ደብረ ማርቆስኢትዮጵያአማራ ብሔራዊ ክልል የምትገኝ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ናት። እንዲሁም ከተማዋ የ ጉዛምን ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ናት። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ85,597 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 43,229 ወንዶችና 42,368 ሴቶች ይገኙበታል። መገኛ

የደብረማርቆስ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቅ ጎጃም ከአዲስ አበባ በ 300 ኪ.ሜ ከባህር ዳር ደግሞ 253 ኪ.ሜ ፣ በ 37021’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 43’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡

አመሰራረት

ደብረማረቆስ ከተማ የጎጃም ገዥ በነበሩት ደጃዝማቸ ተድላ ጓሉ በ1845 ዓም የተቆረቆረች ሲሆን የከተማዋም መጠሪያ መንቆረር ይባል ነበር፡፡ በ 1872 ዓም ወደ ሥልጣን የመጡት ንጉስ ተክለሃይማኖት ካሁኑ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መመስረት ጋር ተያይዞ የከተማዋ ስያሜ መንቆረር መባሉ ቀርቶ ደብረ ማረቆስ እንዲሆን አዋጅ በማስነገራቸው የከተማዋ መጠሪያ ሊሆን በቃ፡፡ ደብረማርቆሰ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን ከተማዋ በስሯ 6 ቀበሌዎችና ማዘጋጃ ቤት ያሉት የከተማ አስተዳደር አላት፡፡ በ2002 ዓ.ም የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ [1]

በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ60,796 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል:: የከተማው አቀማመጥ በ10°20′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°43′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።[2] ደብረ ማርቆስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሰረተ ልማት እየተሟላላት ነው። ከተማዋ አዲስ ድረገጽ ከፍታለች።

ደብረ ማርቆስ በ1894 - ራስ በዛብህ ግቢ


  1. ስዩም ይዘንጋው ድንቁ (talk) 14:14, 23 ጁላይ 2019 (UTC)

ምንጮች ለማስተካከል

  1. ^ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን Archived ኦገስት 13, 2007 at the Wayback Machine, population.pdf
  2. ^ Butler, Rhett A., 2005 population estimates for cities in Ethiopia

3 http://www.mwud.gov.et/web/debremarkos/home Archived ማርች 19, 2015 at the Wayback Machine