ጣና ሐይቅጎንደር ክፍለ አገር ውስጥ ሲገኝ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል።ጣና ሃይቅ በጥንታዊ ቋንቋ (ግእዝ) አገላለጽ ‹‹ጻና ሐይቅ›› ይባላል፡፡ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሐይቁ መጠሪያ ስም “ጣና” መሠረት ሆኖታል ነው የሚባለው።በክርስቶስ ልደት ገደማ ስለግብጽ ብዙ ምርምር ያደረገው ስትራቦ ዓባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ ትልቅ ሐይቅ እንደሚነሳ ያውቅ ነበር ይባላል፡፡ የሐይቁን ስምም ስትራቦ “ሴቦ” ብሎታል፡፡

ጣና ሃይቅ እንዲሁም ጣና ዙሪያ ጎንደር

የሁለተኛው ዘመን የግብጽ መልክዓ ምድር ተመራማሪ ገላውዲዮስ ፕቶሎሚ ደግሞ “ኮሎ” ይለዋል፡፡

የአቴናው ድራማ ጸሐፊ አስክለስ “መዳብ የተቀባው ሐይቅ የኢትዮጵያ ጌጥ” ብሎታል፡፡ ባለቅኔው ሆሜርም “ከሌሎች የተለየና ጥርት ያለ የውኃ ባለቤት ነው” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል።

ጣና በአጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩት 27 ገዳማትን አቅፎ ይዟል።ገዳማቶች በ14ኛ ምእት ዓመት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ባመነኮሷቸው ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ተብለው በሚጠሩት ቅዱሳን አባቶች የተመሠረቱ ናቸው።ከገዳማቶች

መካከል፦

•••ደብረ ማርያም

•••ክብራን ገብርኤል

•••ዑራ ኪዳነምህረት

•••መሀል ዘጌ ጊዮርጊስ

•••አቡነ በትረ ማርያም

•••አዝዋ ማርያም

•••ዳጋ ኢስጢፋኖስ

•••ይጋንዳ ተለሃይማኖት

•••ናርጋ ስላሴ

•••ደብረ ሲና ማርያም

•••ማንድባ መድኃኒዓለም

•••ጣና ቂርቆስ

•••ክርስቶስ ሳምራ ገዳም

•••ራማ መድሕኒ ዓለም

•••ኮታ ማርያም…እና ሌሎችም ገዳማቶች ይገኙበታል።

•••

ሰባቱ ከዋክብት የሚባሉት አኩስም አቅራቢያ የሚገኘው የደብረ በንኮል ገዳም መሥራች አቡነ መድኅነ እግዚእ ደቀ መዛሙርት ናቸው።እነርሱም፦

1.አቡነ ታዴዎስ~ደብረ ማርያም መሥራች

2.አቡነ ዘዮሐንስ~የክብራን እና የእንጦስ ገዳም መሥራች

3. አቡነ በትረማርያም~የዘጌ ጊዮርጊስ መሥራች

4. አቡነ  ኂሩተ አምላክ~የዳጋ እስጢፋኖስ መሥራች

5.አቡነ ኢሳይ~የመንዳባ መድኃኔዓለም መሥራች

6.አቡነ ዘካርያስ~ደብረ ገሊላ መሥራች

7.አቡነ  ፍቁረዮሐንስ~ጣና ቂርቆስ መሥራች ናቸው።

ታሪካዊ የጣና ክፍሎች

ለማስተካከል

ጣና ቂርቆስ

ጣና ቂርቆስ በጣና ሀይቅ ውስጥከሚገኙት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱና ቀዳማዊዉ ሢሆን የተመሠረተው ከክርስቶሥ ልደት በፊት 982 ሲሆን የንጉስ ሰለሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ ከእሥራየል ታቦተ ጽዮንን አጅበው በታቦተ ጽዮን መሪነት በፈቃደ እግዚአብሔር የመኳንንት ልጆችና ታቦተ ጽዮንን የሚያገለግሉ ካህናት እዲሁም ከሌዋዉያን በጠቅላላ ብዙ ሽህ ህዝብ አሥከትሎ ወደ ደሤቱ በመምጣት ይህንን ታላቅ ገዳም መሠረተው፡፡ የቦታውንም ስም ሳፍ ጽዮን መካነ ሣህል በማለት ሠይመውታል፡፡

እስራኤላውያን ካህናት ታቦተ ጽዮንን ከዚህ ገዳም ሲያሥቀምጡ አብሮ የመጣውን ህዝብ ከባህር ውጭ ባለው ሥፍራ ሥላሠፈሩት እስከ ዛሬ ድረስ አከባቢው ነገደ እስራኤል በመባል ይታወቃል፡፡ ከመጡት እስራኤላውያን ካህናት መካከል የሊቀ ካህኑ የሣዶቅ ልጅ አዛርያሥ ይገኝበታል፡፡ ካህኑ አዛርያስ አምልኮተ እግዚአብሔርንና መሠዋተ ኦሪትን ካስፋፋ በሇላ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ በጣና ቂርቆስ ደሴት ነበር መካነ መቃብሩ ያረፈው፡፡ መካነ መቃብሩ የቃል ኪዳኑ ታቦት ድንኳን ካረፈበት ምስራቅ አቅጣጫ በሁለት የድንጋይ ቋጥኞች መካከል ይገኛል፡፡

የጣና ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ከገዳሙ ከፋተኛ ቦታ ላይ የተሰራ ሁኖ የቃል ኪዳኑ ታቦት (ጽላተ ሙሴ) ካረፈችበት ቦታ ምዕራብ አቅጣጫ በቅርብ እርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የቤተ-ክርስቲያኑ ቅርጽ አራት ማዕዘን የሆነበት ምክኒያት የቃል ኪዳኑ ታቦት ድንኳን አምሳያ እንደሆነ መነኮሣት ይገልፃሉ፡፡

ህገ ኦሪትናአዲስ ኪዳን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከበትና የጽላተ ሙሴ ማደሪያ የሆነው ሣፋ ጽዮን ደብረ ሣህል ወይም የዛሬው ጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት ዘመኗ አረጋዊ ዮሴፋንና ቅድስት ሶሎሜን አስከትላ በመላኩ ዑራኤል መሪነት ከዚህ ታላቅ ገዳም 3ወር ከ10 ቀን ከልጇ ጋር ተቀምጣበታለች፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ታላቅ ገዳም ሳለች ይመራ የነበረዉ መላዕክ ለዮሴፍ በህልሙ "ሄሮድሥ ስለሞተ ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ተመለስ" በማለት ሲነግረው ዮሴፍም ወደ ህፃኑ በመቅረብ /ፀአና በደመና/ በደመና ጫናት በማለቱ የገዳሙና የሀይቁ መጠሪያ ስም ጣና በመባል እደቀረ ይነገራል፡፡

የኢትዮጵያ ብርሀን ተብለው የሚጠሩት አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሀንከነገሥታቱ ጋር ወደ ዚህ ቦታ በመምጣት የመጀመሪያውን የክርስትና እምነት ግዝረትን ሽረው ጥምቀትን፡ መሠዋዕተ ኦሪትን ሽረዉ አማናዊዉንየክርስቶስ ስጋና ደም በመሠዋት የክርስትና እምነትን አፅንተውበታል፡፡

አቡነ ሰላማ ጥምቀትን ብቻ ሳይሆንአምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምበትንታቦተ ህግ በቦታው አራት ጽላት በመቅረፅ በዛን ጊዜ እምነቱ ይስፍፍባቸው ወደ ነበሩት ሀገራት በትግራይ አክሱም ፅዮን፡ በጎጃም መርጦ ለማርያም እና ጣና ቂርቆስ፡ በወሎ ተድባበማርያምን በማስተከል ሁሉንም ታቦታት ታቦተ ፅዮን በማለት እንደሰየሙአቸው በቦታው ያለው ታሪክ ያትታል፡፡

አቡነ አረጋዊና አፄ ገብረ መስቀል ወደዚህ ታላቅ ገዳም በመምጣት በረከትን አግኝተዎል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በገዳሙ ለአምስት አመታት በመቀመጥ ምልክት የሌለውን ድጓ ጽፎ ለገዳሙ አበርክቷል፡፡

ብዙ ቅዱሳን አባቶቻችንና ቅዱሳት አንስት እናቶቻችን በምነና እና በጸሎት ፀጋ እግዚአብሔር አግኝተውበታል፡ የተለያዩ ነገስታት አፄ የተባሉባቸውን ዘውዶች፡ አክሊሎች፡ የማዕረግ ልብሶች ጌጣጌጦች እዲሁም ሌሎች የከበሩ ዕቃወች እስከ ዛሬ ተጠብቀው የሚኖሩበት የሀይማኖት ማዕከልና የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ማህደርና መሠረት ነው፡፡

 

ጣና ጭርቆስ ልሳነ ምድር
ዘጌዘጌ
ጣና ሐይቅ

.