ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ
==
ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ | |
---|---|
የ፪ ሶበክሆተፕ ኻአንኽሬ ስዕል ከአቢዶስ (አሁን በሉቭር ፓሪስ) | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1795-1791 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ነጀሚብሬ |
ተከታይ | ረንሰነብ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1796 እስከ 1791 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የነጀሚብሬ ተከታይ ነበረ።
ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር «ሶበክ... ..ሬ» ይታያል፤ አሁን እንደሚታሠብ ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ ከእርሱ በፊት ስለ ነገሠ ይህ ኻአንኽሬ በዘመናዊ ጥናቶች «፪ ሶበክሆተፕ» ይባላል፤ በፊት ግን እንደ «፩ ሶበክሆተፕ» ተቆጠረ። ሙሉ ስማቸው «ሶበክሆተፕ ኻአንኽሬ» ከአንድ የአቢዶስ ቤተ መቅደስ ዓምድ ይታወቃል። ተከታዩ ረንሰነብ ነበር።
ቀዳሚው ነጀሚብሬ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ረንሰነብ |
ዋቢ ምንጭ
ለማስተካከል- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)