ሶበክነፈሩ
==
ሶበክነፈሩ | |
---|---|
የሶበክነፈሩ ምስል (የተጎዳ) | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1823-1819 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | 4 አመነምሃት |
ተከታይ | ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ |
ሥርወ-መንግሥት | 12ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | 3 አመነምሃት |
==
ሶበክነፈሩ (ወይም ነፈሩሶበክ) ግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) መጨረሻ ከ1823 እስከ 1819 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛች ሴት ፈርዖን (ንግስት) ነበረች። የወንድሟ 4 አመነምሃት ተከታይ ነበረች።
የተገኙት ሐውልቶቿ ሁሉ ራሳቸውን ያጡ ናቸው። የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ፈርዖኖች ዝርዝር መሠረት ሶበክነፈሩ ለ፫ ዓመታት፣ ፲ ወርና ፳፬ ቀን ነገሠች።
የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስበው፣ በእርሷ ዘመን (በ1821 ዓክልበ. ግ.) የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሷ ተገዥ ሆኖ ነገሠ። እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ። በጤቤስ ፈርዖኖች ፈቃድና ስምምነት ግዛታቸው በስሜን ግብጽ የንግድ ማዕከል ሆነ፤ ይህም በብሉይ ኪዳን ጌሤም የተባለው ሀገር ነው።
የ13ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ ተከተላት፤ የዚህም መጀመርያ ፈርዖን አሁን ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ እንደ ነበር ይታመናል። ግብጽ እንደገና ተከፋፍሎ የመካከለኛው መንግሥት መጨረሻ እና የ፪ኛው ጨለማ ዘመን መጀመርያ ይቆጠራል።
ቀዳሚው 4 አመነምሃት |
የግብፅ ፈርዖን | ተከታይ ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ |