ሞሪታኒያ
ሞሪታኒያ (አረብኛ፡ موريتانيا) በይፋ የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ ከአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ በደቡብ-ምዕራብ ከሴኔጋል፣ በምሥራቅና ደቡብ-ምሥራቅ ከማሊ፣ በሰሜን-ምሥራቅ ከአልጄሪያ፣ እና በሰሜን-ምዕራብ ከምዕራባዊ ሣህራ ጋር ትዋሰናለች። የአገሩዋ ስም የመጣው ከጥንቱ የሞሪታኒያ መንግሥት ነው። ዋና እና ትልቁዋ ከተማዋ ኑዋክሾት ናት።
የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: የሞሪታኒያ ብሔራዊ መዝሙር | ||||||
ሞሪታኒያ በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ኑዋክሾት | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | አረብኛ | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ሞሐመድ ኡልድ አብደል አዚዝ ያህያ ኡልድ ሃደሚን |
|||||
ዋና ቀናት ኅዳር ፲፱ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. (November 28, 1960 እ.ኤ.አ.) |
ነፃነት ከፈረንሳይ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
1,030,700 (29ኛ) 0.03 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2005 እ.ኤ.አ. ግምት የ1988 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
3,069,000 (135ኛ) 1,864,236 |
|||||
ገንዘብ | ኡጊያ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | 222 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .mr |
ታሪክ
ለማስተካከልበዛሬው ሞሪታንኒያ በመጀመሪያ የሠፈሩት የባፎር ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ስዎች ከዘላን ሕይወት ወደ ግብርና ከተቀየሩት የመጀመሪያ የሰሃራ ሕዝቦች አንዱ ናቸው። ከ5ኛው እስከ 7ኛው ምዕተ ዓመት፣ ባፎሮች በበርበር ህዝቦች ፍልሰት ምክኒያት ተፈናቀሉ።
ግብርና
ለማስተካከልብዙዎቹ የሞሪታኒያ ሕዝብ በመቆያ ግብርና ቢኖሩም ይሄ ወደ ውጭ አገር ለመላክ አይደለም። በተለይ ወደ ውጭ የሚላከው ብረት፣ ፔትሮሊየም፣ እና ዓሣ ናቸው።
አስተዳደራዊ ክለሎች
ለማስተካከልሞሪታኒያ በ12 ዊላያ በሚባሉ ክልሎችና በአንድ የአስተዳደር አካባቢ ተከፍላልች። እነዚህም ክልሎች በ44 ሙጋታ በሚባሉ ክፍሎች ተከፍለዋል።
ክልል | ዋና ከተማ |
---|---|
አድራር | አታር |
አሳባ | ኪፋ |
ብራክና | አሌግ |
ዳክሌት ኑዋዲቡ | ኑዋዲቡ |
ጎርጎል | ካኤዲ |
ጉዊዲማካ | ሴሊቤቢ |
ሆድ ኤክ ቻርጉዊ | ኔማ |
ሆድ ኤል ጋርቢ | አዩን ኤል አትሩስ |
ኢንቺሪ | አክጁጅት |
ኑዋክሾት (አስተዳደር አካባቢ) | |
ታጋንት | ቲጂክጃ |
ቲሪስ ዜሙር | ፍኤዴሪክ |
ትራርዛ | ሮሶ |