ጉግል
ጉግል (Google) በ1998 እ.ኤ.አ. የግለሰብ ድርጅት ሆኖ ነው የጀመረው። የጉግል ፍለጋ ዌብሳይትን የሰራው እና የሚያስተዳድረው ይሄው ድርጅት ነው።
የጉግል ዓላማ የዓለምን መረጃ ለማሰናዳት ፣ ለማቅረብና ጠቃሚ ማድረግ ነው።
ጉግል (Google, Inc) | www.google.com.et | |||
---|---|---|---|---|
150px| | ||||
ኢንዱስትሪ | ኢንተርኔት | |||
ዓይነት | የሕዝብ | |||
የምስረታ_ቦታ | ማውንቴን ቪው | |||
ዋና_መሥሪያ_ቤት | ማውንቴን ቪው፥ ካሊፎርኒያ፥ አሜሪካ | |||
ቁልፍ_ሰዎች | ኤሪክ ሽሚት፥ ዳይሬክተር ሰርጂ ብሪን፥ ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት ላሪ ፔጅ, የምርቶች ፕሬዝዳንት | |||
ገቢ | $6.138 ቢሊዮን (2005 እ.ኤ.አ.) | |||
የተጣራ_ገቢ | $6.138 ቢሊዮን (2005 እ.ኤ.አ.) | |||
የሰራተኞች_ብዛት | 4,989 (በሴፕቴምበር 30፥ 2005 እ.ኤ.አ.) |
ታሪክ
ለማስተካከልመጀመሪያ
ለማስተካከልጉግል እንደ ፕሮጀክት ሆኖ በጃኑዋሪ 1996 እ.ኤ.አ. በላሪ ፔጅ እና ሰርጂ ብሪን በስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ነው የጀመረው። የፕሮጀክቱ ሀሳብ የድረ ገጾችን ግንኙነት በማጥናት የተሻለ የፍለጋ አገልግሎት መሰጠት መቻል ነበር። ወደ አንድ ድረ ገጽ ብዙ መያያዣዎች ካሉ ያ ድረ ገጽ ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን አለው የሚለውን ሀሳብ ሞክረው ትክክለኛ መሆኑን አዩ (ይህ ዘዴ ፔጅራንክ ይባላል)፣ ለፍለጋ ድረ ገጻቸውም መሠረት ጣሉ። በእዚያ ጊዜ ፍለጋውን የሚያስተናግደው የስታንፎርድ ዌብሳይት ነበር። አድራሻውም http://google.stanford.edu ነበር። ያሁኑ አድራሻቸው google.com በመስከረም 5 ቀን, 1990 (Sep. 15, 1997 እ.ኤ.አ.) ነው የተመዘገበው።
በማርች 1999 እ.ኤ.አ. ድርጅቱ ወደ 165 ዩኒቨርስቲ አቬኑ, ፓሎ አልቶ መስሪያ ቤቱን አዛወረ። ከዚያ በኋላ ሌሎች ሁለት ቦታዎች ቢቀያይሩም በ2003 እ.ኤ.አ. 1600 አምፊቲያትር ፓርክዌይ, ማውንቴን ቪው ወደ ሚገኙ ሕንጻዎች አረፉ። አብዛኛው በዚህ ጊዜ ይጠቀምበት የነበረው የኮምፒዩተር ዕቃዎች ከኢንቴል እና አይቢኤም የተለገሡ ነበሩ።
በፍጥነት የሚያድገው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ጉግልን ማድነቅ ጀመሩ። ተጠዋሚዎች ወደ ዌብሳይቱ ቀላል እና ዓይን የሚስብ ዲዛይን ተሳቡ። በ2000 እ.ኤ.አ. በፍለጋ ቃላት ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ጀመሩ። ነጻ የዌብሳይት ዲዛይን አንዲኖርና የዌብሳይቱን የመጫን ጊዜ ፈጣን እንዲሆን ማስታወቂያዎቹ የምስል ሳይሆን የጽሁፍ ብቻ ናቸው። ሌሎች ተወዳዳሪዎቹ እየወደቁ ሲመጡ ጉግል ግን እያደገ እና እየታወቀ መጣ።
በነሐሴ 29 ቀን, 1993 (Sep. 4, 2001 እ.ኤ.አ.) የዩናይትድ ስቴትስ ፓተንት ቢሮ የፔጅራንክ ዘዴን ፓተንት ለስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሰጠ። በፌብሩዋሪ 2003 እ.ኤ.አ. ጉግል ፓይራ ላብስ የሚባለውን የብሎገር ባለቤት ገዛ።
በ2004 እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ጉግል በወርልድ ዋይድ ዌብ ከነበረው የፍለጋ ጥያቄዎች 84.7 በመቶውን በራሱ ዌብሳይትና በሌሎች ጓደኛ ዌብሳይቶች ያስተናግድ ነበር። በፌብሩዋሪ 2004 እ.ኤ.አ. ያሁ! ከጉግል ጋር የነበረውን ጓደኝነት አቆመ።
በበዓል ቀናት፣ የአንድ ነገር መታሰቢያ ቀናት እና ልዩ ቀኖች የጉግል ዌብሳይት አስቂኝ ነገሮችን ይይዛል። ከነዚህም ታዋቂው የድርጅቱን አርማ መለወጥ ነው። ይህም 'ጉግል ዱድልስ' ይባላል።
በየጊዜው አዲስ ነገር ከጉግል ይመነጫል። ጉግል ላብስ የሚባለው የዌብሳይቱ ክፍል አዲስ በሙከራ ያሉ ውጤቶችን ይይዛል። ይህም የተጠቃሚዎችን አስተያየት ስለሚያስገኘው ከተጠቃሚዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያዳብራል። ይህም አዲሶቹን ምርቶች አሰራር ያሻሽላል።
የአርማ ለውጥ
ለማስተካከልበዓመታት ውስጥ የጉግል አርማ ተለውጧል።
-
ከ1995 እስከ 1997 ዓ.ም -
ከ1997 እስከ 1998 ዓ.ም -
ከ1998 እስከ 1998 ዓ.ም -
ከ1998 እስከ 1999 ዓ.ም -
ከ1999 እስከ 1999 ዓ.ም -
ከ1999 እስከ 2010 ዓ.ም -
ከ2010 እስከ 2013 ዓ.ም -
ከ 2013 እስከ 2015 -
ከ 2015 እስከ ዛሬ
- የጉግል አርማዎችን ስብስብ ለማየት
- የጉግል አርማዎችን ያለቅጥ የሚያሳይ Archived ጃንዩዌሪ 10, 2006 at the Wayback Machine ዌብሳይትም አለ
- ይህ ዌብሳይት ደግሞ Archived ማርች 18, 2006 at the Wayback Machine ሰዎች በጉግል የሰሩትን የውሸት አርማዎች ያሳያል
የቃል አመሠራረት
ለማስተካከልጉግል (Google) የሚለው ቃል ጉጎል (Googol) ከሚለው የመጣ ነው። ጉጎል የሚባለው ቃል የተፈጠረው በሚልተን ሲሮታ በ1938 እ.ኤ.አ. በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ሚልተን ኤድዋርድ ካስነር የሚባል ማቲማቲሻን ወንድም/እሀት? ልጅ ነው። የቃሉ አጠቃቀም የጉግልን በኢንተርኔት የሚገኘውን ኢንፎርሜሽን ለማሰናዳት ያለውን ዓላማ ያንፀባራቃል። የጉግል ጠቃላይ መምሪያ ጉግልፕሊክስ (Googleplex) ይባላል።
ዛሬ 'ጉግል' በአንዳንድ ቋንቋዎች እንደ ቃል ይወሰዳል። ትርጉሙም 'የዌብሳይት ፍለጋ ማድረግ' ነው።
ፋይናንስ
ለማስተካከልየጉግል የመጀመሪያ ዕርዳታ ከአንዲ ቤክቶልሸም የተጻፈ የ$100,000 ቼክ ነው።
ዛሬ
ለማስተካከልጉግል እያደገ ሲመጣ ትልቅ ውድድር እየሳበ ይመጣል። አንድ ምሳሌ በጉግል እና ማይክሮሶፍት መሀል ነው። ማይክሮሶፍት ኤምኤስኤን ሰርች የሚባለውን የፍለጋ አገልግሎት በየጊዜው እየለወጠ ከጉግል ጋር የተወዳዳሪ ቦታ እንዲይዝ ይሞክራል። ከዚህም በላይ ሁለቱ ድርጅቶች አንድአይነት አገልግሎቶችን ማቅረብ ጀምረዋል።
ጉግል በፍለጋ አገልግሎት መሪ ስለሆነ እንደ ያሁ! ያሉትን ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ ይጥራል። የጉግልና ያሁ ትኩረት የተለያየ ቢሆንም ጉግል ግን አዳዲስ አገልግሎቶችን እየከፈተ ነው። በጁን 21, 2005 እ.ኤ.አ. ጉግል እንደ ኢቤይ ያሉትን የንግድ ዌብሳይቶችን ለመወዳደር ያለውን ዕቅድ አሳውቋል።
ሠራተኞች
ለማስተካከልበጉግል የመጀመሪያ ዓመታት የሠራተኞች ደሞዝ ትንሽ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ግን ዩጉግል ሼር በከፍተኛ መጠን እያደገ ስለመጣ የሠራተኞች ደሞዝ በአንጻሩ ጨምሯል። ከደሞዝ ሌላ ታዋቂነት እና ሌሎች ጥቅሞች ብዙ አመልካቾችን ስቧል። ከአንድ ላነሰ የሥራ ቦታ አንድ ሺህ አመልካቾች እንዳሉ ተገምቷል።
የድርጅቱ መሥራቾችና ሌሎች ዋና ሠራተኞች አንድ የአሜሪካን ዶላር እየተከፈላቸው ይሰራሉ። እነዚህ ሰዎች የድርጅቱን ብዙ ሼር ይይዛሉ። ማርች 31 2007 የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው ጉግል 12238 ሰራተኞች አሉት።
ቴክኖሎጂ
ለማስተካከልየጉግል አገልግሎቶች በብዙ ሰርቨሮች ውስጥ በሚገኙ ተራ ኮምፕዩተሮች ላይ ነው ያሉት። ኮምፒዩተሮቹ የሊኑክስ ኮምፒዩተር ፕሮግራም ይጠቀማሉ። ድርጀቱ ስለሚጠቀመው ማሽኖች ብዙ ዝርዝር ባይሰጥም በ1996 ከ60,000 በላይ ኮምፒዩተሮችን እንደሚጠቀሙ ይገመታል።
ፔጅራንክ
ለማስተካከልፔጅራንክ (PageRank) ጉግል የፍለጋ ገጾቹ ላይ የዌብሳይቶችን ቅድመተከተል ለማግኘት የሚጠቀመው ዘዴ ነው። በፔጅራንክ እያንዳንዱ ዌብሳይት ቁጥር አለው። ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ጊዜ የዛ ዌብሳይት ደረጃ በፍለጋ ገጹ ላይ ይጨምራል። ይሄ ቁጥር የሚወሰነው ሌሎች ወደዚህ ዌብሳይት በሚያመለክቱ ዌብሳይቶች ነው። የእነዚህ ዌብሳይቶች ቁጥር ከፍተኛ ከሆነ የዚኛውም በአንጻሩ ይጨምራል። በኣንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ ይህ ኣስተማማኝ ላይሆን ይችላል።
የድርጅቱ ባሕል
ለማስተካከልፍልስፍና
ለማስተካከልጉግል የራሱ የተለያዩ ዕምነቶች አሉት። አንዱ 'መጥፎ ነገር ሳትሰራ ገንዘብ ማግኘት ትችላለህ' ይላል። ሊሎች ዋና ሀሳቦች እዚህ ይገኛሉ።
'ሃያ በመቶ' ጊዜ
ለማስተካከልሁሉም የጉግል ኢንጅነሮች 20 በመቶ የሥራ ጊዜያቸውን እነሱ በሚስባቸው ሥራ ላይ እንዲያሳልፉ ያበረታታል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንድ ሥራዎች የጉግል ሌላ አገልግሎት ይሆናሉ።
ጉግልፕሌክስ
ለማስተካከልየጉግል መጥላይ መምሪያ ጉግልፕሌክስ (Googleplex) ይባላል። ይህ ቦታ ለሠራተኞች የተለያዩ መዝናኛዎችን ያቀፈ ነው። ከነዚህም ውስጥ የአካል ማጎልመሻ ክፍል፣ የተለያዩ ስፖርቶች፣ የተለያዩ ምግብና መጠጦች ይጠቀሳሉ።
የስራ ትብብር
ለማስተካከልየሚከተሉት የሥራ አጋሮች ናቸው፦
ዓለምአቀፍ
ለማስተካከልጉግል ከደርዘን በላይ በሚሆኑ ሀገሮች ቢሮዎች አሉት። የተለያዩ ሀገሮች የተለያየ ሕጎች ስላሏቸው ጉግል ሁሉንም ለማስማማት ይሞክራል።
የፍለጋ ዓይነቶች
ለማስተካከል- ምስሎች (Images) - ይህ በኢንተርኔት ላይ ያሉ ምስሎችን ብቻ ለመፈለግ ያገለግላል
- የውይይት መድረኮች(Groups) - የመወያያ ግሩፖችን ለመፈለግ
- ዜና (News) - ከተለያዩ ምንጮች ዜናን ለማንበብ
- ፕሮዳክት ፍለጋ (Product Search) (የድሮ "ፍሩግል" Froogle) - ይህ ድረ-ገጽ ተጠቃሚዎች በኢንተርኔት ዕቃ እንዲገዙ ያስችላል። ፍሩግልን ይዩ
- ሎካል (Local) - በአቅራቢያዎ ያሉ ሱቆችንና ሌሎች የንግድ ቦታዎችን ለመፈለግ ያገለግላል
- እርዝ (Earth) - የዓለም የሳይተላይት ፎቶዎችን የሚያሳይ ፕሮግራም ወደ ኮምፒዩተሮ መጫን ይችላል
- ዴስክቶፕ (Desktop) - በኮምፒዩተሮ ላይ ያሉትን ሰነዶች (ፅሁፍ፣ ፎቶ፣ ድምፅ፣ ምስል) ለመፈለግ
- ቪዲዮስ (Videos) - በኢንተርኔት ላይ ያሉ ቪዲዮችን ለመፈለግ
- ብሎግስ (Blogs) - በኢንተርኔት ላይ ያሉ ብሎጎችን ለመፈለግ
- ስኮላር (Scholar) - ትምህርታዊ ጽሁፎችን ለመፈለግ
- ፋይናንስ (Finance) - የንግድ መረጃ፣ ዜና እና ሰንጠረዦች ለመፈለግ
- ካርታ (Maps) - ካርታዎችንና የመንጃ መመሪያዎችን ለማየት
የውጭ መያያዣዎች
ለማስተካከል- http://www.google.com - የጉግል ዌብሳይት
- http://www.google.com/intl/am/ - የጉግል ዌብሳይት በአማርኛ
- Brin, Sergey; Page, Lawrence (1998). "The anatomy of a large-scale hypertextual Web search engine". Computer Networks and ISDN Systems 30 (1–7): 107–117. doi:10.1016/S0169-7552(98)00110-X. ISSN 0169-7552. http://infolab.stanford.edu/pub/papers/google.pdf በApril 7, 2019 የተቃኘ.
- Barroso, L.A.; Dean, J.; Holzle, U. (April 29, 2003). "Web search for a planet: the google cluster architecture". IEEE Micro 23 (2): 22–28. doi:10.1109/mm.2003.1196112. ISSN 0272-1732. https://semanticscholar.org/paper/8db8e53c92af2f97974707119525aa089f6ed53a. "We believe that the best price/performance tradeoff for our applications comes from fashioning a reliable computing infrastructure from clusters of unreliable commodity PCs.".