ድዋይት አይዘንሃወር
(ከጄኔራል አይዘንሃወር የተዛወረ)
ድዋይት አይዘንሃወር (እንግሊዝኛ: Dwight D. Eisenhower) የአሜሪካ ሠላሳ አራተኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕረዝዳንቱ ሥልጣን ላይ የወጡት እ.አ.አ. በ1953 ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ሁነው የተሾሙት ሪቻርድ ኒክሰን ናቸው። ፕሬዝዳንቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የነበሩ ሲሆን ከሥልጣን የወረዱት እ.አ.አ. በ1961 ነበር።