ቦሊቪያ
ቦሊቪያ በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማው ላፓዝ ነው።
ኤስታዶ ፕሉሪናሲዮናል ዴ ቦሊቪያ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Himno Nacional de Bolivia «የቦሊቪያ ብሔራዊ መዝሙር» |
||||||
ዋና ከተማ | ላፓዝ ሱክሬ (በይፋ) |
|||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እስፓንኛ | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዝዳንት |
ኤቮ ሞራሌስ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
1,098,581 (27ኛ) 1.29 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት |
11,410,651 (81ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ቦሊቪያኖ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC −4 | |||||
የስልክ መግቢያ | 591 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .bo |
11 ሚሊዮን ሕዝብ ያሉበትና ምንም የባሕር ጠረፍ የሌለው አገር ነው። በ2001 ዓም ስሙ በይፋ ከ«የቦሊቪያ ሪፐብሊክ» ወደ «የቦሊቪያ ብዙ-ብሔሮች ሪፐብሊክ» ተቀየረ። ስሙ «ቦሊቪያ» ከ1817 ዓም. ጀምሮ ስለአብዮታዊው አለቃ ሲሞን ቦሊቫር ክብር ደረሰ። ከ1974 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ኖርዋል።
ቦሊቪያ ከፍተኛ አንዴስ ተራሮች ሰንሰለት አለው፤ ላፓዝም ከማናቸውም የአለም ዋና ከተሞች ይልቅ ከባሕር ደረጃ በላይ ከፍተኛነት አለው። በጫፎቹም አመዳይ ይታያል። በዝቅተኛ ሥፍራዎች በጣም የሞቀ በረሃ አለ። እጅግ ብዙ የተለያዩ አትክልትና እንስሳት በቦሊቪያ ይገኛሉ።
አብዛኞቹ ሕዝቦች ከኗሪ ብሔሮች እንደ ቀቿና አይማራ ናቸው፤ ቋንቋዎቻቸው ሁሉ ከእስፓንኛ ጋራ መደበኛ የስራ ቋንቋዎች ሁኔታ አላቸው።
ልዩ ልዩ የጨፈራና የዘፈን አይነቶች አሉ። አበሳሰሉ በተለይ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ድንች ይጠቀማል። እግር ኳስ በተለይ የተወደደው እስፖርት ነው።