ፓሪስ (ፈረንሳይኛ፦ /ፓሪ/ Paris) የፈረንሳይ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 9,854,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,110,400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 48°50′ ሰሜን ኬክሮስ እና 02°20′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የፓሪስ አርማ
ቱር ኤፈል

ኬልቶች ከተማ መጀመርያ «ሉኮቶኪያ» ተብሎ በስትራቦን ተመዘገበ። ፕቶሎመይ ደግሞ ከተማውን «ለውኮተኪያ» አለው። ዩሊዩስ ቄሳር አገሩን ሲይዘው ሥፍራውን በሮማይስጥ «ሉቴቲያ» አለው። የኖረበት ጎሣ ፓሪሲ ስለ ተባሉ፣ የከተማው ስም በሙሉ «ሉቴቲያ ፓሪሶሩም» («የፓሪሲ ሉቴቲያ») ተባለ። በኋላ ግን በዩሊዩስ ከሐዲ ዘመን በ352 ዓ.ም. ስሙ በይፋ «ፓሪስ» ሆነ። ይኸው ዩሊዩስ ለ፫ ዓመታት የሮሜ መንግሥትን ከፓሪስ ገዛ። የሷሶን ግዛትፍራንኮች478 ዓ.ም. ወድቆ ፓሪስ የፍራንኮች ዋና ከተማ በ500 ዓ.ም. ተደረገ። ከ784 እስከ 979 ዓ.ም. ድረስ ግን ዋና ከተማቸው በአሕን ሲሆን ከዚያ በኋላ መንግሥታቸው ወደ ፓሪስ ተመለሰ።

1399 እስከ 1411 ዓ.ም. ድረስ በጦርነት ዘመን የቡርጎኝ ኃያላት ከተማውን ለመያዝ ይወዳደሩ ነበር። ከዚያም እስከ 1428 ዓ.ም. ድረስ የእንግላንድ ንጉሥ ሥራዊት ፓሪስን ይይዝ ነበር። በመጨረሻ በ1428 ዓ.ም. የፈረንሳይ ንጉሥ ኃያላት ፓሪስን ነጻ አወጡ፤ ከዚያ አመት ጀምሮ እስከ ዛሬም ድረስ ፓሪስ የፈረንሳይ ዋና ከተማ ሳይቋረጥ ቆይቷል።