መጋቢት ፲፱
መጋቢት ፲፱፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፺፱ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፹፬ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፷፮ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የንግድ እና ኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የቱርክ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ‘አንጎራ’ ስሟ ተለውጦ አንካራ ስትባል፤ የአገሪቱ አንደኛ ከተማ እና በሮማይስጡ ቄሳር ቁስጥንጢኖስ የተመሠረተችው ቁስጥንጢንያ ወይም ኮንስታንቲኖፕል (Constantinople) ስሟን ቀይራ ኢስታንቡል ተባለች።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ ከተሰነዘሩት ዐበያት ሕዝባዊ እሮሮዎች አንዱ በመሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ግፈኝነት እና ሙስና ስለነበር ይሄንኑ ጉዳይ እንዲያጠና የተመሠረተው ኮሚሲዮን አባላት ተሠየሙ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ፤ በጆሃንስበርግ ከተማ፣ በዙሉዎችና ‘የአፍሪቃ ብሔራዊ ሸንጎ’ (African National Congress) ደጋፊዎች መኻል በተከሰተው ሽብር አሥራ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - ለ መብራት ኃይል የእግር ኳስ ክለብ፤ የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ እና የድሬ ዳዋ ባቡር የእግር ኳስ ክለብ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ ለየመን የአል ሳቅር የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቹ ዮርዳኖስ አባይ
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |