የፈርዖኖች ዝርዝር
የግብጽ ፈርዖኖች ዝርዝር በሥርወ መንግሥታት አከፋፈል እንደ ተለመደ ከማኔጦን የተወረሰ ነው። በተጨማሪ አንዳንድ ሌላ ጥንታዊ ዝርዝር ምንጭ ይታወቃል። ለመሆኑ ለብዙዎች ፈርዖኖች በሥነ ቅርስ የሃይሮግሊፍ መዝገብ በመገኘቱ፣ የስሞቻቸው አጠራር በግብጽኛ አሁን ሊታወቅ ይችላል። ለብዙዎቹም አያሌ ልዩ ስሞች አሏቸው።
ጥንታዊው መንግሥት ለማስተካከል
የጥንታዊ መንግሥት ዘመኖች ቁጥር በትክክል ሊታወቅ አይችልም። ከጥንታዊው ዘመን በኋላ የመካከለኛው መንግሥት (ምሥር) ፈርዖኖች መጀመርያ የገቡት 2130 ዓክልበ. ግድም ስለ ሆነ፣ ጥንታዊው መንግሥት ከዚያው በፊት መጨረስ ነበረበት። ነገር ግን ለያንዳንዱ ፈርዖን የዘመነ መንግሥታቸው ዕድሜዎች በየምንጩ እጅግ ይለያልና በጠቅላላ ምን ያህል ጊዜ እንደ ፈጀ ለማለት ያስቸግራል። በአንዳንድ ሊቃውንት ግምት ዘንድ የተመሠረተው 3200-3100 ዓክልበ. ግድም ቢሆንም፣ ይህ ግመት ብቻ መቅረቱ ማስታወስ ያሻል።
ከ1ኛው ሥርወ መንግሥት አስቀድሞ በደቡብ የነገሡት አለቆች ለማስተካከል
1ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
2ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
3ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
4ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
5ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
6ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
7ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
ማኔጦንና ሌሎቹ ጥንታዊ ምንጮች ለ7ኛው ሥወ መንግሥት በርካታ ተጨማሪ ስሞች (እስከ 70 ፈርዖኖች ድረስ) አስገብተዋል። ከነዚህም ሁሉ አንዱ ስም ብቻ (የነፈርካሬ ነቢ) ኅልውና በሥነ ቅርስ ተረጋግጧል። ስለዚህ ብዙ ሊቃውንት 7ኛው ሥርወ መንግሥት እንደ ኅሣዊ (ታሪካዊ እንዳልሆነ) ይቆጥሩታል።
8ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
የማኔጦን 8ኛው ሥርወ መንግሥት እንደገና ብዙ ተጨማሪ ስሞች (በጠቅላላ 27) አሉት። ከነዚህ ሁሉ 3 ብቻ በዕውነት እንደ ነገሡ ይታወቃል። እነርሱም ቃካሬ ኢቢ፣ ነፈርካውሆር እና ዋጅካሬ ናቸው። ሌሎቹ ስሞች በኋለኛ ዘመን በውሸት እንደ ተፈጠሩ ይታሥባል።
መጀመርያው ጨለማ ዘመን (9ኛው-11ኛው ሥርወ መንግሥታት) ለማስተካከል
ከጥንታዊው መንግሥት መጨረሻ በኋላ ሥነ ቅርስ ስለሚከተለው ዘመን (2758-2413 ዓክልበ. ግድም) ዝም ይላል። ከዚሁም ዘመን በሕዋላ (2413-2002 ዓክልበ. ግድም) ብዙ አይልም። የመቃብሮች ቁጥር እጅግ በመቀነሱ እንዲህ የሕዝብ ቁጥር መቀነሱ ይታወቃል። ፈርዖኖች እንደገና ሲታዩ፣ ዋና ከተማቸው እንደ ዱሮ በሜንፊስ ሳይሆን አሁን በሄራክሌውፖሊስ ይገኛል። ለታሪክ በእርግጥ የታወቁት ፈርዖኖች ጥቂት ናቸው፤ አከታተላቸውና ዘመኖቻቸው የሚጠራጠር ነው።
- ዋህካሬ ቀቲ 2417-2350 ዓክልበ. ግድም
- 1 ነፈርካሬ ቀቲ ? 2350-2331 ዓክልበ. ግድም
- መሪብታዊ ቀቲ 2331-2271 ዓክልበ. ግድም
- ሳ-ቀቲ ኡሰርመሬ ? 2271-2236 ግድም
- 2 ነፈርካሬ ቀቲ ? 2236-2232 ዓክልበ. ግድም
- ሸድ ኡሰርሃፒ ? 2232-2200 ግድም
- ነብካውሬ ቀቲ 2200-2167 ዓክልበ. ግድም
- ሰነን ነፈርካሬ? 2167-2147 ግድም
- መሪካሬ 2147-2081 ግድም
11ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
10ኛው ሥርወ መንግሥት በሄራክሌውፖሊስ እየገዛ፣ ተወዳዳሪው 11ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ ወደ ደቡብ ተመሠረተ። ይሄ ሥርወ መንግሥት በመጨረሻ መላውን ግብጽ ያዘ።
መካከለኛው መንግሥት ለማስተካከል
12ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
ሁለተኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው-17ኛው ሥርወ መንግሥታት) ለማስተካከል
13ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
- ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ 1819-1816 ዓክልበ. ግድም
- ሰኸምካሬ ሶንበፍ 1816-1812 ዓክልበ. ግድም
- ነሪካሬ 1812-1811 ዓክልበ. ግድም
- ሰኸምካሬ 5 አመነምሃት 1811-1808 ዓክልበ. ግድም
- አመኒ ቀማው 1808-1806 ዓክልበ. ግድም
- ሆተፒብሬ 1806-1803 ዓክልበ. ግድም
- ዩፍኒ 1803 ዓክልበ. ግድም
- 6 አመነምሃት 1803-1800 ዓክልበ. ግድም
- ሰመንካሬ ነብኑኒ 1800-1798 ዓክልበ. ግድም
- ሰኸተፒብሬ 1798-1796 ዓክልበ. ግድም
- ሰዋጅካሬ 1796 ዓክልበ. ግድም
- ነጀሚብሬ 1796 ዓክልበ. ግድም
- ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ 1795-1791ዓክልበ. ግድም
- ረንሰነብ 1791 ዓክልበ. ግድም
- ሆር አዊብሬ 1791-1783 ዓክልበ. ግድም
- ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው 1783-1781 ዓክልበ. ግድም
- ጀድኸፐረው 1781 ዓክልበ. ግድም
- ሰጀፋካሬ 1781-1776 ዓክልበ. ግድም
- ኹታዊሬ ወጋፍ 1776-1774 ዓክልበ. ግድም
- ኡሰርካሬ ኸንጀር 1774-1766 ዓክልበ. ግድም
- ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው 1766-1754 ዓክልበ. ግድም
- ሰኸተፕካሬ አንተፍ 1754-1744 ዓክልበ. ግድም
- ሴት መሪብሬ 1744-1741 ዓክልበ. ግድም
- 3 ሶበክሆተፕ 1741-1702 ዓክልበ. ግድም
- 1 ነፈርሆተፕ 1702-1690 ዓክልበ. ግድም
- ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ 1690-1684 ዓክልበ. ግድም
- መርሆተፕሬ 5 ሶበክሆተፕ 1684-1680 ዓክልበ. ግድም
- ኻውተፕሬ 6 ሶበክሆተፕ 1680-1676 ዓክልበ. ግድም
- ዋሂብሬ ኢቢያው 1676-1665 ዓክልበ. ግድም
- መርነፈሬ አይ 1665-1661 ዓክልበ. ግድም፤ ከርሱ በኋላ ያሉት ከጤቤስ ውጭ አልገዙም።
- መርሆተፕሬ ኢኒ 1661-1659 ዓክልበ. ግድም
- ሰዋጅተው 1659-1656 ዓክልበ. ግድም
- መርሰኸምሬ 1656-1653 ዓክልበ. ግድም
- ሰውጅካሬ ሆሪ 1653-1648 ዓክልበ. ግድም
- 7 ሶበክሆተፕ 1648-1646 ዓክልበ. ግድም
- መርኸፐሬ 1646 ዓክልበ. ግድም
- ሰኸቀንሬ 1646 ዓክልበ. ግድም
በ13ኛው ሥርወ መንግሥት ውድቀት 16ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ፣ ሌላው «የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት» በአቢዶስ ተነሡ።
14ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
ከከነዓን የደረሱ እረኞችና ነጋዴዎች በአባይ ወንዝ አፍ በስሜን ግብጽ ነጻ መንግሥት መሠረቱ። ይህ ለጊዜው ከ13ኛው ሥርወ መንግሥት ጋር አንድላይ ነበር (1821-1742 ዓክልበ. ግድም)፤ ዘመናቸው ግን እርግጠኛ አይደለም።
- ያክቢም ሰኻኤንሬ 1821-1811 ዓክልበ. ግድም
- ያዓሙ ኑብዎሰሬ 1811-1801
- ቃረህ ኻዎሰሬ 1801-1791
- አሙ አሆተፕሬ 1791-1786
- ሸሺ ማዓይብሬ 1786-1753
- ነህሲ 1753
- ኑያ 1752
- ሸነህ 1752-1747
- ሸንሸክ 1747
- ዋዛድ 1746-1742
- ያዕቁብ-ሃር 1742 ዓክልበ. ግድም፤ ከርሱ በኋላ ይህ ሥርወ መንግሥት ከጤቤስ ተሠረዘ።
15ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
ከመርነፍሬ አይ ዘመን ቀጥሎ (1661 ዓክልበ.) ሌሎች ከከነዓን ገብተው አዲስ ተወዳዳሪ መንግሥት በስሜን ግብጽ ተነሣ፤ እሱም ሂክሶስ (ኸካ-ሻሱ ወይም «ውጫገር አለቆች») ይባላል።
16ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
የ13ኛው ሥርወ መንግሥት ተከታዮች በጤቤስ ናቸው። በዚህም ዘመን አቢዶስ የራሱን የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት እንደ ነበረው ይታሥባል።
- ጀሁቲ 1646-1643
- 8 ሶበክሆተፕ 1643-1637
- 3 ነፈርሆተፕ 1636
- መንቱሆተፒ 1635
- 1 ነቢሪራው 1635-1614
- 2 ነቢሪራው 1613
- ሰመንሬ 1612
- በቢአንኽ 1612-1600
- ሰኸምሬ ሸድዋሰት 1600-1596
የሚከተሉት አጫጭር ዘመናት የገዙት ነገሥታት ቅድም-ተከተል እርግጠኛ አይደለም።
- 1 ደዱሞስ ? 1595
- ሞንተምሳፍ ? 1594
- መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ ? 1593
- 4 ሰኑስረት ? 1592
- 2 ደዱሞስ ? 1591
በ1590 ዓክልበ. ግድም የ15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን አፐፒ ጤበስን ማረከ።
17ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
ሂክሶስ ከጤቤስ ከወጡ በኋላ የ16ኛው ሥርወ መንግሥት ተከታዮች በጤቤስ ሆኑ። የገዙት ነገሥታት ቅድም-ተከተል እርግጠኛ አይደለም።
አዲሱ መንግሥት (18ኛው-20ኛው ሥርወ መንግሥታት ለማስተካከል
18ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
- 1 አሕሞስ 1558-1534 ዓክልበ.
- 1 አመንሆተፕ 1534-1513 ዓክልበ.
- 1 ቱትሞስ 1513-1501 ዓክልበ.
- 2 ቱትሞስ 1501-1487 ዓክልበ.
- ንግሥት ሃትሸፕሱት 1487-1466 ዓክልበ.
- 3 ቱትሞስ 1487-1433 ዓክልበ.
- 2 አመንሆተፕ 1435-1409 ዓክልበ.
- 4 ቱትሞስ 1409-1399 ዓክልበ.
- 3 አመንሆተፕ 1399-1361 ዓክልበ.
- አኸናተን 1361-1344 ዓክልበ.
- ንግሥት (?) ነፈርነፈርኑአተን 1344-1341 ዓክልበ.
- ስመንኽካሬ 1341-1340 ዓክልበ.
- ቱታንኻመን 1340-1331 ዓክልበ.
- አይ 1331-1327 ዓክልበ.
- ሆረምኸብ 1327-1300 ዓክልበ.
19ኛው ሥርወ መንግሥት ለማስተካከል
- 1 ራምሴስ 1300-1298 ዓክልበ.
- 1 ሰቲ 1298-1287 ዓክልበ.
- 2 ራምሴስ 1287-1221 ዓክልበ.
- መርነፕታህ 1221-1211 ዓክልበ.
- 2 ሰቲ 1211-1205 ዓክልበ.
- ሲፕታህ 1205-1199 ዓክልበ.
- ንግሥት ተዎስረት 1199-1197 ዓክልበ.