አመኒ ቀማው ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1808 እስከ 1806 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰኸምካሬ 5 አመነምሃት ተከታይ ነበረ።

አመኒ ቀማው
የአመኒ ቀማው ሀረም አቀማመጥ
የአመኒ ቀማው ሀረም አቀማመጥ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1808- 1806 ዓክልበ.
ቀዳሚ ሰኸምካሬ 5 አመነምሃት
ተከታይ ሆተፒብሬ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት 5 አመነምሃት?

ስሙ ከቶሪኖ ቀኖና ነገስታት ዝርዝር ጠፍቶ ቢሆንም፣ የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስረዳው የ፭ አመነምሃት ልጅና ተከታይ ይሆናል። ስያሜው «አመኒ ቀማው» ማለት «የአመኒ ልጅ ቀማው» ይመስለዋል፤ ይህም «አመኒ» ማለት ፭ አመነምሃት እንደ ነበር ይመስላል። የሚታወቀው ሀረሙ በ1949 ዓ.ም. በዳሹር ስለ ተገኘ ነው።

በራይሆልት አስተሳሰብ፣ የአመኒ ቀማው ተከታይ ሆተፒብሬ ይሆናል። የሆተፒብሬ ሌላ ስም «ቀማው ሲሃርነጅሀሪተፍ» ሲሆን ማለቱ በራይሆልት ዘንድ «የቀማው ልጅ ሲሃርነጅሀሪተፍ» መሆን አለበት።

ቀዳሚው
ሰኸምካሬ 5 አመነምሃት
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1808-1806 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሆተፒብሬ

ዋቢ ምንጭEdit

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)