ኪጋሊሩዋንዳ ዋና ከተማ ነው።

መሀል ኪጋሊ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 851,024 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 01°56′ ደቡብ ኬክሮስ እና 30°04′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ኪጋሊ በ1899 ዓ.ም. በጀርመን ግዛት ተመሠረተ። ሆኖም ሯንዳ ነጻነት በ1953 ዓ.ም. እስከሚያገኝ ድረስ ዋና ከተማ አልነበረም። ከነጻነት በፊት የሟሚ (ንጉሥ) መቀመጫ በንያንዛ ሲሆን የጀርመኖች መቀመጫ በአስትሪዳ (የዛሬ ቡታሬ) ተገኘ።

መጋቢት 28 ቀን 1986 ዓ.ም. ጀምሮ በሁቱ እና በቱጺ ነገዶች ላይ በደረሰው ፍጅት አንድ ሚሊዮን ያሕል ሰዎች በኪጋሊ ተገደሉ።