==

ሰቀነንሬ ታዖ
የሰቀነንሬ ሬሳ ሳትን
የሰቀነንሬ ሬሳ ሳትን
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1566-1563 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰናኽተንሬ አሕሞስ
ተከታይ ካሞስ
ባለቤት 1 አሖተፕሲትጀሑቲ፣ ?አሕሞስ ኢንሃፒ
ሥርወ-መንግሥት 17ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት ? ሰናኽተንሬ አሕሞስ

==


ሰቀነንሬ ታዖላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (17ኛው ሥርወ መንግሥት) ለአጭር ወራት ምናልባት 1566-1563 ዓክልበ. አካባቢ በሂክሶስ ዘመን የገዛ ፈርዖን እንደ ነበረ ይታመናል።


በኋላ በአዲስ መንግሥት በተጻፈ ታሪካዊ ልማድ ዘንድ፣ የሂክሶስ ፈርዖን አፐፒ ወደ ሰቀነንሬ ደብዳቤ ጽፎ ጉማሬዎቹ ስላስቸገሩት እንዲያጥፋቸው አዘዘ። ሰቀነንሬ ግን ዘመቻ በሂክሶስ ላይ እንደ ጀመረ ይመስላል። ሬሳው ለሥነ ቅርስ የተገኘው ከጦርነት መሣርዮች ብዙ የራስ ቁስል አለበት፤ ሬሳውም በችኩላ ተዘጋጀ፣ ሂክሶስ ወገን እንደ ገደሉት ይታሥባል። ያም ሆነ ይህ ተከታዩ ካሞስ ዘመቻውን እንደ ተከተለ ይነገራል።

ሰቀነንሬ እንደ ቅድመኞቹ ጥንታዊ መንግሥት ፈርዖኖች በመምሰል ሦስት እኅቶቹን እንዳገባ ይነገራል። እናታቸው ተቲሸሪ ነበረች። ከልጆቻቸው መካከል ካሞስና የካሞስ ተከታይ 1 አሕሞስ (የአዲስ መንግሥት መስራች) አሉ።

ቀዳሚው
ሰናኽተንሬ አሕሞስ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1566-1563 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ካሞስ