ሚያዝያ ፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፩ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፬ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

ለማስተካከል
  • ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የአሜሪካ የጠፈር በረራና ምርመራ ባለሥልጣን (NASA the National Aeronautics and Space Administration) ’መርኩሪ’ በሚባለው የአገሪቱ የመጀመሪያ የሰው አሳፋሪ መንኮራኩር መርሐ-ግብር የሚሳተፉትን ጠፈርተኞች ለዓለም አስተዋወቀ። እነርሱም፦ ስኮት ካርፔንተር፣ ጎርደን ኩፐር፣ ጆን ግሌን፣ ቨርጅል ግሪሰም፣ ዎልተር ስኪራ፣ አላን ሼፈርድ እና ዶናልድ ስሌይተን ነበሩ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ሁለት የብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ብራያን ሃሪሶን (Brian Harrison) እና ጄምስ ስሌተር (James Slater) ለጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። ከንጉሠ ነገሥቱም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - የጥቁር አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት መሪ የዶክቶር ማርቲን ሉተር ኪንግ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተወለዱበት ከተማ በአትላንታ ተከናወነ። የጆርጂያ ክፍለ-ሀገር ገዥ ሌስተር ማደክስ ዶክቶር ኪንግ የ’ሀገር ጠላት’ ነበሩ በሚል አቋም እቀብሩ ላይ አልሳተፍም ብለው መቅረታቸው ሳይበቃ ለሟቹም ክብር የክፍለ ሀገሩን መንግሥታዊ ቢሮዎች እንደማይዘጉ አስታወቁ።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የቡልጋሪያ ባለ ሥልጣናት ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር በሁለቱ አገሮች መኻል የባህላዊ ግንኙነት እና ልውውጥ ለመወያየት አዲስ አበባ ገቡ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓትን ለመመሥረት የታዘዘውን አጥኒ ሸንጎ በማንኛውም ጉዳይ እንደሚተባበረውና እንደሚረዳው አረጋገጠ። አያይዞም መሬትን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ማንም ሰው ለማልማት ከሚችለው በላይ መሬት መያዝ እንዳይችልና ለወደፊት ከአርሶ አደሮች በስተቀር የእርሻ መሬት ለማንም እንደማይሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ እንደሚወጣ አስታወቀ።


ዕለተ ሞት

ለማስተካከል
  • ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የኒጄር ፕሬዚደንት ኢብራሂም ባሬ ማይናሳራ በአገሪቱ በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተገደሉ።

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ