የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካቦትስዋናዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው።

Republic of Zimbabwe
የዚምባᎆ ሬፑብሊክ

የዚምባብዌ ሰንደቅ ዓላማ የዚምባብዌ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የዚምባብዌመገኛ
የዚምባብዌመገኛ
ዋና ከተማ ሀራሬ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
 
ኤመርሰን ምናንጋጓ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
390,580 (59ኛ)
ገንዘብ የዚምባብዌ ዶላር
ሰዓት ክልል UTC +2
የስልክ መግቢያ +263

ታሪክ ለማስተካከል

ከተገዢነት በፊት ለማስተካከል

ድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅየዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር።

1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ።

የሮዴዢያ ጊዜ ለማስተካከል

1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው።

የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል።

ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች።

የሰፋሪዎች አመራርና የእርስ -በርስ ጦርነት ለማስተካከል

ኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ።

የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር።

የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ።

1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።

ሙጋቤ በ ኅዳር 12 ቀን 2010 ዓም ማዕረጋቸውን ተዉ።