መስከረም ፳፱
መስከረም ፳፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፳፱ ኛው ዕለትና የወርኅ መፀው ፬ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፴፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፮ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ መርድ አዝማች አስፋ ወሰን፣ ሎንዶን በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ለማገገም በዛሬው ዕለት ወደ ስዊዘርላንድ አመሩ
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - ሰመጉ (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ))በፕሮፌሶር መስፍን ወልደ ማርያም አነሳሽነት በ፴፪ መሥራች ኢትዮጵያውያን አባላት ተመሠረተ።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. - የሴኔጋል መሪ የነበሩት ሌኦፖልድ ሴዳር ሴንግሆር ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻ ዓ/ም - የሐረር ገዥ የነበሩት ደጃዝማች ይልማ መኮንን (የራስ መኮንን የመጀመሪያ ልጅ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታላቅ ወንድም) አርፈው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአባታቸው መቃብር ተቀበሩ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ የኢትዮጵያ አራተኛው ዋና መላክተኛ (Envoy Extraordinary and Minister Plenipotentiary) የነበሩት ሐኪም አዛዥ ወርቅነህ (Dr. Charles Martin) በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. - የአርጀንቲና ተወላጅ የነበረው፤ በአብዮት ቅስቀሳና ፍልሚያ፣ በተለይም በኩባ አብዮታዊ ትግል የሚታወቀው ኤርኔስቶ ጌቫራ በቦሊቪያ የአብዮት ፍንዳታ ሊያንቀሳቅስ ሲሞክር በተያዘ በማግስቱ ተረሽኖ ሞተ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., Hohler, T.R despatch No.224 [ 37912] (Adis Ababa, October 21, 1907)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O.,FCO 371/1660 -ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
- (እንግሊዝኛ) The London Gazette; p. 5494
- (እንግሊዝኛ) EHRCO; Covenant, Memorandum of Assoiation & Reports (undated)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |