የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከባድ እና አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት በሽታ አምጪ በሆነው SARS-CoV-2 ቫይረስ ምክንያት የተከሰተ የኮሮናቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ነው። ወረርሽኙ ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘው በቻይና ዉሃን ሁቤ ውስጥ በእ.ኤ.አ. ዲሴምበር 2019 ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በእ.ኤ.አ. ማርች 11 ቀን 2020 በሽታውን የወረርሽኝ ደረጃ ላይ መድረሱን አወጀ። እስከ መጋቢት እ.ኤ.አ. ማርች 29 ቀን 2020 ድረስ ባለው መረጃ መሠረት ከ670 ሺህ በላይ የኮቪድ-19 ኬዞች በ199 አገራት ውስጥ ተመዝግበዋል። በበሽታው 31,191 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 143,840 ገደማ የሚሆኑት ደግሞ አገግመዋል። በወረርሽኙ በዋነኝነት ከተጠቁት አገራት መካከል ቻይናኢጣልያኢራንደቡብ ኮርያ እና ስፔን ይገኙበታል።

ልክ እንደ ኢንፍሉዌንዛ የቫይረሱ ዋነኛ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ከሚረጩ ፈሳሾች ነው። በሽታው ተላላፊ ነው ተብሎ የሚወሰደው ሰዎች የበሽታውን ምልክቶች በሚያሳዩበት ወቅት ቢሆንም አንድ አንድ ጊዜ ምልክቱን የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። አንድ ሰው ለቫይረሱ ከተጋለጠ በኋላ በአማካይ በአምስት ቀን ውስጥ ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል። ነገር ግን ምልክቱ እስኪታይ እስከ ዐሥራ አራት ቀን የሚቆይበት ሁኔታ አለ። የተለመዱት ምልክቶቹ ትኩሳት ፣ ሳል እና የትንፋሽ መቆራረጥ ናቸው። በሽታው ሲባባስ የሣንባ ምች እና የተለያዩ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ሊያስከትል ይችላል። በአሁኑ ጊዜ በሽታው ክትባት ወይም የጸረ-ቫይረስ ህክምና የለውም። በሽታውን ለመከላከል እጅን መታጠብ ፣ ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍን መሸፈን ፣ በሽታው ካለባቸው ሰዎች ራቅ ማለት እናም በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ከነበረ ራስን ለ14 ቀናት ማግለል ይመከራል።

የበሽታውን መስፋፋት ለመቀነስ የጉዞ ዕገዳዎችን መጣል ፣ ለይቶ ማቆያዎችን ማዘጋጀት ፣ ሠዓት እላፊን መጣል ፣ የተለያዩ ሕዝባዊ ዝግጅቶችን መሠረዝ ወይም ማስተላለፍ እና ብዙ ሰዎች የሚገኙባቸውን ተቋሞችን መዝጋት በዓለም ላይ ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ይህ ወረርሽኝ ዓለምአቀፋዊ የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን አስከትሏል። የተለያዩ የባሕላዊ እና የስፖርታዊ ዝግጅቶችም ተሠረዘዋል። በመድሃኒት ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ምግብ ረገድ የአቅርቦት እጥረት ይፈጠራል የሚል ፍርሃትንም በሰዎች ውስጥ አሳድሯል። በዚህም ምክንያት በምዕራቡ ዓለም ሰዎች ዕቃዎችን በማግበስበስ እንደ መጸዳጃ ቤት ወረቀት ያሉ መሠረታዊ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ ዕጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል።

ሥዕላዊ መግለጫዎች ለማስተካከል

የበሽታው ምልክቶች ለማስተካከል

ምልክት[3] %
ትኩሳት 87.9%
ደረቅ ሳል 67.7%
ድካም 38.1%
አክታ 33.4%
ትንፋሽ ማጠር 18.6%
የጡንቻ ወይም የመገጣጠምያ ህመም 14.8%
የጉሮሮ ህመም 13.9%
ራስ ምታት 13.6%
ብርድ ብርድ ማለት 11.4%
ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ 5.0%
የአፍንጫ መደፈን 4.8%
ተቅማጥ 3.7%
ደም ማሳል 0.9%
የዓይን መቅላት እና ማበጥ 0.8%
 
የኮቪድ-19 ምልክቶች
 
የጀርሞችን ስርጭት ያስቁሙ

በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች አንዳንዴ ምንም ምልክት ላያሳዩ ሲችሉ የተቀሩት ደግሞ እንደ ኢንፍሉዊንዛ ዓይነት ምልክቶች የሆኑትን እንደ ድካም ፣ ሳል ፣ ትኩሳት ፣ የትንፋሽ ማጠር እና የጡንቻ ህመሞች ይታዩባቸዋል። የተለመዱት የበሽታ ምልክቶች በቀጣዩ ሰንጠረዥ ውስጥ ተካትተዋል።

በሽታው ሲከፋ ከባድ የሣንባ ምች ፣ የተለያዩ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ፣ ከባድ ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ምንም ምልክት ሳያሳዩ ግን በላቦራቶሪ ምርመራ በሽታው ሊገኝባቸው ይችላል። በዚህም ምክንያት ከነዚህ ሰዎች ጋር ቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የቅርብ ክትትል እንዲደረግላቸው ተመራማሪዎች ይመክራሉ።

የበሽታው ምልክት የመታየት ጊዜ አብዛኛውን ጊዜ አምስት ቀን ቢሆንም ከአንድ ቀን እስከ ዐሥራ አራት ቀን ሊሆንም ይችላል። በአንድ ኬዝ እስከ 27 ቀን የቆየበት ሁኔታም ታይቷል።[4]

መነሻ ለማስተካከል

መተላለፊያ መንገዶች ለማስተካከል

 
ሰው ሲያስነጥስ የሚረጩ ፈሳሾች

የቫይረሱ ቀዳሚ የመተላለፊያ መንገድ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ከሚረጩ ፈሳሾች ነው። ፈሳሾቹ ዓየር ላይ ለትንሽ ጊዜ ቢሆንም የሚቆዩት እንደ ብረት ፣ ካርቶን ፣ መስታወት እና ፕላስቲክ ዕቃዎች ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ። ቫይረሱ ልክ እንደሌሎች ኮሮናቫይረሶች ዓየር ላይ እና አንዳንድ ቁሳቁሶች ላይ እስከ ዘጠኝ ቀን ሊቆይ የሚችልበት ሁኔታዎች አሉ።[5]

ቫይረሱ የሚገኝባቸው አገራት ለማስተካከል

የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአገራት መረጃ የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው የአገራት መረጃ (እስከ እ.ኤ.አ. 23 April 2020)[6]
አገር የዛሬ ኬዞች ሕክምና ላይ ያሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያሉ ዛሬ የሞቱ አጠቃላይ ኬዞች አጠቃላይ የሞቱ አጠቃላይ ያገገሙ
  አሜሪካ 375 717358 14016 25 849092 47684 84050
  እስፓንያ 4635 101617 7705 440 213024 22157 89250
  ኢጣልያ 0 107699 2384 0 187327 25085 54543
  ፈረንሣይ 0 97880 5218 0 159877 21340 40657
  ጀርመን 374 42388 2908 19 151022 5334 103300
  ዩናይትድ ኪንግደም 0 115051 1559 0 133495 18100
  ቻይና 10 959 63 0 82798 4632 77207
  ቱርክ 0 79821 1814 0 98674 2376 16477
  ፋርስ 1030 16702 3105 90 87026 5481 64843
  ሩሲያ 4774 57327 2300 42 62773 555 4891
  ብራዚል 591 18096 8318 28 46348 2934 25318
  ቤልጅግ 908 26507 993 228 42797 6490 9800
  ካናዳ 0 24230 557 0 40190 1974 13986
  ኔዘርላንድስ 887 31302 1050 123 35729 4177 None
  ስዊዘርላንድ 228 7087 386 0 28496 1509 19900
  ፖርቱጋል 371 20332 204 35 22353 820 1201
  ህንድ 427 16735 0 5 21797 686 4376
  ፔሩ 0 11693 396 0 19250 530 7027
  ስዊድን 751 14184 515 84 16755 2021 550
  አየርላንድ 0 6669 147 0 16671 769 9233
  ኦስትሪያ 77 2786 169 12 15002 522 11694
  እስራኤል 94 9067 136 2 14592 191 5334
  ሳዑዲ አረቢያ 1158 11884 82 7 13930 121 1925
  ጃፓን 0 10227 241 0 11950 299 1424
  ቺሌ 0 5750 399 0 11296 160 5386
  ሲንጋፖር 1037 10270 27 0 11178 12 896
  ኤኳዶር 0 9051 141 0 10850 537 1262
  ፓኪስታን 735 8246 60 16 10811 228 2337
  ደቡብ ኮሪያ 8 2051 55 2 10702 240 8411
  ሜክሲኮ 1043 6947 378 113 10544 970 2627
  ፖላንድ 177 8171 160 9 10346 435 1740
  ሮማንያ 386 7091 236 3 10096 527 2478
  የተባበሩት የዓረብ ግዛቶች 518 7063 1 4 8756 56 1637
  ዴንማርክ 161 2295 74 10 8073 394 5384
  ኢንዶኔዥያ 357 6168 0 12 7775 647 960
  ቃጣር 623 7004 72 0 7764 10 750
  ኖርዌይ 0 7117 54 2 7338 189 32
  ቤላሩስ 0 6454 92 0 7281 58 769
  ዩክሬን 578 6479 45 13 7170 187 504
  ቼክ ሪፐብሊክ 4 4924 76 2 7136 210 2002
  ሰርቢያ 0 5955 101 0 7114 134 1025
  ፊሊፒንስ 271 5797 1 16 6981 462 722
  አውስትራሊያ 12 1541 45 1 6661 75 5045
  ማሌዢያ 71 1966 42 2 5603 95 3542
  ዶሚኒካን ሪፐብሊክ 0 4459 135 0 5300 260 581
  ፓናማ 171 4593 97 3 4992 144 255
  ኮሎምቢያ 0 3280 98 0 4356 206 870
  ፊንላንድ 155 2112 60 23 4284 172 2000
  ባንግላዴሽ 414 3951 1 7 4186 127 108
  ግብፅ 0 2448 0 0 3659 276 935
  ሉክሰምበርግ 0 2863 32 0 3654 80 711
  ደቡብ አፍሪካ 0 2515 36 0 3635 65 1055
  ሞሮኮ 91 2956 1 2 3537 151 430
  አርጀንቲና 0 2257 123 0 3288 159 872
  አልጄሪያ 0 1304 40 0 2910 402 1204
  ታይላንድ 13 359 61 1 2839 50 2430
  ሞልዶቫ 0 2041 212 1 2778 76 661
  ግሪክ (አገር) 0 1710 55 0 2408 121 577
  ኩዌት 151 1887 55 1 2399 14 498
  ሃንጋሪ 116 1655 61 14 2284 239 390
  ካዛክስታን 116 1682 29 1 2251 20 549
  ባሕሬን 71 1008 2 1 2098 8 1082
  ክሮኤሽያ 31 1048 19 2 1981 50 883
  አይስላንድ 0 313 5 0 1785 10 1462
  ኦማን 102 1401 3 0 1716 8 307
  ኡዝቤኪስታን 0 1214 8 0 1716 7 495
  ኢራቅ 0 402 0 0 1631 83 1146
  ኤስቶኒያ 33 1355 7 1 1592 45 192
  አዘርባጃን 30 580 14 0 1548 20 948
  አርሜኒያ 50 840 10 0 1523 24 659
  ኒው ዚላንድ 3 370 2 2 1451 16 1065
  ቦስኒያና ሄርጸጎቪና 45 874 4 1 1413 54 485
  ሊትዌኒያ 28 961 17 0 1398 38 399
  ስሎቬኒያ 13 1076 23 0 1366 79 211
  ስሎቫኪያ 81 1022 9 1 1325 15 288
  መቄዶንያ 41 943 14 0 1300 56 301
  አፍጋኒስታን 50 1009 7 0 1226 40 177
  ኩባ 0 808 16 0 1189 40 341
  ካሜሩን 0 723 33 0 1163 43 397
  ጋና 0 1046 4 0 1154 9 99
  ቡልጋሪያ 57 841 37 1 1081 50 190
  ሆንግ ኮንግ 2 333 9 0 1036 4 699
  ጅቡቲ 0 789 0 0 974 2 183
  ኮት ዲቯር 0 628 0 0 952 14 310
  ቱኒዚያ 0 681 32 0 909 38 190
  ናይጄሪያ 0 648 2 0 873 28 197
  ቆጵሮስ 0 679 15 0 790 13 98
  ላቲቪያ 17 634 6 0 778 11 133
  ጊኒ 0 591 0 0 761 6 164
  አንዶራ 0 377 17 0 723 37 309
  ሊባኖስ 6 526 26 0 688 22 140
  ኮስታ ሪካ 0 495 6 0 681 6 180
  ቦሊቪያ 63 588 3 3 672 40 44
  አልባኒያ 29 251 4 0 663 27 385
  ኒጄር 0 447 0 0 662 22 193
  ኪርጊዝስታን 19 321 11 1 631 8 302
  ቡርኪና ፋሶ 0 181 0 0 609 39 389
  ኡራጓይ 0 200 10 0 549 12 337
  ሆንዱራስ 9 441 10 1 519 47 31
  ሳን ማሪኖ 0 386 4 0 488 40 62
  ፍልስጤም 6 384 0 0 480 4 92
  ሴኔጋል 37 216 1 0 479 6 257
  ማልታ 1 238 2 0 445 3 204
  ጆርዳን 0 113 5 0 435 7 315
  ታይዋን 1 168 0 0 427 6 253
  ቡታን 4 304 6 0 420 5 111
  ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 18 305 0 0 377 25 47
  ጓተማላ 26 307 3 2 342 10 25
  ስሪ ላንካ 5 221 2 0 335 7 107
  ሞሪሸስ 0 59 3 0 329 9 261
  ሞንቴኔግሮ 1 195 7 0 316 5 116
  ኬንያ 0 206 2 0 303 14 83
  ቬኔዝዌላ 0 166 4 0 298 10 122
  ማሊ 0 203 0 0 293 17 73
  ሶማሊያ 0 274 2 0 286 8 4
  ታንዛኒያ 0 263 7 0 284 10 11
  ቬት ናም 0 44 8 0 268 0 224
  ጃማይካ 0 218 0 0 252 6 28
  ኤል ሳልቫዶር 13 175 2 1 250 8 67
  ፓራጓይ 0 142 1 0 213 9 62
  ፋሮ ደሴቶች 2 9 0 0 187 0 178
  Congo 0 164 0 0 186 6 16
  ጋቦን 0 140 1 1 166 2 24
  ሱዳን 22 135 0 0 162 13 14
  ሩዋንዳ 0 69 0 0 153 0 84
  ብሩነይ 0 18 2 0 138 1 119
  በርማ 4 113 0 0 127 5 9
  ካምቦዲያ 0 12 1 0 122 0 110
  ማዳጋስካር 0 63 1 0 121 0 58
  ኢትዮጵያ 0 92 0 0 116 3 21
  ትሪኒዳድና ቶቤጎ 0 70 0 0 115 8 37
  ላይቤሪያ 0 73 0 0 101 8 20
  አሩባ 0 30 4 0 100 2 68
  ቤርሙዳ 0 55 10 0 99 5 39
  ሞናኮ 0 64 2 0 94 3 27
  ማልዲቭስ 8 78 2 0 94 0 16
  ቶጎ 0 26 0 0 88 6 56
  ኢኳቶሪያል ጊኔ 0 76 0 0 84 1 7
  ቡታን 9 80 0 0 82 1 1
  ሊክተንስታይን 0 25 0 0 81 1 55
  ባርቤዶስ 0 43 4 0 76 6 27
  ዛምቢያ 0 36 1 0 74 3 35
  Bahamas 5 49 1 0 70 9 12
  ጋያና 0 51 5 0 67 7 9
  ዩጋንዳ 0 17 0 0 63 0 46
  ሃይቲ 0 56 0 0 62 4 2
  ሴየራ ሌዎን 0 55 0 0 61 0 6
  ሊቢያ 0 44 0 0 60 1 15
  ቤኒን 0 26 0 0 54 1 27
  ጊኔ-ቢሳው 0 47 0 0 50 0 3
  ኔፓል 2 38 0 0 47 0 9
  ማካው 0 18 1 0 45 0 27
  ሶርያ 0 33 0 0 42 3 6
  ሞዛምቢክ 0 33 0 0 41 0 8
  ኤርትራ 0 33 0 0 39 0 6
  ሞንጎልያ 0 27 0 0 35 0 8
  ማላዊ 10 27 1 0 33 3 3
  ቻድ 0 25 0 0 33 0 8
  ስዋዚላንድ 0 22 0 0 31 1 8
  ዚምባብዌ 0 22 0 0 28 4 2
  አንጎላ 0 17 0 0 25 2 6
  አንቲጋ እና ባርቡዳ 0 11 1 0 24 3 10
  ምሥራቅ ቲሞር 0 22 0 0 23 0 1
  ቦትስዋና 0 21 0 0 22 1 0
  ላዎስ 0 15 0 0 19 0 4
  ቤሊዝ 0 11 1 0 18 2 5
  ፊጂ 0 10 0 0 18 0 8
  ዶመኒካ 0 7 0 0 16 0 9
  ናሚቢያ 0 9 0 0 16 0 7
  ግሬናዳ 0 9 4 0 15 0 6
  ሰይንት ኪትስና ኒቨስ 0 14 0 0 15 0 1
  ሰይንት ሉሻ 0 0 0 0 15 0 15
  የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ 0 4 0 0 14 0 10
  ሰይንት ቪንሰንትና ዘ ግረነዲንዝ 0 10 0 0 13 0 3
  ቡሩንዲ 0 6 0 0 11 1 4
  ግሪንላንድ 0 0 0 0 11 0 11
  ሲሸልስ 0 5 0 0 11 0 6
  ኒካራጓ 0 1 0 0 10 2 7
  ጋምቢያ 0 7 0 0 10 1 2
  ሱሪናም 0 3 0 0 10 1 6
  ቫቲካን ከተማ 0 7 0 0 9 0 2
  ፓፑዋ ኒው ጊኒ 0 8 0 0 8 0 0
  ሞሪታኒያ 0 0 0 0 7 1 6
  ቡታን 0 4 0 0 7 0 3
  ሳን ቶሜ እና ፕሪንሲፔ 0 4 0 0 4 0 0
  ደቡብ ሱዳን 0 4 0 0 4 0 0
  የመን 0 1 0 0 1 0 0
  1. ^ The Novel Coronavirus Pneumonia Emergency Response Epidemiology Team. The Epidemiological Characteristics of an Outbreak of 2019 Novel Coronavirus Diseases (COVID-19) – China, 2020. China CDC Weekly, 2020, 2(8): 113–122.
  2. ^ Roser, Max; Ritchie, Hannah; Ortiz-Ospina, Esteban (4 March 2020). "Coronavirus Disease (COVID-19)". Our World in Data. https://ourworldindata.org/coronavirus በ12 March 2020 የተቃኘ. 
  3. ^ WHO-China Joint Mission (16–24 February 2020). "Report of the WHO-China Joint Mission on Coronavirus Disease 2019 (COVID-19)". World Health Organization.
  4. ^ "Coronavirus incubation could be as long as 27 days, Chinese provincial government says". Reuters. 22 February 2020. https://www.reuters.com/article/us-china-health-incubation/coronavirus-incubation-could-be-as-long-as-27-days-chinese-provincial-government-says-idUSKCN20G06W. 
  5. ^ Kampf, G.; Todt, D.; Pfaender, S.; Steinmann, E. (March 2020). "Persistence of coronaviruses on inanimate surfaces and their inactivation with biocidal agents". The Journal of Hospital Infection 104 (3): 246–251. 
  6. ^ "Coronavirus Live Updates". በእ.ኤ.አ. 23 April 2020, 16:08 UTC+03:00 የተወሰደ.