እጨጌ በጥንቱ ዘመን ኢትዮጵያውያን ይጠቀሙበት የነበረው የቤተ ክርስቲያን የማዕረግ አይነት ነው። ከፓትሪያርኩ ዝቅ ብሎ ግን ከተቀሩት ጳጳሳት ከፍ ያለ ነበር።

ትርጉሙ ሲብራራ፦ እጨጌ ከወላይትኛው ጨጋ (ጮጌ) የመጣ ሳይሆን መሠረቱ ከግእዙ ሐፄጌ የመጣ ነው፤ ሐጼጌ ማለት የምድር ጠባቂ ማለት ሲሆን በአማርኛ ዐጨ (አጨ) ዕጮኛ ጠባቂ፤ አጨጌ የሃገር ጠባቂ የገዳማትና የአድባራት ዋና ሹም አቡን ማለት ነው፡፡ የአጼው ሁለተኛ ረዳት (ከእቴጌ ቀጥሎ) ያለ ባለሲሶ ድርሻ የሆነ ሹም የሚሰጥ የማዕረግ ስም ነው፡፡ አጨ ጠበቀ፥ እጮኛ ጠባቂ፤ ጌ፦ ስፍራ ቦታ ሃገር፤ (እቴጌ እጨጌ ሰላምጌ ንብጌ ቅዱስጌ ደረስጌ አምባላጌ አሸንጌ ሐረርጌ ጉራጌ እጅጌ አንገትጌ ወገብጌ እራስጌ ግርጌ ወዘተ…) በተገናኘ ጊዜ እጨጌ፦ የሃገር ጠባቂ፥ ባለአደራ፥ ይምድር ዕጮኛ ማለት ነው፤ በግአዝ ሐጼጌ (ሐፄጌ) ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው፡፡ (የቋንቋዎች መወራረስ ቢኖርም እንደ አካባቢው ማይት ይቻላል ለምሳሌ በአራዳ ጮጋ ዝም ማለት እንዲሁም ጮጌ (ጨጋ) በወላይትኛ አባት ማለት ሲሆን፤ ጌ በክስታኒኛ ቤት ማለት ነው ሁሉም ከእጨጌ ጋር በድምጽ እንጂ በትርጉም አይገናኙም፡፡) ተወራራሽ ድምጾች፦ ሐጼ አጼ (ዐፄ) አጤ አጨ (ዐጨ)፡፡ እጨጌ የተሰኘው ማእረግ ይሰጥ የነበረው ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳስ ቅጥሎ ያለ ትልቁ ሹመት ሲሆን፥ እጨጌ ሆኖ የሚሾመው አባት የደብረ ሊባኖስም ገዳም አበምኔትም ነበር፡፡ ከመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሊቀ ጳጳስና ኋላም የመጀመሪያው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስና ሁለተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እጨጌነትንም ደርበው ይዘው ነበር፡፡ በመጀመሪያው የሃገራችን የመደብ አብዮት ዘመን በመንግስት የተሰየመው የተሐድሶ ምክር ቤት እጨጌነቱን ከፓትርያሪኩ በመቀማት የመንግሥት ተወካይ የሆነው የቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እንዲሠራው በመወሰኑ ሦስተኛውና አራተኛው ፓትርያሪኮች እጨጌ አልነበሩም፡፡ በሁለተኛው የዘውግ አብዮት ዘመን ከመንግሥት የሚመደበው ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በመቅረቱና ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመርጠው ሊቀ ጳጳስ ጠ/ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን በመወሰኑ አምስተኛውና አሁን በመንበሩ ላይ ያሉት ፓትርያሪክ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመሰኘት የእጨጌነትን መንበር የመሠረቱት ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም የስያሜው አካል ሆነዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እጨጌነት የፓትርያሪኩ ሥልጣን ስለሆነ የደብረ ሊባኖስ አበምኔት ጸባቴ ተብሎ ይጠራል፡፡

ምንጭ፦ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፡፡ (ል.ሣ.)

ታዋቂ ፊት አፄወች

ለማስተካከል