ኦሊቨር ክሮምዌል
ኦሊቨር ክሮምዌል (ሚያዝያ 30 ቀን 1591 ዓ.ም.-መስከረም 6 ቀን 1651 ዓ.ም. የኖሩ) በንጉሥ ፋንታ የእንግሊዝ አገር ጠባቂና መሪ ነበሩ።
የእንግሊዝ ብሔራዊ ጦርነት በጀመረበት ጊዜ (1634 ዓ.ም.) ዖሊቨር ክሮምዌል የፒዩሪታን ወገን መሪ ሆነው ነበር። በተደረገው አብዮት በንጉሡ 1 ቻርልስ ይሙት በቃ ከተፈረደባቸው ቀጥሎ (1641 ዓ.ም.) አገሩ ያለ ንጉሥ መንግስት ሆኖ የእንግሊዝ ኅብረተሠብ (Commonwealth ወይም የጋራ ደኅንነት) ይባል ነበር። በ1645 ዓ.ም. የክሮምዌል ማዕረግ «ጌታ ጠባቂ» ሆነ። ሆኖም እንደ ንጉሥ ያሕል ሥልጣን ነበራቸው። የፕዩሪታን ወገኖች በጽናት የሮማ ቤተክርስቲያንና ፓፓን እንደ ተቃወሙት መጠን በዚያን ዘመን የፕሮቴስታንት ኮዝ (ምክንያት) ተግፋፋ። ከዚህ በላይ የኤጲስቆጶሳዊ ወይም የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን (አንግሊካን) ተቃዋሚዎች ነበሩ።
በ1650 ዓ.ም. ክሮምዌል በድንገት ከትኩሳት ታምመው በቅርቡ ዓረፉና ልጃቸው ሪቻርድ ክሮምዌል ተከታያቸው ጌታ ጠባቂ ሆነ። ሪቻርድ ግን እንደ አባቱ ኃይለኛ መሪ አልነበረምና በጥቂት ጊዜ ውስጥ (በ1651 ዓ.ም.) ከሹመቱ ወረደ። ከአንድ አመት ችግሮች በኋላ በ1652 ዓ.ም. ንጉሣዊው ወገን ወደ ሥልጣን ተመለሰና የ1 ቻርልስ ልጅ 2 ቻርልስ ዙፋኑን ያዙ።