍሒ, ሴሚናዊ ምብራቕ አስመራ, ሰረጅቓ, ደቡባዊ ምብራቕ አስመራ, ሰሜናዊ ምዕራብ አስመራ, ደቡባዊ ምዕራብ አስመራ
2 ደቡብ ዞባ
ዞባ ደቡብ
ዓዲ-ቐይሕ, ዓዲ-ዃላ,ዓረዛ, ድባርዋ, ደቀምሓረ, ማይ-ዓይኒ, ማይ-ምነ,መንደፈራ, ሰገነይቲ, ሰንዓፈ, ጾሮና
3 ጋሽ በረካ
ዞባ ጋሽ ባርካ
ኣቑርደት, ባረንቱ,ድገ, ፎርቶጎኘሃይኮታሎጎ-ዓንሰባመንሱራሞጎሎሞልቂጎሉጅሻምብቆተሰነይላዕላይ-ጋሽ
4 ዓንሰባ
ዞባ ዓንሰባ
ዓዲ-ተከሌዛን,አስማጥ, ዒላ-በርዕድ, ገለብ, ሓጋዝ,ሓልሓል, ሃበሮ, ከረን, ከርከበት, ሰልዓ
5 ሰሜናዊ ቀይ ባሕር
ዞባ ሰሜናዊ ቀይሕ ባሕሪ
አፍዓበት, ዳህላክ, ገላዕሎ,ፎሮ, ጊንዳዕ, ቃሮራ, ምጽዋዕ, ናቕፋ, ሽዕብ
6 ደቡባዊ ቀይ ባሕር
ዞባ ደቡባዊ ቀይሕ ባሕሪ
አራዕታ, ማእከል ደንካልያደቡብ ደንካልያዓሰብ

የሕዝብ ስብጥር

ለማስተካከል

ታዋቂ ኤርትራውያን

ለማስተካከል

ኣቶ ወልደአብ ወልደማሪያምዓብደል ቃድር ከቢረ ራስ ወልደሚካኤል

ሓሚድ እድሪስ ዓዋተ

እብራሂም ሱልጣን

ባሕታ ሓጎስ

ተድላ ባይሩ

አማን አንዶም

ኢሳያስ አፈወርቂ

ስብሓት ኤፍሬም

ሃይለ ወልደትንሳኤ (ድሩዕ)

ጴጥሮስ ሰለሙን

ማሕሙድ ኣሕመድ ሸሪፎ

ብርሃነ ገብረእግዚኣብሄር

በራኺ ገብረስላሴ

ጀርማኖ ናቲ

ዑቕበ ኣብርሃ

ሳልሕ ኬክያ

እስቲፋኖስ ስዩም

መስፍን ሓጎስ

የማነ ገብረሚካኤል (ባርያ)

ኣብራሃም ኣፈወርቂ

ተኸስተ ሰለሙን

ዮሃንስ ትኳቦ

ኪሮስ ኣስፋሃ

የማነ ተኸስተ

ደሳለኝ ነጋሽ

ዮናስ ዘካርያስ

ስብሓት ኣስመሮም

ሳምሶን ሰለሙን

ቢንያም ያሬድ

ቢንያም በርሀ



Ibrahim Harun

Mear Mussa

ali ibrhm

wedi fenql

sbhat efrem

gerzgher wechu